Posts

በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል: ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል

9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 25/2005 ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። በ8ኛው ሳምንት መርሀ ግብር በሜዳው በሀዋሳ ከነማ ሽንፈት የደረሰበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ህዳር 25/2005 ሀረር ላይ ከሀረር ቢራ አንድ አቻ በመለያየት ተመልሷል፡፡ባለ ሜዳዎቹ ሀረር ቢራዎች አሸናፊ አደም ባስቆጠራት ግብ ለበርካታ ደቂቃዎች መርተዋል። የደረጃ ሰንጠረዡ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ ያገኘበትን የአቻነት ግብ ኡመድ ኡኩሪ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ 5 ነጥቦችን የጣለው ቅዱስጊዮጊስ ህዳር 26/2005 ሀዋሳ ከነማ የሚያሸንፍ ከሆነ የደረጃ መሪነቱን ይነጠቃል፡፡ደደቢትም በተሻለ ግብ ልዩነት ድል ከቀናው ከቅዱስ ጊዮርጊስ በላይ መቀመጥ ይችላል፡፡ የህዳር 25/2005 መርሀ ግብር የሆነው ሌላው በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያና የኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ፍልሚያ ነበር፡፡መከላከያ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ ማለት ችሏል፡፡ኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ግን ከዘጠኝ ጨዋታዎች በምንም ማሸነፍ ተስኖታል፡፡ያለው ብቸኛ ነጥብ ከሙገር ሲሚንቶ ጋር አንድ አቻ የተለያዩበት ሲሆን በርካታ የግብ ክፍያዎችን ይዞ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ህዳር 25/2005 የ9ኛው ሳምንት ቀሪ አምስት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል፡፡ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል፡፡ደደቢት በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ውጤት ከራቀው አዳማ ከነማ ይገናኛል፡፡እዚህ አዲስ አበባ ስታድየም

3ቱ የኑሮ ችግሮች

የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች የተመራቂዎች ሥራ አጥነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመራቂዎች ሥራ አጥ ሆነዋል፤ በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ይመረቃሉ። የኑሮ ውድነት ሸክም የዋጋ ንረት በአስር አመት በአምስት እጥፍ ጨምሯል። የደሞዝተኛ ሰራተኞች የኑሮ ደረጃ ደግሞ በግማሽ አሽቆልቁሏል። የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች በገበያ እጦትና በመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ ከስረዋል፤ የተበደሩትን ሳይመልሱ ጠፍተዋል በመጪው ግንቦት የሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ይከብዳል። በዚያው ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚከናወኑት የወረዳና የቀበሌ ምርጫዎች፤ ከሞላ ጎደል ኢህአዴግና አጋሮቹ በዘጠና ምናምን ፐርሰንት እንደሚያሸንፉ አያጠራጥርም። የአዲስ አበባውም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ግን ላይሆንም ይችላል። የሆነ ሆኖ፤ ከምርጫው ጋር ተያይዞ፤ ለረዥም ጊዜ ጠፍቶ የነበረው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ ሰሞኑን ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል። የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውዝግብም ሞቅ ሞቅ ማለቱ አይቀርም - ፉክክር መሆኑ ነው። ግን ምን ዋጋ አለው? ፉክክራቸውና ውዝግባቸው ሁሉ ያን ያህልም ከዜጎች ተጨባጭ የኑሮ ችግር ጋር ግንኙነት የለውም። የምርጫ ንትርክና ውዝግብ ለግለሰብ ነፃነት የተሻለ ክብር እየሰጡ፣ በስልጣኔ ጎዳና ደህና የተራመዱ አገራት ውስጥ የምናየው ፉክክር ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናየው ውዝግብ በእጅጉ ይለያል። የአሜሪካና የእንግሊዝ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ወቅት የሚያነሷቸው አጀንዳዎች፣ ከዜጎች ኑሮ ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። በዜጎች ኑሮና ፍላጎት ዙሪያ እየተከራከሩ፣ በዜጎች ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ እየተፎካከሩ የምርጫ ውድድር ያካሂዳ

በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ በሁለተኛው ዙር የመሬት ልኬት ከ5 መቶ በላይ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ሰርተፊኬት ለጊዲቦ ቀበሌ አርሶ አደሮች አዘጋጅቶ መስጠቱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ገለፀ

በወረዳው ጊዲቦ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑ አባወራና እማወራ አርሶ አደሮች ለሁለተኛ ዙር የመሬት ልኬት ካርታና ሰርተፍኬት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ሳሙኤል ባሰሙት ንግግር አርሶ አደሩ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ሰርቲፍኬት ማግኘቱ በመሬቱ የባለቤትነት መብት ተሰምቶት ልማቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችላል፡፡ የወረዳው ግብርና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በርናባስ ሮማ በበኩላቸው መንግስት የአርሶ አደሩን የመሬት ይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ መሬቱን አልምቶ የምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል  አርሶ አደር ብሩ ሙፋቶሃና ሴት አርሶ አደር አማረች ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት የይዞታ ማረጋገጨ ካርታና ሰርቲፍኬት መስጠቱን በንብረታቸው ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም ሌላ ሁሉንም ፆታዎች በእኩል ደረጃ የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረጉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/23HidTextN205.html

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በክልል ደረጃ ሲዳማ ዞን በይርጋዓለም ከተማ በድምቀት ተከበረ

Image
ሃዋሳ ህዳር 25/2005 ህገ መንግስቱ የፈጠራቸው መልካም ሁኔታዎችን በመጠቀም የተጀመረውን የጸረ ድህነት ዘመቻ በማጠናከር የመለስን ራዕይ እውን ለማድረግ የክልሉ ህዝብ በጋራ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት የደቡብ ክልል ምክር አፈ ጉባዔ አስገነዘቡ፡፡ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በክልል ደረጃ ሲዳማ ዞን በይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትናንት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡ አፈጉባዔ ወይዘሮ ገነት ወልዴ ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ህገ መንግስቱ የፈጠራቸውን ምቹና መልካም ሁኔታዎችን በመጠቀም ድህነትን ለማስወገድና የመልካም አስተዳደር ለማስፈን በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተቀየሱ የልማት ራዕዮችን እውን ለማድረግ ሁሉም በጋራ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል፡፡ ህዳር 29 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በልዩነታቸው ውበትን፣ በውበታቸው አንድነትን የመሰረቱበት ብቻ ሳይሆን ባህል፣ ወግ፣ ልማዳቸውንና ቱውፊታቸውን ያደሱበት ልዩና ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል፡፡ የክልሉ ህዝብ በህገ መንግስቱ የተጎናጸፈውን ራስን በራስ የማሰተዳደር ነፃነት በመጠቀም ባለፉት 21 ዓመታት በርካታ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ድሎችን ሊያስመገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሃንዲስነት የተዘረጉትን የልማት መስመሮችንና መልካም ፖሊሲዎችን በማስቀጠል ድህነትን ታሪክ አድርጎ ለማለፍ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች መደረጋቸውን ጠቁመው በመስኩ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡ ወይዘሮ ገነት በማያያዝም በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ዘላቂና ቀጣይነት ያለውን ልማት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ ለተያዘው ዕቅድ መሳካት አመራሩ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብተሰብ ክፍሎች በየተ

Unity over Rights Pave Ethiopian Oppositions’ Future

Image
It takes two to tango. EPRDF’s talk about democracy appears to deal more with the image of democracy than with its reality. The oppositions’ talk about democracy seems to be targeted more at assuming power by whatever means than at providing a unified alternative for the people to choose from. That is the drama of democracy played everyday inEthiopia. The vital question, however, is; how can the drama be abandoned and reality be adopted? Standing at the fore of the stage is the Ethiopian opposition. How the drama would be played out would also be highly dependent on their move. The political climate on the ground is squeezing the opposition with each passing day. To make things worse, the opposition itself is weak due to divisions. Forgoing its purpose, it settles for mere opposition. The opposition has to go through rebirth. Otherwise, it will soon become a do-nothing force as far as peaceful struggle is concerned. Even then, the opposition is not at the mercy