3ቱ የኑሮ ችግሮች
የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች የተመራቂዎች ሥራ አጥነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመራቂዎች ሥራ አጥ ሆነዋል፤ በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ይመረቃሉ። የኑሮ ውድነት ሸክም የዋጋ ንረት በአስር አመት በአምስት እጥፍ ጨምሯል። የደሞዝተኛ ሰራተኞች የኑሮ ደረጃ ደግሞ በግማሽ አሽቆልቁሏል። የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች በገበያ እጦትና በመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ ከስረዋል፤ የተበደሩትን ሳይመልሱ ጠፍተዋል በመጪው ግንቦት የሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ይከብዳል። በዚያው ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚከናወኑት የወረዳና የቀበሌ ምርጫዎች፤ ከሞላ ጎደል ኢህአዴግና አጋሮቹ በዘጠና ምናምን ፐርሰንት እንደሚያሸንፉ አያጠራጥርም። የአዲስ አበባውም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ግን ላይሆንም ይችላል። የሆነ ሆኖ፤ ከምርጫው ጋር ተያይዞ፤ ለረዥም ጊዜ ጠፍቶ የነበረው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምፅ ሰሞኑን ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል። የገዢው ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውዝግብም ሞቅ ሞቅ ማለቱ አይቀርም - ፉክክር መሆኑ ነው። ግን ምን ዋጋ አለው? ፉክክራቸውና ውዝግባቸው ሁሉ ያን ያህልም ከዜጎች ተጨባጭ የኑሮ ችግር ጋር ግንኙነት የለውም። የምርጫ ንትርክና ውዝግብ ለግለሰብ ነፃነት የተሻለ ክብር እየሰጡ፣ በስልጣኔ ጎዳና ደህና የተራመዱ አገራት ውስጥ የምናየው ፉክክር ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናየው ውዝግብ በእጅጉ ይለያል። የአሜሪካና የእንግሊዝ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በምርጫ ወቅት የሚያነሷቸው አጀንዳዎች፣ ከዜጎች ኑሮ ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው። በዜጎች ኑሮና ፍላጎት ዙሪያ እየተከራከሩ፣ በዜጎች ችግርና በመፍትሄ ሃሳቦች ላይ እየተፎካከሩ የምርጫ ውድድር ያካሂዳ