«የጊዳቦ መስኖ ግድብ ግንባታ በተያዘው ዓመት ይጠናቀቃል»-ኢንጂነር ብሥራት ደምሴ የጊዳቦ መስኖ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት የሥራ ሂደት ባለቤት
በአካባቢው እዚህም እዚያ ዛፎች ቁጥቋጦዎች በብዛት ይታያሉ። አልፎ አልፎ ከሚታዩ መለስተኛ ኮረብታዎች በስተቀር አካባቢው ሜዳማ ነው። በስፍራው ባሉት ሁለት መለስተኛ ኮረብታዎች መካከል የጊዳቦ ወንዝ ሰንጥቆ ያልፋል። በእዚህ ሥፍራ የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል። ትልልቅ ገልባጭ ተሽከርካሪዎች ያለፋታ አሸዋ ያራግፋሉ። አፈር ይጭናሉ፤ ጠጠር ይደፋሉ። ኤክስካቫተሮች፣ ሎደሮችና ሌሎች ማሽነሪዎች በየሥፍራው ይቆፍራሉ። ይጠርጋሉ። ያስተካክላሉ። ይደመድማሉ። ሠራተኞች በሥራ ተጠምደዋል። ከፊሎቹ አርማታ ይሞላሉ። የተወሰኑት ማሽነሪዎችን በማንቀሳቀስ ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያቀርባሉ። ሁሉም ሠራተኞች የአካባቢው ሙቀት ሳይበግራቸው ጥድፊያ ላይ ናቸው። በጊዳቦ የመስኖ ግድብ ግንባታ ለማፋጠን 24 ሰዓት ሥራው አይቋረጥም። በሌሊት በየሥፍራው ያሉት ትልልቅ ፓውዛዎች ጨለማውን ገፈው ብርሃን አላብሰው ታል። በሌሊቱ ግማሾቹ ሠራተኞች ሲያርፉ ቀሪዎቹ ሌሊቱን በሙሉ ሲሰሩ ያነጋሉ። የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በአማካሪው የውሃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት እና በውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ተቋራጭነት በኦሮሚያና በደቡብ አጐራባች ክልሎች ውስጥ ከ 13 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት የሚገነባ ፕሮጀክት ነው። ግድቡ የሚገነባው በጊዳቦ ወንዝ ላይ ነው። ፕሮጀክቱ መንግሥት በመደበው ከ 258 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ይገኛል። ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በላይ እንደሆነው የሚገልጹት በውሃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት የፕሮጀክቱ አማካሪ መሐንዲስ ኃላፊ ኢንጂነር ብርሃኑ ውቤ ናቸው። እሳቸው እንዳሉት በፕሮጀክት ግንባታው የግድብ፣ የትርፍ ውሃ ማስወገጃ የተያዘ ውሃ