Posts

Unity over Rights Pave Ethiopian Oppositions’ Future

Image
It takes two to tango. EPRDF’s talk about democracy appears to deal more with the image of democracy than with its reality. The oppositions’ talk about democracy seems to be targeted more at assuming power by whatever means than at providing a unified alternative for the people to choose from. That is the drama of democracy played everyday inEthiopia. The vital question, however, is; how can the drama be abandoned and reality be adopted? Standing at the fore of the stage is the Ethiopian opposition. How the drama would be played out would also be highly dependent on their move. The political climate on the ground is squeezing the opposition with each passing day. To make things worse, the opposition itself is weak due to divisions. Forgoing its purpose, it settles for mere opposition. The opposition has to go through rebirth. Otherwise, it will soon become a do-nothing force as far as peaceful struggle is concerned. Even then, the opposition is not at the mercy of the

‹‹ሐዋሳ ላንጋኖ ለሽርሽር ……

በሔኖክ ረታ ኅዳር መባቻ ማለዳ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰበሰበው የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሴንተር (ኤምሲሲ) ሠራተኛ በድርጅቱ አማካይነት የተሰናዳለትን የሽርሽር ጉዞ ለመጀመር በንቃት ቦታ ቦታውን ይዟል፡፡ ሁለተኛውን የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሞያዎች የእግር ኳስ የዋንጫ ውድድርን በሦስተኛነት በማጠናቀቁ ነበር ከሌሎቹ አሸናፊዎች ጋር በመሆን ይህን የጉዞ ዕድል ያገኘው፡፡ ከማለዳው አንድ ሰዓት ላይ ወደ ሐዋሳ ከተማ የተጀመረው ጉዞ ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ዱከም ከተማ ላይ የቁርስ ቆይታ ነበረው፡፡ በቀድሞው አትሌት ወርቁ ቢቂላ ሆቴል ቁርስ የተመገቡት የኤምሲሲ አባላት ከቀድሞው አትሌት ጋር ትውውቅና የተወሰነ ቆይታ የማድረግ አጋጣሚም ነበራቸው፡፡ ቢሾፍቱንና ሞጆን በተከታታይ አልፎ በግምት አምስት ሰዓት ገደማ ላይ የካስቴል ወይን እርሻና ፋብሪካ ለመጎብኘት አዳሚ ቱሉ ወረዳ ደርሷል፡፡ በዘመናዊ ማሽኖችና ቴክኖሎጂዎች የተገነባው የወይን መጥመቂያ ፋብሪካ ከተንጣለለው የወይን እርሻ በሰው ኃይል አማካይነት የተለቀመውን ፍሬ በረዥም የጊዜ ሒደት ውስጥ የሚፈለገውን የወይን ጣዕም አቀነባብሮ ለገበያ የሚያቀርብ ግዙፍ የወይን እርሻና ማምረቻ እንደሆነ በድርጅቱ የምርት ክፍል ባለሞያ የሆኑት አቶ ዳዊት ገብሬ ለጎብኚዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ እንደ ብረት ምጣድ በጋለው የመኪናው ጣራና ግድግዳ በኩል እየገባ የሚፋጀው ጠራራ ፀሐይ ጎብኚዎችን በከፍተኛ ሙቀት ቢፈትንም በጨዋታና በሙዚቃ የተዋዛውን ጉዞ ሊያደበዝዘው አልቻለም ነበር፡፡ መቂ፣ ዝዋይንና አርሲ ነገሌ ከተሞችን በፈታኝ የፀሐይ ሙቀት የጨረሰው ጉዞ ሰባት ሰዓት ገደማ ላይ ከመዳረሻዋ የሐዋሳ ከተማ በ23 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ብቻ ቀደም ብላ የምትገኘውን ሞቅ ያለች

ግልጽነትና ተጠያቂነት የመልካም አስተዳደር ወሳኝ መሣሪያዎች ናቸው

Image
ሕዝብም መልካም አስተዳደር እፈልጋለሁ ይላል፡፡ መንግሥትም መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ማረጋገጥ ራዕዬ፣ ዓላማዬና ዕቅዴ ነው ይላል፡፡ በዚህ ላይ ልዩነት የለም፡፡ በአባባል፣  በፍላጎትና በምኞት ደረጃ፡፡ መልካም አስተዳደርን ተግባራዊ ለማድረግ ግን የግድ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በተግባር ማስፈን ያስፈልጋል፡፡ ግልጽነትና ተጠያቂነት ከሌለ መልካም አስተዳደር አይኖርም፣ አይሰፍንም፡፡ ግልጽነት ሲባል ትርጉሙ ‹‹ግልጽና ግልጽ›› ነው፡፡ በሕዝብ ተመርጫለሁ የሚል መንግሥት ውክልና ሰጥቶ፣ መርጦ ለሥልጣን ላበቃው ሕዝብ የሚሠራውንና የሚያስበውን በግልጽ ማሳወቅ አለበት፡፡ ሕዝብ መንግሥትን እዚህ ጋ ተሳስተሃል፣ እዚህ ጋ አጥፍተሃል፣ እዚህ ጋ ጥሩ ሠርተሃል፣ እዚህ ጋ እንዲህ ብታደርግ ይሻላል በማለት ሕገ መንግሥቱ የሰጠውን መብት ተጠቅሞ ሐሳብ ለመስጠት፣ ሂስ ለማቅረብና ድጋፉን ለመግለጽ መንግሥት የሚያከናውነውን ሁሉ በግልጽ ሊያውቀው ይገባል፡፡ መንግሥት ግልጽ ሊሆንለት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥታችን ግልጽነትን ይደግፋል፡፡ ሁሉም ነገር ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆን የሚያዝና የሚደነግግ ሕግም አለን፡፡ የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፡፡ በሕገ መንግሥትና በሕግ በኩል በአገራችን ግልጽነት እንዳይኖር የሚያደርግ አንዳችም ነገር የለም፡፡ በተግባር ግን ግልጽነት እየተዳከመ ነው፡፡ በተግባር ግን ቢሮክራሲው የሚጠቅመውን ይናገራል፤ የማይጠቅመውንና የሚያጋልጠውን ይደብቃል እንጂ ግልጽነት (ትራንስፓረንሲ) እውን ሊሆን አልቻለም፡፡ ለመልካም አስተዳደር ትልቅ የተደቀነ እንቅፋት የሆነው የግልጽነት አለመኖር ሆኗል፡፡ ተጠያቂነትን (አካውንተቢሊቲ) በሚመለከትም ሕገ መንግሥታችንና ሕጎቻችን የሚደግፉትና የሚያበረታቱት ናቸው፡፡ በተግባር ግን ተጠያቂነት እየጠፋ ነው፡፡ ቢሮክራ

Media and the political process

The thinking that media and the political process have a dialectical relationship, that includes action and reaction, is a recent and not yet well developed theory of mass communication. Whether media actually does have the ability to influence foreign policy is the subject of intense debate among scholars, journalists and policy makers.  “The CNN (Cable News Network) Effect” , as it is called by scholars, however, demonstrates the impact of new global real time media. The CNN effect regards the role of media as typically substantial if not profound. Some radicals even define the CNN effect as a loss of policy control on the part of policymakers, because of the power of the media; a power that they can do nothing about. Their thinking is a major deviation from the existing and almost hegemonic thinking of the propaganda model. According to propaganda model the relationship between the media and the political process was seen as a rather supplementary one. The media were thought to

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውስጥ - የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽኗ እና የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

Image
በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መመረጥ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሯ እና የሰመጉ ዳይሬክተር ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ​​ የኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት መመረጥ ካስመዘገበቻቸው የምጣኔ ኃብት እና ማኅበራዊ ስኬቶች በአካባቢውና በምክር ቤቱ ምሥረታ ላይም ከተጫወተቻቸው ሚናዎቿ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አምባሣደር ጥሩነህ ዜና አስታውቀዋል፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ​​ በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫው በወቅቱ ያስደነገጠው መሆኑንና ምናልባትም ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዟን እንድታሻሽል ግፊት ማሣደሪያ አጋጣሚ ሊሆንም እንደሚችል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ሞላ አመልክተዋል፡፡ ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡ ዝርዝሩን ከዘገባው