Posts

ለትምህርት ስርዓታችን ህልውና ከፖለቲካዊ ብልጠት ይልቅ ብልህነት ያሻል

  Written by  የተከበሩ አቶ ሙሼ ሰሙ ትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሃገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው፡፡ የትምህርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ መጣል ከጀመረ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በፊት ትምህርት የሚሰጠው በመንግስትና በሃይማኖት ተቋማት ዙርያ ለአስተዳደራዊ ክህሎት፣ ለቀኖናና ለሃይማኖት እውቀት ሲባል እንደነበረ እ.ኤ.አ 2004 ላይ ዮኔስኮ የትምህርት ስርዓትን አስመልክቶ ባዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ የወጡ ዘገባዎች ይገልጻሉ፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአፄ ሃይለ ስላሴ ስርዓት ዘመናዊ ትምህርትን በተደራጀ መልኩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ቢሆንም የትምህርት ቤቶች እድገት ከማህበረሰቡም ሆነ ከሃይማኖት ተቋማት በገጠመው ተጽእኖ ምክንያት የመስፋፋቱ እድል አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል የተደረጉ ተከታታይ ጥረቶችም በወቅቱ ከተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስና ድርቅ ጋር ተዳብለው ለአፄው ስርዓት ውድቀት ምክንያት ሊሆን ችሏል፡፡ ለደርግ በወቅቱ የነበረው አጣዳፊ ጉዳይ አብዮቱ በመሆኑ በመማርና ማስተማር ላይ የነበሩትን መምህራንና ተማሪዎች በነቂስ አሰልፎ አብዮቱን ለማስተዋወቅ በሚል ሰበብ ወደ እድገት በሕብረት የዕውቅትና የስራ ዘመቻ አዘመተ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ እራሱን በጥቂቱም ቢሆን ማጎልበት የጀመረው የትምህርት ስርዓት ከባድ ፈተና ውስጥ ወደቀ፡፡ ከየመንግስት መስርያ ቤቱና ተቋማቱ ሁሉም ዓይነት ባለሙያዎች በወረንጦ እየተለቀሙ የማስተማር ሂደቱን በግድ እንዲቀላቀሉ ተደረገ፡፡ እዚህ ላይ የመምህርነትን ሙያ በፍቅር ሳይሆን በተጽእኖ እንዲቀበሉ የተገደዱ ግለሰቦች ምን ዓይነት ትውልድ

Ethiopia Combating Stunting in Children in Aleta-Wondo Woreda town of the Southern Regional State of Ethiopia

Image
BY Mekonnen Teshome Adugna Mitiku had never realized the advantage of giving colostrum to her children within an hour of their birth and also did not exclusively feed her breast in the six months after their birth, contrary to doctors’ advice to help them physically and mentally develope. Adugna (Right) and her daughter Meron embracing her ten-month old son Rather Adugna, a resident in 04 Dela Kebele of the Aleta-Wondo Woreda town of the Southern Regional State of Ethiopia, spilled out the colostrum before feeding breast her daughters as she thought it was something unclean and unpleasant for them to take against the teaching of health professionals. She also gave her babies Hamessa, juice of a “medicinal” plant that usually affects newborn babies’ kidney, with in few hours of their birth thinking that it would make the newly born babies strong and healthy according to the tradition of her society. She also didn’t start complementary food when they get six months old

የጋዜጠኞች መገደል

Image
ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍራ ከተከረቸሙ ዓመታት አልፏቸዋል።ዳ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች እስር ቤቶችን ተመላልሰዉባቸዋል። ዉብሸት ታዬ፥ ርዕዮት ዓለሙ፥ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ዛሬም በየወሕኒ ቤቱ ይማቅቋሉ። 19 12 12 የተገባደደዉ የጎርጎሮሳዉያኑ ዓመት 2012 ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ጋዜጠኞች የተገደሉበት፥ በርካቶች የታሠሩ ወይም የተንገላቱበት ዓመት እንደሆነ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች አስታወቁ።ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅትና ሌሎች ተቋማት እንዳስታወቁት የግብፅ ሕዝባዊ አብዮት፥ የሶሪያዉ ጦርነት፥ የሶማሊያ ግጭት ለበርካታ ጋዜጠኞች ሞት ምክንያት ሆኗል።እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ከ1995 ወዲሕ በአንድ ዓመት ዉስጥ በርካታ ጋዜጠኞች ሲገደሉ ዘንድሮዉ ከፍተኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ። «ሶሪያ ዉስጥ ጋዜጠኛ መሆን ፈንጂ በፈሰሰበት ምድር እንደመራመድ ነዉ።ብዙ የማይነኩ ነገሮች አሉ።አንዳዶቹ ለምሳሌ ፖለቲካዊ፥የሰብአዊ መብቶች ወይም የሥርዓቱ ባሕሪያት የመሳሰሉት ርዕሶች በግልፅ ይታወቃሉ።ሌሎች ደግሞ ቀይ መስመራቸዉ የማይታወቅ ግን አይነኬ ብዙ ጉዳዮች አሉ።እና ፈንጂዉን መቼ እንደምትረገጠዉ፥መቼ እንደሚፈነዳም የሚያዉቅ የለም» ብሎ ነበር። ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ ማዘን ዳርዊሽ፥-ሐቻምና መጋቢት። ዳርዊሽ ፈንጂዉን እንዴት እንደረገጠዉ በርግጥ የሚያዉቅ የለም።ብቻ ፈነዳ። ግን አልገደለዉም። ካልታወቀ ስፍራ-አሳሰረዉ እንጂ።ዳርዊሽ የዘንድሮዉን የድንበር የለሽ ዘጋቢዎችን ሽልማትን አግኝቷል። ሕይወትን ለሙያ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች እንደሚለዉ ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍ

የጊዳቦ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት 47 ነጥብ 80 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ

Image
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2005(ዋኢማ) -  በኦሮሚያና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በመገንባት ላይ ያለው የጊዳቦ የመስኖ ልማት ግድብ ፕሮጀክት 47 ነጥብ 80 በመቶ መጠናቀቁን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ በዘንድሮው የበጀት ዓመትም የጊዳቦን የመስኖ ልማት ግድብ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ታቅዷል። የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት በ303 ሚሊየን 386 ሺ ብር በ2002 ዓ.ም ጥር ወር ላይ ግንባታው የተጀመረ መሆኑን ገልፀው፤ በዘንድሮው የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ብዙነህ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ለማጠናቀቅም በዘንድሮው የበጀት አመት 95 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የቁፋሮ፣ የግድብ አፈር ሙሌት፣ ቁፋሮ፣ የኮንክሪት ስራና የውሃ ማውጫ ግንባታ ቁፋሮና ኮንክሪት ሙሌት ስራዎችን ለማጠናቀቅ ታቅዷል ብለዋል። ግድቡ 20 ነጥብ 80 ሜትር ከፍታ የሚኖረው ሲሆን ርዝመቱም 269 ሜትር እንደሚኖረው ጠቁመው፤ ግድቡ ሲጠናቀቅም  117 ነጥብ 82 ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የማጠራቀም አቅም እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም 7 ሺ 374 ሄክታር መሬትን በመስኖ ሊያለማ የሚችል ሲሆን፤ በዚህም 79 ሺ 820 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል አቶ ብዙነህ ገልፀዋል። የግንባታ ማሽነሪዎች አቅርቦት አናሳ በመሆኑና የአካባቢው የክረምት ወቅት መርዘምን ተከትሎ በተፈለገው ፍጥነት ለመስራት አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በሚፈለገው መጠን ፕሮጀክቱ እየሄደ አለመሆኑን ጠቁመው፤  ችግሩን በመፍታት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆ

መገናኛ ብዙኃን ምርጫውን በትክክል በመዘገብ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

Image
ፕሮፌሰር መርጋ በቃና፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በ 2005  ዓ . ም የሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫን ትክክለኛ ገጽታ በመዘገብ አገራዊ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተገለጸ። በምርጫ ሕጎች አሠራሮችና በምርጫ አዘጋገብ ላይ ለመገናኛ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ ሥልጠና ትናንት ሲጀመር የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደተናገሩት፤ ባለሙያዎቹ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለዜጎች በማድረስ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል። እንደ ፕሮፌሰር መርጋ ገለፃ፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በምርጫው ወቅት ለሕዝቡ ከወገንተኝነት የፀዳ መረጃ ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች በሕገ መንግሥቱ የተጎናፀፉትን የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዲጠቀሙ ማነሳሳት አለባቸው። በመሆኑም ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከምርጫ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እንዲያገኙ መደረጋቸው ይህን ከግቡ ለማድረስ እንደሚያስችል ፕሮፌሰሩ አመልክተዋል። የሥልጠናው ዓላማ ጋዜጠኛው በምርጫው ላይ ያለው የአዘጋገብ ክህሎትን የሚያስጨበጥ እንደሆነ አመልክተው፤ እንዲሁም ልምዳቸውን የሚለዋወጡበት መድረክ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ፓርቲዎችም ሆነ የግል ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት መተባበርና መቻቻል እንዲኖራቸው፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴውን ሳያውኩ በሥነ ምግባር ሕጉ መሠረት እንዲያካሂዱ የማድረግ አገራዊ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የሥልጠናው ተሣታፊዎች የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የየክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያዎች እንዲሁም የጋዜጠኞች ማኅበራት ተወ