‹‹የምርጫ ምልክቴ የሆነውን አውራ ዶሮ ከምርጫ ቦርድ የወሰድኩት ሐዋሳን ጨምሮ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄው የክልል ጥያቄ ስለሆነ ሕዝቡ በዚህ ምርጫ ተሳትፎ በምርጫ ካርድ መብቱን ሊያስከብር ስለሚፈልግ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ወደ ምርጫ እንድንገባ ወስኗል›› የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ ጸሃፊ አቶ ለገሰ ላቃሞ
በመጪው ሚያዚያ ወር በሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ የአፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ አስቀድሞ በምርጫው ፍትሃዊነት እና በሌሎች 18 አጀንዳዎች ላይ ሊወያዩ እንደሚገባ በማመን ፒትሽን ተፈራርመው ጥያቄያቸውን ለምርጫ ቦርድ ካስገቡ 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች አምስቱ የምርጫ ምልክታቸውን የወሰዱ ሲሆን 28ቱ ፓርቲዎች በቅርቡ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠሩ አስታወቁ፡፡ የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የፓርቲዎች ሰብሳቢ አቶ አሥራት ጣሴ እንደገለፁት፤ ፓርቲዎቹ ጥር 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሦስት በላይ የአዳራሽና የመስክ ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ያቀዱ ሲሆን ለአዲስ አበባ መስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ፈቃድ ክፍል ደብዳቤ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳውን በመቃወም ፒትሽን ከፈረሙት 33 ፓርቲዎች ውስጥ አምስቱ የምርጫ ምልክታቸውን እንደወሰዱ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡ ፡ የኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ግምባር(ኢፍዲሃግ)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት(ኢዲህ)፣ የባህር ወርቅ መስመስ ሕዝቦች ዲሞክራሲ ድርጅት(ባመህዴድ)፣ ዱቤና ደጀኔ ብሄረሰብ ዲሞክራሲያዊ (ዱብዴፓ) የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ(ሲአንፓ) የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ “በሲዳማ ዞን ሕዝብ ጥያቄ በምርጫ ለመሳተፍ ተገደናል” ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ፓርቲ በበኩሉ የምርጫ ምልክት ወስዶ ለምርጫው ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም በትግል ከ28ቱ ፓርቲዎች ጎን እንደሚሰለፍ ገልጿል፡፡ የ28ቱ ፓርቲዎች ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ “የምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ጥያቄዎች ሳይመልስ ዐዋጁን ጥሶ ሕጋዊም፣ ሞራላዊም፣ ዲሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መጠንከር ወሳኝነት ያላቸ