በቅርቡ ሲዳማ ውስጥ የምካሄደውን የኣካባቢ ምርጫ ለማሸነፍ ብቸኛው ኣማራጭ የህዝቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን መመለስ ብቻ ነው
ከሁለት ወራት በኃላ በኢትዮጵያ ብሎም በሲዳማ የምከሄደው የኣከባቢ ምርጫ ላይ ለመሳተፊ ሃዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ኣራት የምሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ተመዝግበው የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን ከኣገሪቱ ምርጫ ቦርድ ሰምተናል። እነዚህ በሲዳማ እንወዳደራለን ብለው የምርጫ ምልክት የወሰዱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ( ሲኣን ) ፤ ደኢህዴን _ ኢህኣዴግ፤ኢዴፓ እና ኢህኣፓ ናቸው። በነገራችን ላይ በምርጫ ቦርድ ኣደራጃጀት ሃዋሳ እና ሲዳማ የምል ክፍፍል የለም። በኣሁኑ ጊዜ ሃዋሳ እና ሲዳማ ተብለው የተከፋፈሉ ኣከባቢዎችን የምወክሉ ሰዎች በማንኛውም መንገድ የሲዳማ ተወላጆች መሆን ኣለባቸው። ምክንያቱ በዚህ ምርጫ ላይ ብቻ ሳይሆን በተለይ ከሶስት ኣመት በኃላ በምካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሲዳማን ብሄር የምወክሉ ግለሰቦች ከሁሉም የሲዳማ ኣካባቢዎች መምጣት ስላለባቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ከሃዋሳ የምወከሉት ግለሰብ የሲዳማ ተወላጅ ካልሆኑ የሲዳማን ህዝብ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የምወክሉት ተወካዮች ቁጥር ያሳንሳል በተጎዳኝ በሃዋሳ የምያሸንፈው የሌላ ብሄርሰብ ተወላጅ ለብሄረሰቡ ተጨማር የተወካይ ቁጥር ይጨምርለታል ማለት ነው። ይህ ማለት ቀድሞም ብሆን የሲዳማ ህዝብ ብዛት እና በተወካዮች ምክር ቤት ያለው ውክልና ተመጣጣኝ ኣይደለም የምል ኣመለካከት ያጠናክራል። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ በዚህ ጽሁፍ በኣራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ትኩረት ከመሰጠት ይልቅ በሁለቱ ላይ ማለትም በሲኣን እና በደኢህዴን ላይ ትኩረት ለመሰጠት ፈልጋለሁ። እስቲ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይዘው ነው የቀረቡ ? ለሲዳማ ህዝብ የምጠቅም ምን ይዘዋል ? በምሉት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንጫዎት። በኣጠቃላይ በኣገሪቱ ደረጃ ሲታይ ‹‹በግንባ