የነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ
አዋሳ ታሀሳሰ 03/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከዩኒቨርስቲ ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው አለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን ትናንት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ ቀኑን አስመልክቶ በዩኒቨስርቲው በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለፀው በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃቶችን ማሰቆም ሰብአዊ መብቶች በማስተባበር ልማትና እድገትን ለማፋጠን ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲው ሶስቱም ካምፓስ መምህራን፣ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በውይይቱ መጨረሻ በተቋሙ ውስጥም ሆነ ውጭ በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ማንኛውንም ጥቃት እና ትንኮሳዎችን ለመከላከል ግንዛቤ በመፍጠር የበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የሃይል ጥቃቶች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመሆናቸው ከተለያዩ ማህበራት፣ መንግስታዊ ከሆነ ተቋማትና ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመግታት ግንባር ቀደም ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በዛ ነገዎ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ባሻገር የሴቶችን አኩልነት ፣ የሃይማኖት ነፃነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ሁሉም ተገንዝቦ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ኮሚሽነር አቶ አስማሩ በሪሁን በበኩላቸው ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳዎች ሴቶች ለሀገር ልማትና እድገት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ የሚገድብ፣ በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያቀጭጭ፣ የሀገሪቱ የ