Posts

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት ጀምሮ በድምቀት አየተከበረ ነው

Image
ሃዋሳ ህዳር 22/2005 ህገ መንግሰቱ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የተጀመረውን የፀረ ድህነት ዘመቻና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራዕይ ከዳር ለማድረስ ህብረተሰቡ በጋራ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት አስገነዘቡ ። ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ከትናንት ጀምሮ በተለያየ ዝግጅት በድምቀት እየተከበረ ነው ። ፕሬዚዳንቱ ዶክተር ዮሰፍ ማሞ በአሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የፓናል ውይይት ሲከፍቱ እንደተናገሩት ህገ መንግስቱ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ድህነትን ለማስወገድና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተቀየሱ የልማት ራዕዮችን ለማሳካት ሁሉም በጋራ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል። የክልሉ ህዝብና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በህገ መንግሰቱ የተጎናፀፈውን ራስን በራስ የማስተዳደር ነፃነት በመጠቀም ባለፉት ሃያ አንድ አመታት በርካታ የልማት ድሎችን ሊያስመዘግብ መቻሉን አስታዉቀዋል ። በሀገሪቱ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ልማት በማስመዝገብ ድህነት ለማስወገድ ለተያዘው እቅድ መሳካት ሁሉም በየተሰማራበት ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። በአሉ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ሲያነሱት የነበረው የነፃነትና የእኩልነት መብት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ዕለት በመሆኑ በአሉ ለዘላለም ሲዘከር ይኖራል ብለዋል ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ አቶ መሃመድ ረሽድ በበኩላቸዉ በሀገሪቱ ሁሉም አከባቢ እየተካሄዱ ያሉትን የልማት ጅምሮች በማፋጠን ዋንኛ ጠላት የሆነውን ድህነት ድል ለመንሳት የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀር ላይ የመሰረቱትን አንድነታቸውን በማጠናከር ባለፉት አመታት በድህነት ላይ በጋራ በከፈቱት ዘመቻ በ

በሀዋሳ ከተማ ከ210 ሚልዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ስራዎች እየተካሄዱ ናቸዉ -በከተሞች ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የምስክር ወረቀት ተሰጠ

Image
አዋሳ ህዳር 21/2005 በሀዋሳ ከተማ ከ210 ሚልዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ግንባታ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የከተማው አስተዳደር ገለጸ፡፡ በአራተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ላስመዘገበችው አመርቂ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ድርጅቶች፣ ማህበራትና ግለሰቦች ትናንት ምሽት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በዚሁ የምስጋና ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት ከተማዋን ለነዋሪው ምቹ፣ የኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በርካታ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸዉ ። ሀዋሳ ውብ፣ ጽዱና አረንጓዴ፣ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ገጽታዋ የጎላ እንዲሆን የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል ። በከተማ አስተዳደር፣ በማዘጋጃ ቤት የውስጥ ገቢ፣ በመንግስት መደበኛ በጀትና ከአጋር ድርጅቶች በተመደበው 210 ሚልዮን ብር ወጪ እየተካሄዱ ያሉት 10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ፣ ከ45 ኪሎ ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ የጠጠርና የኮብል ስቶን ንጣፍ ናቸዉ ። በተጨማሪ የባህል ማዕከል፣ ዘመናዊ የመንገድ ላይ መብራትና የውሃ መስመር ዝርጋታዎች፣ እንዲሁም ዘመናዊ ቄራ ግንባታ በዋናነት እንደሚገኙበት አቶ ዮናስ ተናግረዋል፡፡ ከመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውስጥ እስከ አሁን አብዛኛዎቹ ከ50 በመቶ በላይ መከናወናቸዉንና በጀት ዓመቱ ከፍፃሜ ለማድረስ ጥረት ከወዲሁ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታገሰ ጫፎ ለተቋማቱ፣ ድርጅቶችና ማህበራት ሰርተፍኬት ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት በአመራሩና ከተማ ነዋሪዎች የጋራ ጥረት የተመዘገበ ውጤት በ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአምስት ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

Image
አዲስ አበባ ህዳር 20/2005 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስት የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት የሥራ ኃላፊዎች ሹመትን አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው የ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የንግድ ሚኒስትርና የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል። በዘህም መሰረት አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር፣ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን መገናኛና ሚኒስትር በመሆን ተሹመዋል። ይህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲኖሯት ያስቻለ ሹመት ሆኗል፡፡ እንዲሁም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የንግድ ተጠባባቂ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ከበደ ጫኔ የንግድ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በፖለቲካ አመራር ብቃታቸውና ባላቸው የስራ ልምድ ለኃላፊነቱ የተመረጡ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አሁን የተካሄደው ሹመት የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ለማጠናከር፣ የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብና የመተካካት ሥርዓቱን ለማጎልበት ነው። ሹመቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን ተሿሚዎቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በአቶ ተገኔ ጌታነህ አማካይነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ በተጨማሪ ምክር በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካካል 4ኛውን የመንገድ ዘር

“ሕዝቡ ከማጉረምረም አልፎ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነ አይመስልም” ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሲዳማም ውስጥ ያለው እውኔታ ይሄው ነው

Image
በኣጠቃለይ በኢትዮጵያ ደረጃ በኣገሪቱ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሉት ከሆነ ህዝቡ በመልካም ኣስተዳደር ይዞታ ላይ ያለውን ቅሬታ ኣውጥቶ  ለመናገር ወነ ያጣ ሲሆን ተመሳሳይ ሁኔታ በሲዳማ ውስጥም በመከሰት ላይ ነው፤ ምናልባት የሲኣን በኣዲስ ኣመራር መዋቀር ህዝቡን ከላነቃቃው በስተቀር ማለት ነው። በኣጠቃላይ ኣገሪቱን በተመለከተ ዝርዝሩን ከታች ያንቡ።  ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር -    ኢሕአዴግ ለሕዝብ ደንታ የለውም አሉ -    ብልሹ የምርጫ ሥርዓት መስፈኑን ወቀሱ በጋዜጣው ሪፖርተር ባለፈው እሑድ ኅዳር 16 ቀን 2005 ዓ.ም. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረገው ውይይት ላይ የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶተኛና በማጉረምረም ደረጃ ላይ የሚገኝ እንጂ፣ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም አሉ፡፡ የአገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በዳሰሱበት ክፍል ላይ በሰጡት ማብራሪያ ሕዝቡ በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዳሉበት ገልጸው፣ ይህንን ሰቆቃውንና ብሶቱን ያማርራል እንጂ በይፋና በአደባባይ አይገልጽም ብለዋል፡፡ “ብሶቱ በማጉረምረም ደረጃ የሚገለጽ ነው እንጂ ወደ ኅብረተሰባዊ ንዴት አልተለወጠም ብለው፣” የተናጠል ንዴቶች አልፎ አልፎ ቢገለጹም ሰፊና የአጠቃላይ ኅብረተሰቡ አለመሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ “እነዚህ የተናጠል ትናንሽ ንዴቶች ወደተደራጀና ሕዝባዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች አልተለወጡም፡፡ በሌሎች አገሮች በዳቦ ወይም በነዳጅ ዋጋ ላይ ትንሽ ጭማሪ ከታየ የኅብረተሰቡ ንዴት ይገነፍላል፡፡ በእኛ ሕዝብ ዘንድ ግን ይህ አይታይም፡፡ ምልክቶች ከታዩ ጥቂ

80 ኪሎ ሜትር መንገድ በዳራ ወረዳ በመገንባት ላይ መሆኑ ተሰማ

Ethiopia: Road Building Accord Addis Ababa — A contract agreement providing for building the roads linking the country's road network with three new sugar factories at a cost of over 3.9 billion birr was signed here yesterday. Similarly, 80-kms road is being constructed in Dara Woreda , Sidama Zone of Southern Nations, Nationalities and Peoples State at a cost of over 40 million birr allocated by the government, the Woreda's Road Transport Office said. Ethiopian Roads Authority Director-General Zayid Wolde-Gebriel and General Manager of China Communications Construction Company (CCCC) Group Zhou Yongsheng and CGC Overseas Acting General Manager Gao Lei. The roads linking Enjibara-Chagni- Pawe, Pawe-Fendiqa Ayma and Kesem Sugar Factory will be upgraded to asphalt concrete level. CCCC will construct the 100-kms Enjibara-Chagni- Pawe road with over 2.2 billion birr. CGC Overseas will also construct the 75-kms Pawe-Fendiqa Ayma road and the 22-kms road leading to Kes