ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ከጌታ መንገድና ከኢህአዴግ መንገድ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨረቃን ከሰማይ አውርዱልን እያለ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ ያለው ግልጽነትን፣ ቀጥተኝነትን፣ ቅንነትንና ሀቀኝነትን አውርዱልን ነው። ዴሞክራሲን አውርዱልን ነው። ቁሳዊ ልማት ብቻውን አይበቃም፣ ሰብአዊና መንፈሳዊ ልማትንም አውርዱልን ነው። ዶ/ር ኃይሉ አርአያ የጌታ ኢየሱስ መንገድ ስል የክርስትና ሃይማኖት ዕምነት ቀኖናውን (ዶግማውን) ሳይሆን ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲያስተምር ያሳየውን የቀናነት፣ የሃቀኝነት፣ የግልጽነት፣ የፍትሓዊነት፣ የእኩልነት፣ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲያዊነት፣ የመተሳሰብ፣ የመፈቃቀር፣የመከባበር፣ የመተማመን... መንገድ ማለቴ ነው። ይህ መንገድ የክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የእስልምና እንዲሁም የሌሎች የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች መንገድ ነው። በዚህ መንገድ በሚመራ ህብረተሰብ ውስጥ በዕውቀት (በችሎታ) ማነስ ወይም በተራ ስህተት ወይም በስንፍና ካልሆነ በስተቀር ሆን ተብሎ፣ ታስቦና ታቅዶ በተንኮል በሚፈጸም ቂም በቀል፣ ግፍና በደል አገርና ሕዝብ አይጎዱም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ መንገድ ቢመራ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት የመላቀቅ፣ በዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሥርዓት የመመራትና በነፃነት፣ በሠላምና በአንድነት የክብር ኑሮ የመኖር ተስፋው እየራቀ ሳይሆን እየቀረበና እየለመለመ ይመጣል። የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመራው በዚህ መንገድ ሳይሆን በኢህአዴግ መንገድ ነው። የኢህአዴግ መንገድ ደግሞ በአብዛኛው ከላይ ከተገለጸው መንገድ የተለየ ነው። በእኔ እምነት የኢህአዴግ መንገድ ቀናነት፣ ግልጽነትና ሀቀኝነት የሚጎድለው መንገድ ነው። ከታሪካቸው እንደተረዳሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከልብ አማኝ ክርስቲያን ና