ሲዳማ ኔትን ጨምሮ 16 የኣሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እገዳ ተጣለባቸው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ 16 የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እገዳ ጣለ። በደቡብ ክልል ፍቃድ አግኝተው ስልጠና የሚያካሂዱ 36 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትን ፥ በክልሉ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሲባል የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ተቋማቱን በአመታዊ እቅዱ ያሳትፋቸዋል። የቢሮው ሃላፊ አቶ ታገሰ ኤሮሞ እንደሚሉት ፥ እንዲሳተፉ በተደረገበት እቅድ ደግሞ አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ለማሰልጠን ሊያሟላ የሚገባቸው መስፈርቶች ተካተዋል። የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ባለሙያዎች በተቋማቱ ላይ ባደረጉት ግምገማ ፥ 8 ያህሉ በተገኘባቸው ጉድለት በማስጠንቀቂያ ሲታለፉ ፥ 16ቱ ደግሞ ስልጠናውን የሚሰጡበት ተገቢ ቦታ የሌላቸው ፣ የራሳቸው የማለማመጃ መኪና ሳይኖራቸው በኪራይ የሚጠቀሙ ፤ በቂ ክህሎት ያለው አሰልጣኝ ሳይኖራቸው በመስራታቸው እርምጃው ሊወሰድባቸው እንደተቻለ ይናገራሉ። 12 ተቋማት ደግሞ በተካደው ግምገማ አንጻራዊ ለውጥ በማምጣታቸው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የተደረጉ ናቸው። በቤንች ማጂ ፣ ስልጤ ዞን ወራቤ ፣ ጋሞ ጎፋ ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጉራጌ ዞኖች ላይ የሚገኙ ናቸው እነዚህ ተቋማት። ሲዳማኔት ፣ ፊውቸር ላይት ፣ ዎስመካ ፣ ጋላክሲ ፣ መካነ ኢየሱስ ፣ መገናኛ ፣ ወራቤኬሪ ፣ ፍሬም ፣ ኢሻ ፣ ዱዛ ፣ ጂፎር ፣ ወገሹር ፣ አግነት ፣ እና ሚቴማ እርምጃው የተወሰደባቸው ተቋማት ናቸው። ተቋማቱ በስልጠና ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በተጓደለ መልኩ እንዳያስመርቁም ፤ በየጊዜው ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው ስልጠናውን እንዲጨርሱ አቅጣጫ መቀመጡን ነው ሃላፊው የተናገሩት። እገዳ ስለተጣለባቸው ተቋማት ህብረተሰቡ እንዲያውቅ