የወንዶገነት ደንና አሳሳቢ የሥነ ምህዳር ቀውሶች
ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሻሸመኔ ከተማ ሲደርሱ ቀኙን ትተው ወደ ግራ ሲታጠፉ አንድ አረንጓዲያማ አካባቢ የሚያደርሰውን አስፋልት ያገኛሉ፡፡ ከዚያም 11 ኪ.ሜ እንደተጓዙ በአገራችን የመጀመሪያው በደን የተሸፈነ ስፍራና በአገሪቱ ብቸኛው የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ይደርሳሉ፡፡ ቀጥሎም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች መዳረሻ ወደሆነው ዋቢሸበሌ መዝናኛ ሆቴል ከሦስት ኪ.ሜ ጉዞ በኋላ ያገኛሉ፡፡ በአሳብ ይዤአችሁ የምወስዳችሁ ሥፍራ ወንዶ ገነት ይባላል፡፡ እነዚህን ከላይ የዘረዘርኳቸው ስፍራዎች ከ30 ዓመታት በፊት በነበሩበት ማራኪ የተፈጥሮ ውበታቸው ጋር ማየት በእርግጥ የማይቻል በመሆኑ የሰነድና የስው አስረጅ ካላገኙ የቀድሞውን ታሪክ ማወቅ አስቸጋሪ ይሆንቦታል፡፡ በአገሪቱ በደን ሽፋንና በተፈጥሮ መስህብ የማንንም ቀልብ የመግዛት አቅም የነበረው ስፍራ ዛሬ ትዝታ የመሆኑ ምስጢርና ተያያዥ የሥነ ምህዳር ችግሮች ሰለባ ሆኗል፡፡ ወንዶገነትና የአረንጓዴው ዘመቻ በ1970ዎቹ መጀመሪያ በደርግ የሥልጣን ዘመን የአረንጓዴው ዘመቻ ደን ሠርቶ ማሳያ ማዕከል የነበረው ወንዶገነት ከተፈጥሮ ጫካ በተጨማሪ የባሕር ዛፍና ጥድ እንዲሁም ሌሎች ዛፎች የተሸፈነ እጅግ ማራኪ ስፍራ ነበረ፡፡ በወቅቱ በስዊድናውያን ዕርዳታ የተቋቋመው የደን ኮሌጅ ዓላማም ከአካባቢው ባለፈ በአገሪቱ የደን ሀብትን ማስፋፋት ስለነበረ የወረዳው ዙርያ በዛፎች እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡ ከነዚህም አካባቢዎች ዛሬ የጫት ማሳ ሆነው የቀሩትንና የቀድሞውን መላጌ ወንዶ ሥጋ ፋብሪካ (አሁኑ ኤልፎራ) የሚገኝባቸው ቀበሌዎችን ያካትታል፡፡ የደን ኮሌጅ ከሚገኝበት ሆሻ ከተማ ዙሪያውን ስድስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን ሌላ ትንሽ ከተማ ኬላና በ