“ገዥውን ፓርቲ የሚጠቅሙ እየመሰላቸው በምርጫ ወቅት ችግር የሚፈጥሩ አስፈጻሚዎች አሉ”
አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕና የአስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከአራት ወራት በኋላ ሚያዝያ 6 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ግልጽና ተዓማኒ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለት ጀመርኩ ካለ ሰነባብቷል፡፡ ባስቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የምርጫ ቁሳቁሶችን ከማሳተም፣ ከማዘጋጀትና ከማሠራጨት ጐን ለጐን ደግሞ፣ ቀደም ብሎ ማከናወን ቢገባውም በምርጫው ዙሪያ ውይይትና ሥልጠና በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ቦርዱ እያደረጋቸው ከሚገኙት የምርጫ ክንውኖች መካከል ታህሳስ 7 እና 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል ለጋዜጠኞች የሰጠው የሁለት ቀናት ሥልጠና ተጠቃሽ ነው፡፡ ሥልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምህር ዶክተር ገብረ መድኅን ስምዖንና በተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕና የአስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ናቸው፡፡ አቶ አስመላሽ “የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግና አፈጻጸሙ” በሚል ርዕስ ባዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፍ ዙሪያ የምርጫ ቦርድ አባላትንና ሌሎች የምርጫ ክንውኖችን በሚመለከት ከሥልጠናው ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አቶ አስመላሸ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ ታምሩ ጽጌ እንደሚከተለው አዘጋጅቶታል፡፡ ጥያቄ፡- የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባላት ገለልተኛ ናቸው ብለው ያምናሉ? አቶ አስመላሽ ፡- የምርጫ ቦርድ አባላት ገለልተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም ለማለት ዋናውና አንዱ መሠረታዊ ጉዳይ፣ የሚለዩበትን መሠረታዊ ነገር መፈተሽ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድ አ