Posts

የጊዳቦ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት 47 ነጥብ 80 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ

Image
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2005(ዋኢማ) -  በኦሮሚያና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በመገንባት ላይ ያለው የጊዳቦ የመስኖ ልማት ግድብ ፕሮጀክት 47 ነጥብ 80 በመቶ መጠናቀቁን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ በዘንድሮው የበጀት ዓመትም የጊዳቦን የመስኖ ልማት ግድብ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ታቅዷል። የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት በ303 ሚሊየን 386 ሺ ብር በ2002 ዓ.ም ጥር ወር ላይ ግንባታው የተጀመረ መሆኑን ገልፀው፤ በዘንድሮው የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ብዙነህ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ለማጠናቀቅም በዘንድሮው የበጀት አመት 95 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የቁፋሮ፣ የግድብ አፈር ሙሌት፣ ቁፋሮ፣ የኮንክሪት ስራና የውሃ ማውጫ ግንባታ ቁፋሮና ኮንክሪት ሙሌት ስራዎችን ለማጠናቀቅ ታቅዷል ብለዋል። ግድቡ 20 ነጥብ 80 ሜትር ከፍታ የሚኖረው ሲሆን ርዝመቱም 269 ሜትር እንደሚኖረው ጠቁመው፤ ግድቡ ሲጠናቀቅም  117 ነጥብ 82 ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የማጠራቀም አቅም እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም 7 ሺ 374 ሄክታር መሬትን በመስኖ ሊያለማ የሚችል ሲሆን፤ በዚህም 79 ሺ 820 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል አቶ ብዙነህ ገልፀዋል። የግንባታ ማሽነሪዎች አቅርቦት አናሳ በመሆኑና የአካባቢው የክረምት ወቅት መርዘምን ተከትሎ በተፈለገው ፍጥነት ለመስራት አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በሚፈለገው መጠን ፕሮጀክቱ እየሄደ አለመሆኑን ጠቁመው፤  ችግሩን በመፍታት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆ

መገናኛ ብዙኃን ምርጫውን በትክክል በመዘገብ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

Image
ፕሮፌሰር መርጋ በቃና፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በ 2005  ዓ . ም የሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫን ትክክለኛ ገጽታ በመዘገብ አገራዊ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተገለጸ። በምርጫ ሕጎች አሠራሮችና በምርጫ አዘጋገብ ላይ ለመገናኛ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ ሥልጠና ትናንት ሲጀመር የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንደተናገሩት፤ ባለሙያዎቹ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለዜጎች በማድረስ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል። እንደ ፕሮፌሰር መርጋ ገለፃ፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በምርጫው ወቅት ለሕዝቡ ከወገንተኝነት የፀዳ መረጃ ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች በሕገ መንግሥቱ የተጎናፀፉትን የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዲጠቀሙ ማነሳሳት አለባቸው። በመሆኑም ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከምርጫ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና እንዲያገኙ መደረጋቸው ይህን ከግቡ ለማድረስ እንደሚያስችል ፕሮፌሰሩ አመልክተዋል። የሥልጠናው ዓላማ ጋዜጠኛው በምርጫው ላይ ያለው የአዘጋገብ ክህሎትን የሚያስጨበጥ እንደሆነ አመልክተው፤ እንዲሁም ልምዳቸውን የሚለዋወጡበት መድረክ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ፓርቲዎችም ሆነ የግል ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት መተባበርና መቻቻል እንዲኖራቸው፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴውን ሳያውኩ በሥነ ምግባር ሕጉ መሠረት እንዲያካሂዱ የማድረግ አገራዊ ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የሥልጠናው ተሣታፊዎች የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የየክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያዎች እንዲሁም የጋዜጠኞች ማኅበራት ተወ

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የመንግሥት ፕሮጀክት ግዥዎችን እመረምራለሁ አለ

Image
-    ስዊስ ባንክ በታምራት ላይኔ ስም የተቀመጠ ስምንት ሚሊዮን ዶላር መለሰ በውድነህ ዘነበ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ግዙፍ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ከሚያካሂዷቸው ግዥዎች ጋር በተያያዘ የሙስና ሥጋት በመፈጠሩ፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ እጀምራለሁ አለ፡፡ ኮሚሽኑ ምርመራ ከሚያካሂድባቸው ፕሮጀክቶች መካከል በስኳር ኮርፖሬሽን አማካይነት የሚካሄዱ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሚካሄዱ ትላልቅ የኃይል ማመንጫ ግድቦችና ጣቢያዎች ግንባታና በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሚካሄዱ ትላልቅ የኢንጂነሪንግ ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ በትላልቅ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ እንዲያተኩር መመርያ ተሰጥቶታል፡፡ “ቀደም ሲል ከምናካሂደው በተለየ ሁኔታ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ግዥ ላይ እናተኩራለን፤” ሲሉ አቶ ዓሊ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ በመቶ ቢሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ በርካታ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ መሰማራቱ ይታወቃል፡፡ በእነዚህ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀ ያለው የፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ለምርመራው ያለውን የሰው ኃይል እንደሚያሰማራ ተገልጿል፡፡ ጥቃቅን የሙስና ወንጀሎችን እንጂ ታላላቅ ሙስናዎች አይደፍርም በሚል የሚታማው ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ዘግይቶም ቢሆን በእነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ ለመጀመር መዘጋጀቱ መልካም ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሽግግሩ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ከነበሩት አቶ ታምራት ላይኔና የመከላከያ ሚኒስትር ከነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ ወዲህ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በሙስና ባለመጠየ

የስኳር ህመም መንስኤና ጥንቃቄ

Image
የዓለም የጤና ድርጅት የስኳር ህመም ቆሽት የተሰኘዉ የዉስጥ አካል ኢንሱሊን የተባለዉን ተፈላጊ ቅመም በበቂ ማምረት ሲሳነዉ ወይም፤ ቆሽት ያመረተዉን ኢንሱሊን ሰዉነት በአግባቡ መጠቀም ሲያቅተዉ ሊከሰት እንደሚችል ያመለክታል።  እንዲህ ያለዉ እክል ሰዉነትን ሲያጋጥም ደግሞ ደም ዉስጥ በርከት ያለ የስኳር ፈሳሽ/ግሉኮስ/ ይከማቻል። ይህ የመጀመሪያዉ ዓይነት የስኳር ህመም ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ዓይነት ደግሞ፤ በተመሳሳይ ሰዉነት ተገቢ ያልሆነ የኢንሱሊን አጠቃቀም ሲኖረዉ የሚከሰት ሆኖ፤ መጠን ያጣ ክብደት ሲኖርና በአግባቡ የሰዉነት እንቅንቃሴ ባለመደረጉ እንደሚከሰት መረጃዉ ያብራራል። የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማኅበር ፕሬዝደንትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ሃኪም ቤት በተለይ የስኳር ህመምን የሚከታተሉት ባለሙያ ዲክተር አህመድ ረጃ ይህ የጤና እክል የእድሜ ዘመን ህመም መሆኑን ያመለክታሉ።   የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየጨመረ እንደሚገኝ ጥናቶች እያመለከቱ ነዉ። እንዲያም ሆኖ ጥናቱ እንደሚለዉ የህመሙ ተጠቂ ከሆኑ ግማሽ ያህሉ ገና ተገቢዉን ምርመራ አላደረጉም። የሰዉነት ክብደትን መቆጣጠር ከአንድ ዓመት በፊት 366 ሚሊዮን የነበረዉ በዓለማችን የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 371 ሚሊዮን መድረሱን በቅርቡ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ዓለም ዓቀፍ የስኳር ህመም ፌዴሬሽን እንደሚለዉም ከሆነም በጎርጎሮሳዊዉ 2030ዓ,ም ቁጥሩ ወደ552 ሚሊዮን ማሻቀቡ አይቀርም። ቻይና ዉስጥ ብቻ 92,3 ሚሊዮን ህዝብ ለዚህ የጤና ችግር ሲጋለጥ የጤና አገልግሎቱ ባልተስፋፋበት በአፍሪቃም እንዲሁ ቁጥሩ ሊበረክት እንደሚችል ይገመታል። ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ የስኳር ህመም መንስኤና ጥንቃቄ  

33 የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫ ስም ገንዘብ ማባከን እንዲቆም ጠየቁ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ በጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሄቴል በዚህ አመት በሚደረገው የአካባቢ እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ ምርጫ የግዜ ሰሌዳን አስመልክቶ  የውይይት መድረክ መጥራቱን ጠቅሰዋል። ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ” ምርጫ ለማካሄድ ነባራዊ ሁኔታው የማይፈቅድ ስለሆነ በፖለቲካ ምህዳሩና በህዝብ ወሳኝነት ሁሪያ መወያየት አለብን ብለን ፒቲሺን ተፈራርመን ለቦርዱ ያስገባን 33 ፓርቲዎች ጉዳይ ወደ ጎን ተትቶ ቀልድ በሚመስል መልክ በጾታ ጉዳይ ልናወያያችሁ እንፈልጋለን ማለት የህዝብን የምርጫ ባለቤትነት የሚጋፋ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል።” ካሉ በሁዋላ፣ ቦርዱ ጾታን በተመለከተ እና አሁን ላለንበት ሁኔታ ቀላል የሆነ ጉዳይ ጠቅሶ በጠራው የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት  መድረክ የማንሳተፍ መሆናችንን ፔቲሺን የፈረምን 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች እናሳውቃለን።” ብለዋል። 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርቻ ቦርድ በገለልለተኛ ወገኖች እንዲቋቋም፣ ነጻና ፍትሀዊ የመገናኛ ብዙሀን እንዲኖሩ፣ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሁሉንም ድርጅቶች በእኩል እንዲያገለግሉ፣ መከላከያ፣ ፖሊስና የደህንነት ተቋማት በነነጻነት እንዲዋቀሩ፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማዋከብ እንዲቆም የሚሉና ሌሎችንም በርካታ ጥያቄዎች መጠየቃቸው ይታወሳል።