Posts

አካል ጉዳተኞችን በማቋቋምና በመደገፍ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማብቃት በሚል የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበር ያዘጋጀው የኘሮጀክት ትውውቅ መድረክ በአለታ ወንዶ ወረዳ ተካሄደ፡፡

አቶ ባልጉዳ ጳውሎስ የአለታ ወንዶ ወረዳ አካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር እንዳሉት አካል ጉዳተኞች ካለባቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ተላቀው የበኩላቸውን  አስተዋፅኦ ለማበርከት የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አቶ ተፈራ ጨመሳ የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበር አማካሪ በበኩላቸው አካል ጉዳተኛችን ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ከማብቃት በተጨማሪ የአካል ጉዳተኛ ህፃናትን የትምህርት ተሳትፎ በማሳደግ የወደፊቱን የትውልድ ተስፋ እንዲያብብ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለአስሩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ለእያንዳንዱ ተማሪ በወር 15ዐ ብር ለአስር ወራት ድጋፍ በማድረግ ለሁሉም ተማሪዎች 15 ሺህ ብር ተመድቦላቸው በመማር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN405.html

ባለፈው ዓመት በሁሉም የልማት እቅዶች አፈፃፀም ላይ የታዩ ክፍተቶችንና ውስንነቶችን ለመቅረፍ መዘጋጀቱን በሲዳማ ዞን የቡርሳ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የወረዳው ምክር ቤት 3ኛ ዙር 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ ዋና አስተደደሪው አቶ አማረ ሻላሞ እንዳሉት  የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የልማት እቅዶች በጠንካራና በተደራጀ የልማት ሰራዊት መመራት አለባቸው ብለዋል፡፡ በወረዳው በሚከናወነው የበልግና የመኸር እርሻ 7 ሺህ 831 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች በመሸፈን 16 ሺህ 584 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡ ለዚህም15 ሺህ 13ዐ ኩንታል ዳኘና ዩሪያ ማዳበሪያ እንዲሁም አሲዳማ አፈርን በማከም ለእርሻ ሥራ ለማዋል 2ዐዐ ኩንታል ኖራና የተለያዩ ሰብሎች 3 ሺህ 289 ኩንታል ምርጥ ዘር በግብዓትነት እንደሚሠራጭም አቶ አማረ አስረድተዋል፡፡ ጉባኤው ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ መጠናቀቁንም የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN505.html

የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ

በ Hagerselam Haroressa ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ መግቢያ አገራችን ለአያሌ ዘመናት ለተለያዩ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋልጣ የቆየች በመሆኗ አብዛኛው ህዝቧ በድህነት አረንቋና በኋላቀርነት ቀንበር ተተብትቦ መኖሩ የማይካድ ታሪካዊ ሀቅ ነው :: የሲዳማ ህዝብም የዚሁ አስከፊ ሰቆቃ ተጠቂ በመሆኑ ይህንን ነባራዊ ችግር ለመታገልና ለመፍታት ፈርጀ - ብዙ ትግል ማድረግ በማስፈለጉ፣ እንዲሁም የችግሩን መሠረታዊ ምንጭ አጉልቶ ለማሳየትና የመፍትሔውንም አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያስችል የትግል ስልት ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ለ ማዘጋጀት ተገደናል :: እንደሚታወቀው የሲዳማ ብሔር ባለፉት አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከመውደቁ በፊት የራሱ የሆነ ባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓት (The Luwa System) ፣ ቋንቋና (Sidaamu Afoo) ባህል፣ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አመጣጥ ያለው ህዝብ ሆኖ በአንድ ጆኦግራፊያዊ ክልል ሰፍሮ የሚኖር በአንድ ስነልቦና የተሳሰረ ታላቅ ብሔር እንደሆነ ይታወቃል :: ይሁን እንጂ ህዝቡ በእነዚያ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከወደቀ በኋላ በራሱ ማስተዳደር እንዳይችልና ነፃነት እንዳይኖረው ፣ በገዛ ክልሉ ሊኮራባቸው ቀርቶ በአደባባይ በቋንቋውና በባህሉ እንዳይጠቀምበት ይልቁንም እንዲያፍርበት ተደርጎ ቆይቷል ::  በአጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት የበላይ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት እንዳይኖረው በተለያዩ ሥውር ስልቶች ተከልክሎ ቆይቷል :: ከእነዚህ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ለመላቀቅ በየሥርዓቱ በተናጠል፣ በቡድንና በተደራጀ መልኩ ሳይታገል ያለፈበት አንድም ጊዜ አልነበረም :: በተለይ የንጉሣዊው ሥርዓ