Posts

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱ ተገለጸ

አዋሳ ጥር 08/2005 (ዋኢማ)  - በደቡብ ክልል በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የአከባቢ ምርጫ እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።  ኃላፊው አቶ አብርሃም ገዴቦ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እስከትናንት ከሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበው ካርድ ወስደዋል፡፡  ካርድ ከወሰዱት መካከል አንድ ሚሊዮን 168ሺህ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ መራጮቹ ምዝገባ ያደረጉት በክልሉ 14 ዞኖች፣ 4 ልዩ ወረዳዎችና በ22 የከተማ አስተዳደር በተቋቋመው 8ሺህ 130 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን ገልፀው በክልሉ ሰባት ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡  በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎቹ 40 ሺህ ስድስት መቶ ምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫውን ስራ ለማስፈፀም እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው በተመሳሳይ ቁጥርም የህዝብ ታዛብዎች ተመርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡  የአከባቢ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ ህብረተሰቡና ሌሎች የባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡  የምርጫ አስፈፃሚዎች በበኩላቸው ህዝቡ ዛሬ ነገ ሳይል በመራጭነት ተመዝግቦ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠለትን መብት መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡  http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=7034:----400-----&catid=58:2011-08-29-12-55-21&Itemid=383

በ2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ ምርጫ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች ተመዝግበዋል

Image
አዲስ አበባ ጥር 14/2005 በመጪው ሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ አስተዳደሮች ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው። በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከታህሳስ 22 እስከ ጥር 13 /2005 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታወቋል፡፡ የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 10 ሚሊዮን 794 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ ቦርዱ በአጠቃላይ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመምረጥ ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጭ መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በተለያየ ምክንያት የመራጭነት ካርድ ያልወሰዱ መራጮችም በቀሪዎቹ 10 ቀናት የመራጭነት ካርዱን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4804&K=1

Ethiopia: Two Deadlines Gone, Only Five Collect Election Symbols

Legesse Lanikamo, secretary of the Sidama Liberation Movement, says his party decided to participate in the election "after a long discussion with the Sidama people," although he still vows allegiance to the cause of the 33 parties.   On the press conference held at the head office of the Blue party on Tuesday, Asrat Tase, the chairperson of the 33 parties and Gebru Gebremariam, executive member of Medrek, declared that they will be taking their case to the court if the election board does not accept their claim. Only five of the 33 parties that are in dispute with the National Electoral Board of Ethiopia, have collected their candidature symbols for the local election, which may not see the participation of the remaining 28 parties. The five that have joined the list are; the Ethiopian Justice & Democratic Front, Sidama Liberation Movement, Dube & Degeni Nations Democratic Party, Ethiopian Democratic Unity and Yebaher Work Mesmes People D
Image
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ   ሲዳማ በደኢህዴን/ኢህአዴግ ዘመን በሲህዴድ አመራር ወቅት የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች   1. የሲዳማ ዞን መስተዳድርና ሲህዴድ የአመራርና የፖለቲካ ስልጣን በእጃቸው በነበረበት ወቅት በርካታ የልማት ስራዎች እንደተጀመሩ ከላይ ተገልጿል፡፡ ከተጀመሩ የልማት ስራዎች መካከል በተለይም የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግንባታና በየወረዳውና በየቀበሌው የተስፋፋው መደበኛ ያልሆኑ የት/ ተቋማት፤ በውጭና በሃገር ውስጥ በርካታ የሲዳማ ልጆች የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲወስዱ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች፣ 2. ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የቦና ሆስፒታል ግንባታ፣ 3. በሰው ጉልበት የሚሰሩ በርካታ ወረዳዎችን የሚያገናኙ መንገዶች፣ 4. የሲዳማ ልማት ኮርፖሬሽን፣ የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ፣ በይርጋለም የሚገኘው ፉራ የልማትና ጥናት ምርምር ተቋም፣ የሐዋሳ መሐል ከተማ ጉዱማሌ የገበያ ማዕከላት መመስረትና መገንባት፣ 5. የሲዳማ አስተዳደር አባላትና የልማት መስሪያ ቤት ተወካዮች በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በአውሮፓና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በአካደሚክ ትምህርትና በመስክ የስራ ልምድ ጉብኝቶች ሁሉ ለሲዳማ ሕዝብ ልማትና የእድገት ጥማት ምላሽ የሰጡና ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች በዚያው ፍጥነት ቢቀጥሉ ኖሮ ዛሬ የሲዳማ ዞን የት ሊኖር እንደሚችል መገመትም አያዳግትም፡፡   እነዚህና በዝርዝር ያልቀረቡ የልማት ስራዎች የተሰሩት በዋናነት የሲዳማ ዞን መስተዳድር ከአየርላንድ መንግስት ባገኘው የልማት ቀጥተኛ ድጋፍ ሲሆን የመንግሥት ድጎማም እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ሲህዴድ ከከሰመ በኋላ በሲዳማ ላይ የተፈጸሙ አሉታዊ ተፅዕኖዎች የደኢህዴን መሰሪ አመራር የድርጅታቸው ዋናው ዓላማና ግብ የሲዳማን ህዝብ መብት

ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዋና የሥራ ሂደት  ጊዜያዊ አስተባባሪ ወይዘሮ መስከረም ባህሩ እንደተናገሩት ባለሦስት ሊትር 91 ካርቶንና ባለ አምስት ሊትር 234 ካርቶን ዘይት በአይሱዙ መኪና ተጭኖ በአንድ ነጋዴ መጋዘን ሲራገፍ ከክልሉ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በደረሰ ጥቆማ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በገንዘብ ሲተመን ከ138 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን   ወደ ኦሮሚያ ክልል ጎዴ ዞን የሚሄድ እንደነበር ነው የገለፁት፡፡ በተጠርጣሪው መጋዘን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ባለ 2ዐ ሊትር 336 ጀሪካን ዘይትም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነም አስተባባሪዋ ተናግረዋል፡፡ ባልደረባችን አደገ አየለ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/05TirTextN305.html