ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈበት
•ፕሪሚየር ሊጉ ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ ይካሄዳል ሲዳማ ቡና እየተካሄደ በሚገኘው የ2005ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ውድድር በአራተኛው ሣምንት ሲዳማ ቡና በሜዳው ይርጋለም ላይ አርባ ምንጭ ከነማን ባስተናገደበት ጨዋታ በተፈጠረው የዲሲፕሊን ጥሰት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተላልፎበታል። ፌዴሬሽኑ ያደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ውድድሩን የሚመራው የሊግ ኮሚቴ ከዲሲፕሊን ኮሚቴ የደረሰውን ሪፖርት ከገመገመ በኋላ ሲዳማ ቡና በስድስተኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ነገ በሜዳው ከሃዋሳ ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጨዋታ በሌላ ገለልተኛ ሜዳ እንዲያካሂድ ወስኖበታል። ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ይርጋለም ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ የቦታና ሰዓት ለውጥ ተደርጎበት በአሰላ ስታዲየም ከቀኑ በስምንት ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ተግባራት የተመልካቾች ማነስ እያሳሰበው ለሚገኘው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫን የበለጠ የሚያደበዝዙት በመሆኑ ክለቦች ደጋፊዎቻቸውንም ሆነ ተጫዋቾቻቸውን ለስፖርታዊ ጨዋነት መርሆዎች ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የስድስተኛው ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ ሰባት ጨዋታዎችም ይከናወናሉ። አምስቱ ጨዋታዎች ነገ በአበበ ቢቂላና በክልል ከተሞች የሚደረጉ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። በእዚሁ መሠረት ነገ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ትኩረት ስቧል። ሁለቱ ክለቦች በደረጃ ሠንጠረዡ በአንድ ነጥብ ተበላልጠው ስምንተኛና ዘጠንኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ መከላከያ በሰባት ነጥብ ስምንተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና