Posts

ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈበት

Image
•ፕሪሚየር ሊጉ ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ ይካሄዳል ሲዳማ ቡና እየተካሄደ በሚገኘው የ2005ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ውድድር በአራተኛው ሣምንት ሲዳማ ቡና በሜዳው ይርጋለም ላይ አርባ ምንጭ ከነማን ባስተናገደበት ጨዋታ በተፈጠረው የዲሲፕሊን ጥሰት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተላልፎበታል። ፌዴሬሽኑ ያደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ውድድሩን የሚመራው የሊግ ኮሚቴ ከዲሲፕሊን ኮሚቴ የደረሰውን ሪፖርት ከገመገመ በኋላ ሲዳማ ቡና በስድስተኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ነገ በሜዳው ከሃዋሳ ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጨዋታ በሌላ ገለልተኛ ሜዳ እንዲያካሂድ ወስኖበታል። ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ይርጋለም ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ የቦታና ሰዓት ለውጥ ተደርጎበት በአሰላ ስታዲየም ከቀኑ በስምንት ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ተግባራት የተመልካቾች ማነስ እያሳሰበው ለሚገኘው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫን የበለጠ የሚያደበዝዙት በመሆኑ ክለቦች ደጋፊዎቻቸውንም ሆነ ተጫዋቾቻቸውን ለስፖርታዊ ጨዋነት መርሆዎች ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የስድስተኛው ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ ሰባት ጨዋታዎችም ይከናወናሉ። አምስቱ ጨዋታዎች ነገ በአበበ ቢቂላና በክልል ከተሞች የሚደረጉ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። በእዚሁ መሠረት ነገ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ትኩረት ስቧል። ሁለቱ ክለቦች በደረጃ ሠንጠረዡ በአንድ ነጥብ ተበላልጠው ስምንተኛና ዘጠንኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ መከላከያ በሰባት ነጥብ ስምንተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና

የክልሉ መንግስት በሁሉም አካባቢዎች ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልና የመሠረተ ልማት ዝርጋታን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡

Image
ከአራት የአውሮፖ አገራት ፓርላማዎች የተውጣጡ ልዑካን ቡድን አባላት በክልሉ በአውሮፖ ህብረት ድጋፍ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ውጤታማ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፣ም/ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊና ከክልሉ ምክር ቤት ኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መክረዋል፡፡ ዝርዝሩ የደቡብ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡ በአውሮፖ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የልማት ኘሮጀክቶችን እንስቃሴ ለማየት ከሀንጋሪ፣ ክቼክ ሪፓብሊክ ፣ ከሶሎቫኪያና ከፖላንድ ፓርላማዎች የተወከሉና የልማት ድርጅቶች ተወካዮች ጉብኝት እያደረጉ ናቸው፡፡ የልዑካኑ ቡድን አባላት ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በወቅቱ ርዕሰ መሰተዳድሩ እንዳሉት የክልሉ መንግስት በሁሉም የልማት ዘርፎች የክልሉን አካባቢዎች እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡ ባለፉት አመታት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌያት የህፃናትን ሞትን ለመቀነስ ተችሏል፡፡ ከ6ዐዐ በላይ ጤና ጣቢያዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሠጡ ናቸው፡፡ አርሶ አደሩ በቂ ምርት እንዲያመርትና ራሱን ከመመገብ አልፎ ለገበያ እንዲያቀርብ የተደረገው ጥረት ውጤታማ መሆኑን አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡ በሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የሚያሰችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2ዐዐ5 ዓ/ም 65ዐ ሚሊዮን ብር በመመደብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እየተሠራ ያለውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ በቼክ ሪፓብሊክ ኤምባሲ የልማት ተልዕኮው ምክትል ኃላፊ ሚስስ ጃና ኮርቤሎቫ እንዳሉት በክልሉ የሚደረጉ የልማት ሥራዎች ውጤታማ ናቸው፡፡ እነዚህን በ9 ወረዳዎች በግብርና፣ በትምህርት

የህዳሴ ግድብ በተያለዘት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መወሰናቸውን የወንዶ ገነት ወረዳ የወጣቶችና የሴቶች ሊግ ገለፀ፡፡

የ2ዐዐ4 ዓ/ም የስራ ክንውን በመገምገም በተያዘው የበጀት አመት አበይት የትኩረት አቅጣጫዎችን ለይተው ተቀናጅተው ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ለአንድ ቀን ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ሊግ የጋራ ስብሰባ ባለፈው አመት ባከናወኗቸውና በቀጣይ በሚሰ b ቸው አበይት ስራዎችን ለአባላቱ በማቅረብ ተወያይተውበታል፡፡ በዚህም የወጣቶች ሊግ በተጠናቀቀው አመት በከተማ የስራ አጥነት ችግር በቁጠባ፣ በአካባቢ ፅዳት ስራዎች የበጎ አገልግሎት ላይ ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ በገጠር ወረዳው ያለውን ምቹ የመሰኖ አቅምን  በዘመናዊ መንገድ እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር መቻላቸውን የወረዳው ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሴ ሙዴ ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ የወረዳው ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃለፊ ወይዘሮ ድንቅነሽ ደግፌ እንዳሉት የወረዳው ሴቶች በተለይም የገጠር ሴቶች በሰብልና በእንስሳት ሀብት ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ እንዲሁኑ ስራዎችን በመስራት ምርታማ ለማድረግ ተንቀሳቅሰናል ይላሉ፡፡ የሁለቱ ሊጐች አባላት በተደረገ ውይይትም የ2ዐዐ5 የትኩረት አቅጣጫ ላይ ከመግባበት የደረሱ ሲሆን በጋራ ሆነው የተጀመሩ ስራዎች ቀጥሏል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የህዳሴው ግድብ በተያለዘት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከወጣቶችና ሴቶች ሊግ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መወሰናቸውን አቶ ሙሴ ተናግረዋል፡፡ ሌላው ትልቁተግባራቸውም በቀጣይ በሚከናወነው ማሟያ ምርጫ ላይ እነዚህ አካላት ከዚህ ቀደም ከከነበራቸው ተሳትፎ በላቀ ደረጃ እንደሚሳተፉ ም ተስማሟተዋል፡፡ የወረዳው ዴህዴን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ደበላ በበኩላቸው ሊጐቹ ለወጣቶችና ሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሰብ በቀጣይ ደካማ አፈፃፀማቸውን በማረም ጠንካራ ጎናቸውን በማጠናከር መ

የቡና ምርት መጠንና ጥራትን በማስጠበቅ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ በሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀው የባለ ድርሻ አካላት ግብረ ኃይል ፎረም ስብሰባ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሉት የቡና ግብይት ስርዓቱ ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን ገቢና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

ባለፉት ተከታታይ የምርት ዘመናት በተደረገ ሰፊ እንቅስቃሴ በቡና ምርት ዝግጅት ስራ ላይ የነበሩ ድክመቶችን ለይቶ በማስወገድ ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋልም ብለዋል፡፡ ዘመናዊ የግብይት ስርዓቱን ጤናማ በማድረግ ሀገሪቷ ከዘርፉ የምታገኘው የገቢ እቅድ ለማሳካት ምርቱን በወቅቱ ያለማቅረብና ህገወጥ የቡና ግብይቶች የመሳሰሉ ችግሮች ለማስወገድ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱም አሳስበዋል፡፡ የቡና ግብይ ማዕከላትን በማጠናከር የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥሩ በአስተባባሪ ግብረ ኃይሎች ሊጠናከር ይገባልም ብለዋል፡፡ የንግድ ሚኒስቴር ማኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ እንዳሉተም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተነድፎ ተግባራዊ መሆን ከተጀመረ ወዲህ ሀገሪቷ ከውጭ ምርቶች የሚገኘው ገቢ እያደገ መጥቷል፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጨረሻ ሀገሪቷ ከውጭ ምርቷ የምታገኘው ገቢ 1ዐ ነጥብ አራት ቢሉዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ በያዝነው ዐመት 5 ቢልዮን ዶላር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የቡ ምርቱ መጠንና ጥራት በማሻሻልም ዘንድሮ ከአንድ ነጥብ አነድ ቢልዮን ዶላር በላይ ገቡ እንዲገኝ የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል፡፡ ከአምራቾች እስከ ገበያ ድረስ ያለው የጥራትና የአቅርቦት ችግሮች በማስወገድ በያዝነው የምርት ዘመን 3መቶ 43 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡ በውይይቱ የቡና ምርት መጠንና ጥራት እንዲሁም የግብይት ስርዓቱ እየተሻሻለ ቢመጣም ወደፊት የተሻለ ዋጋ ሊያወጣ ይችላል በሚል ቡናን አከማችቶ ያለመሸጥ ችግር፣ ህገወጥ ግብይት ሙሉ በሙሉ አለመወገድ፣ የመጀመሪያ የቡና ግብይት ማዕከላት አለመጠናከርና፣ የብድር አቅርቦት ችግሮ

Unity over Rights Pave Ethiopian Oppositions’ Future

Image
It takes two to tango. EPRDF’s talk about democracy appears to deal more with the image of democracy than with its reality. The oppositions’ talk about democracy seems to be targeted more at assuming power by whatever means than at providing a unified alternative for the people to choose from. That is the drama of democracy played everyday inEthiopia. The vital question, however, is; how can the drama be abandoned and reality be adopted? Standing at the fore of the stage is the Ethiopian opposition. How the drama would be played out would also be highly dependent on their move. The political climate on the ground is squeezing the opposition with each passing day. To make things worse, the opposition itself is weak due to divisions. Forgoing its purpose, it settles for mere opposition. The opposition has to go through rebirth. Otherwise, it will soon become a do-nothing force as far as peaceful struggle is concerned. Even then, the opposition is not at the mercy of the