Posts

The current regime and its policies in Sidama While noting some positive changes initiated by the current regime, ... The following are details of what has occurred in Sidama since the replacement of an overly arrogant central rule by a ...

Image
The current regime and its policies in  Sidama  While noting some positive changes initiated by the current regime,  ...  The following are details of what has occurred in Sidama  since the replacement of an overly arrogant central rule by a  ... Read more:  http://books.google.com.gt/books?id=sbddoOdnkyAC&pg=PA174&dq=sidama&hl=en&sa=X&ei=RjcJUZa8B4iu8ASjnYGwCw&ved=0CEcQ6AEwBg#v=onepage&q=sidama&f=false

ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡

Image
በደቡብ ክልል ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ ተሰራጨ አዋሳ ጥር 22/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ የጀት ዓመት ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያውን በማረጋጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ የኔወርቅ ቁምላቸው ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ ያለውን ህብረተሰብ ከሚጎዱ የንግድ አሰራሮች በመከላከል ገበያን የማረጋጋቱ ስራ ውጤታማ ሆኗል፡፡ የክልሉ መንግስት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ስርጭት የሚመራበትን አሰራር ቀይሶ በሁሉም አከባቢ የስራ መዋቅሮችን በመዘርጋት ባለፉት ስድስት ወር ከ508ሺህ 054 ኩንታል በላይ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያን የማረጋጋት ስራ ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ ስርጭቱ ፍትሃዊና ተደራሽ በሆነ መንገድ የተከሄደው በየአከባቢው የሚገኙ የጅንአድ ቅርንጫፍ ማዕከላት፣ ከ14 ዞኖችና ከ22 የከተማ አስተዳደር በተመረጡ የጅምላ ንግድ ፈቃድ ባላቸው ነጋዴዎችና በተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው ብለዋል፡፡ በዘይት አቅርቦት በኩል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በስምንት የጅንአድ ማዕከላትና በየከተሞች በተቋቋሙ ዩኒየኖች አማካኝነት ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና ገበያን ለማረጋጋት የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና ስርጭቱን ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተደራሽ ለማድ

በዞኑ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ተሰማሩ

Image
አዋሳ ጥር 21/2005 በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ተሰማሩ፡፡ የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ትናንት እንደገለጹት በግማሽ ዓመቱ አምስት ባለሃብቶች ፈቃድ በማውጣት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል ስራ ጀምረዋል፡፡ ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ግብርናና ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙበት አመልክተዋል፡፡ ባለሃብቶቹ ለ88 ቋሚና 894 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸው አንዳንድ ከተሞች ላይ ባለፈው ዓመት የተጀመሩ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከ5 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን አስረድተዋል፡፡ መምሪያው በገጠር የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጥናትና በመለየት ለባለሃብቶች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብተቶች ከ600 ሄክታር በላይ የገጠር መሬት አዘጋጅቶ መስጠቱን የስራ ሂደቱ አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም ለበርካታ ባለሃብቶች የፈቃድ እድሳትና ተጨማሪ የማስፋፊያ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው ከዚህ ቀደም ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችን በመከታተልና ድጋፍ በመስጠት በፍጥነት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሂደት ለማመቻቸት ባደረገው ጥረት 288 ፕሮጀክቶች የአገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ አዲስ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ከገቡት ባለሃብቶች መካከል አቶ ብርሃኑ አድማሱና አባተ አርጊሶ በሰጡት አስተያየት መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ በርካታ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥ እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በድህነት ላይ ለሚደረ

Ethiopia: Who Is More Ethiopian?

COLUMN In every way, the political opposition parties of the 2005 elections were irresponsible hooligans who did not even know their own goals. Given their smear campaign, I have always wondered how they could have undertaken the job of governance had they succeeded in their quest for power. They were dividing the nation even before gaining votes. They were contradictorily promising tax cuts, whilst still planning to increase public spending. They lacked the minimum internal stability necessary for smooth administrative functioning. Amazingly, they also invited the international community to interfere in the internal affairs of the nation they were seeking to administer, with little concern for its sovereignty. I am always surprised to hear people lamenting about the 2005 elections, as if it was the turning point for Ethiopian democracy, whereas, rather, it was the point where our aspirations for democracy were crushed. By and large, Ethiopian minorities were deeply concer

ደኢህዴን በሲዳማ ዞንና በከተሞች የሚወዳደሩ ከ115ሺህ በላይ እጩዎችን ስያስመዘግብ ሲኣን ግን እስከኣሁን እጩ ኣላስመዘገበም ተባለ

Image
ሀዋሳ ጥር 20/2005 ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞንና በሌሎች ከተሞች በመጪው ሚያዝያ ለሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ደኢህዴን ከ115 ሺህ በላይ እጩዎችን ማስመዝገቡን የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በዞኑና በከተሞቹ ለሚካሄደዉ ምርጫ ከ1ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውም ተገልጧል ። የጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ደኢህዴን ያስመዘገባቸው 115 ሺህ 368 ዕጩዎች ለዞን ፣ለወረዳ ፣ለከተማና ለቀበሌ ምክር ቤቶች ድርጅቱን ወክለው የሚወዳደሩ ናቸው። ደኢህዴን ለሲዳማ ዞን ፣ለሀዋሳ ፣ለይርጋለምና ለአለታ ወንዶ ከተሞች አስተዳደሮችና ለ21 ወረዳዎች ካስመዘገባቸው ዕጩዎች ውስጥ 105 ለዞን ምክር ቤት፣ 277 ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት፣ 1ሺ524 ለወረዳና ፣113 ሺህ 462 ለቀበሌ ምክር ቤት የሚወዳደሩ መሆኑን ተናግረዋል። ለምርጫው በዞኑና በከተማ አስተዳደሮች ፣በወረዳዎችና በቀበሌ ለመወዳደር ካስመዘገባቸው ዕጩዎች ውስጥ 53 ሺህ 289 ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህ ዕጩዎች 38 ለዞን ምክር ቤት ፣110 ለከተማ ምክር ቤት፣ 484 ለወረዳ የሚወዳደሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ለቀበሌ ምክር ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ አስረድተዋል። በዞኑ ለመወዳደር ተመዝግበዉ የመለያ ምልክት ከወሰዱ አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ደኢህዴን፣ ፣ሲአን፣ኢዴአፓና ኢራፓ ውስጥ እስካሁን ዕጩዎቹን ያስመዘገበው ደኢህዴን ብቻ መሆኑን አስተባበሪዉ አመልከተዉ የዕጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው በነገዉ እለት በመሆኑ ፓርቲዎቹ ዕጩዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል። በተጨማሪም በዞኑ በተቋቋሙ 1648 የምርጫ ጣቢያዎች እስካለፈው አርብ ድረስ 1 ሚሊዮን 33 ሺህ መራጮች መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ 472 ሺህ 764 ሴቶች መሆናቸውን አቶ ብርሃ