አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት አዳዲስ አገልግሎቶችን እየሠጠ ነው
አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት የምስጢራዊ ህትመት፣ የማማከር፣ ጥገና፣ የግራፊክ ዲዛይንና ፕሌት ቀረፃ እንዲሁም የህትመት ቴክኖሎጂ ሥልጠና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። ድርጅቱ የተመሰረተበትን 82 ኛ ዓመቱንና የሐዋሳ ቅርንጫፍ የተቋቋመበትን ስድስተኛ ዓመት ምስረታ በዓልን እንዲሁም የደንበኞች ቀንን በሐዋሳ ከተማ አክብሯል ። በከተማዋ ሌዊ ሆቴል ከደንበኞች ጋር የፓናል ውይይት ባካሄደበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተካ አባዲ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ብቸኛው የህትመት ቴክኖሎጂ ሥልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው ። ድርጅቱ በእስካሁኑ ሂደት ወደ 500 ያህል ሠልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን፤ ሁሉም ምሩቃን ወደ ሥራው ዓለም ተቀላቅለዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ምሩቃን ድርጅቱ የማሽንና የሌሎች መሳሪያዎች ድጋፍ ያደርጋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ ድርጅቱ ከአዳዲስ አገልግሎቶች መካከል የምስጢራዊ ህትመት አገልግሎትን ጀምሯል። በእስካሁንም ሂደት ከሠራቸው ምስጢራዊ ህትመቶች መካከል የደቡብና የሐረሪ ክልልን እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ፈተናን ለአብነት ጠቅሰዋል። ይህንንና ሌሎችንም ምስጢራዊ ህትመቶችን በቀጣይ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አመልክተዋል። ድርጅቱ የግራፊክ፣ የዲዛይንና የፕሌት ቀረፃ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተለይም በሰዓት እስከ አንድ ሺ ድረስ ፕሌት ማውጣት የሚችል ማሽን መግዛቱን ተናግረዋል። ማተሚያ ድርጅቱ ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የማማከርና የጥገና አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የበርካታ ዩኒቨርሲቲዎችን ማተሚያ ማሽኖች ለመጠገን የሚያስችሉ የጥገና ስምምነት መፈራረሙን ገልጸዋል። በቅርቡም የጥገና ሥራው እንደሚጀመርም ነው