ሲዳማ ኔት ኮሌጅ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል በመሳተፍ ላይ ነው
ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጀመር አዘጋጁ አስታወቀ። የፌስቲቫሉ አዘጋጅ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበር ትናንት በሴንትራል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ አራተኛው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ . ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ይጀመራል። ይሄው መታሰቢያነቱ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተሰጠው የ 2005 ዓ . ም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ከኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች አምስት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ አሥራ አምስት በድምሩ ሃያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ማኀበሩ ገልጿል። በስፖርት ፈስቲቫሉ ማኀበሩ በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ውድድር እንዲደረግ ዝግጅት ቢያደርግም ተሳታፊ ተቋማቱ በስምንቱ ብቻ ለመሳተፍ በመመዝገባቸው በእነዚሁ ስፖርቶች ውድድሩ እንደሚካሄድ የማኀበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ግርማዬ አስታውቀዋል። ለአሥራ ሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የስፖርት ፌስተቫል ለመሳተፍ ከክልሎች ለሚመጡ ስፖርተኞች በሴንትራል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ ማረፊያ መዘጋጀቱንም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። በስፖርት ፌስቲቫሉ ላይ ሃያዎቹን ተቋማት የወከሉ ሦስት ሺ የሚጠጉ ስፖርተኞች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ አብነት አስረድተዋል። ለፌስቲቫሉ ስኬት ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ለዚህ ተግባራቸውም በኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህር