የማይዝል ክንድ
በምሕረት አስቻለው ጥቂት የማይባሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች የቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መገኘት በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የመሥራት አቅማቸው፣ ወይም ሌሎች የዕለት ተዕለት ክንዋኔአቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይሰማቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አብረዋቸው የሚሠሩ በዙርያቸው ያሉ ስለ እነዚህ ሰዎች ኤችአይቪ ፖዘቲቭ መሆንና የመሥራት አቅምና ተመሳሳይ አመለካከት ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል፡፡ እያንዳንዷን ቀን መርካቶ ጭድ ተራ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ላይ ለሚያሳልፈው ወጣት የቀን ሠራተኛ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ነገር ግን የሥነ ልቦና ጥንካሬ ያለው ሰው ጉልበት ፈታኝ በሆነው የቀን ሥራ ላይ ቢሰማራ ምንም የሚገርም ነገር እንደሌለው ይናገራል፡፡ ባደረገው የኤችአይቪ ምርመራ የቫይረሱን በደሙ ውስጥ መገኘት ካወቀ አራት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የመጀመርያዎቹን ሁለት ዓመታት ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መውሰድ አላስፈለገውም ነበር፡፡ አራቱንም ዓመታት ግን የጉልበት ሥራ ሠርቷል፡፡ የትውልድ ቀዬው ቂጨሞን ጥሎ እንደ ብዙዎቹ የቀዬው ወጣቶች ሠርቶ ለመለወጥ ወደ አዲስ አበባ የመጣው ከአሥር ዓመታት በፊት የ18 ዓመት ወጣት እያለ ነበር፡፡ የሆቴል መስተንግዶ፣ ጀብሎን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ እዚህም እዚያም እያለ የጉልበት ሥራ እየሠራ ኑሮውን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል በነበረበት ወቅት ከተዋወቃት ጓደኛው ጋር በትዳር ተሳስሮ አንድ ልጅ ማፍራት ችሏል፡፡ ለወጣቱ በምን አጋጣሚ የኤችአይቪ ምርመራ እንዳደረገ ጥያቄ አቅርበንለት ነበር፡፡ ከጓደኛው ጋር በጋብቻ ተሳስረው መኖር እንደጀመሩ ሳንባ መታመም ጀመረ፡፡ ይኖሩ የነበረው የባለቤቱ አክስት የሚያከራዩት አንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡ ሕመሙን የተመለከቱት አክስቷ በግልጽ ኤችአይቪ መሆኑን