የነፃ ገበያ ውድድሩ ወዴት?
በዳዊት ታዬ የዜጎችን የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ አተገባበር ሲያወያይ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡ ማወያየት ብቻ ሳይሆን ብዙ ውዥንብር መፍጠሩንም ከሁለት ሳምንታት በፊት በየቀበሌው ደጃፍ የተመለከትነው ግርግር ይመሰክራል፡፡ የ40/60 የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን የነበረው ጉጉት ከልክ በላይ መሆኑንም የምንረዳበት ነው፡፡ የ40/60 የቤቶች ፕሮጀክት አተገባበር አሁንም ድረስ ብዥታ እንደፈጠረ ነው፡፡ ከዛሬ ነገ ምዝገባው ይጀመራል እየተባለ አሁንም ድረስ እየተጠበቀ ቢሆንም ነገሩ በእንጥልጥል ላይ ቀርቷል፡፡ ምዝገባው ለምን አልተጀመረም? ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ አልተገኘም፡፡ ሌሎች ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችም እስካሁን ጥርት ብለው አልተገለጹም፡፡ በ40/60 የመኖርያ ቤቶች ፕሮጀክት እየተስተዋለ ያለው ሽፍንፍን ያለ አካሄድ እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱን መሬት ላይ ለማውረድ ቤት ፈላጊው እንዲያሟላ የሚጠበቅበት የ40 በመቶ የቅድሚያ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በሚካሄድ ቁጠባ ስለመሆኑ ግን ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የግንባታ ወጪውን ከባንክ ጋር አስተሳስሮ ግንባታውን ለማከናወን መቻሉ የሚደገፍ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራር እስካሁንም መዘግየት አልነበረበትም፡፡ ሆኖም የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለመገንባት ወይም አሁን እንደታሰበው በ40/60 የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ከባንክ ጋር በማስተሳሰር የሚሠራውን ሥራ ለአንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መስጠቱ እንደ ትክክለኛ ዕርምጃ ሊወስድ ግን አይችልም፡፡ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ያሉትን የመኖርያ ቤት ፈላጊዎችን ትተን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ብቻ ወደ በሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የራሳቸው