Posts

የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ

በ Hagerselam Haroressa ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ መግቢያ አገራችን ለአያሌ ዘመናት ለተለያዩ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋልጣ የቆየች በመሆኗ አብዛኛው ህዝቧ በድህነት አረንቋና በኋላቀርነት ቀንበር ተተብትቦ መኖሩ የማይካድ ታሪካዊ ሀቅ ነው :: የሲዳማ ህዝብም የዚሁ አስከፊ ሰቆቃ ተጠቂ በመሆኑ ይህንን ነባራዊ ችግር ለመታገልና ለመፍታት ፈርጀ - ብዙ ትግል ማድረግ በማስፈለጉ፣ እንዲሁም የችግሩን መሠረታዊ ምንጭ አጉልቶ ለማሳየትና የመፍትሔውንም አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያስችል የትግል ስልት ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ለ ማዘጋጀት ተገደናል :: እንደሚታወቀው የሲዳማ ብሔር ባለፉት አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከመውደቁ በፊት የራሱ የሆነ ባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓት (The Luwa System) ፣ ቋንቋና (Sidaamu Afoo) ባህል፣ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አመጣጥ ያለው ህዝብ ሆኖ በአንድ ጆኦግራፊያዊ ክልል ሰፍሮ የሚኖር በአንድ ስነልቦና የተሳሰረ ታላቅ ብሔር እንደሆነ ይታወቃል :: ይሁን እንጂ ህዝቡ በእነዚያ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከወደቀ በኋላ በራሱ ማስተዳደር እንዳይችልና ነፃነት እንዳይኖረው ፣ በገዛ ክልሉ ሊኮራባቸው ቀርቶ በአደባባይ በቋንቋውና በባህሉ እንዳይጠቀምበት ይልቁንም እንዲያፍርበት ተደርጎ ቆይቷል ::  በአጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት የበላይ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት እንዳይኖረው በተለያዩ ሥውር ስልቶች ተከልክሎ ቆይቷል :: ከእነዚህ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ለመላቀቅ በየሥርዓቱ በተናጠል፣ በቡድንና በተደራጀ መልኩ ሳይታገል ያለፈበት አንድም ጊዜ አልነበረም :: በተለይ የንጉሣዊው ሥርዓ

የሐዋሳ ፍርድ ቤት በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት የተለያዩ ቅጣቶችን መወሰኑ እያነጋገረ ነው

Image
-    በአንደኛው ቅጣት 10 ዓመት በሌላኛው ደግሞ ዕድሜ ልክ እስራት ወስኗል በታምሩ ጽጌ በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል በቀረቡለት የተለያዩ ክሶች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን መስጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑን፣ ሁለቱም የክልሉ የከፍተኛ መርማሪ ከሳሾች ክሶች ያስረዳሉ፡፡ የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ከሳሽ መጀመርያ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበ ሲሆን፣ ለክሱ መነሻ የሆነው ፍሬ ጉዳይ አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሁለት ጓደኞቹ የተፈጸመን የግፍ አገዳደል ወንጀል የሚያስረዳ ነው፡፡ ከሳሽ በክሱ ላይ እንዳብራራው፣ ሟች አማረ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ አፈወርቅ ሌሊሳና ውብሸት ደሞል ከሚባሉ ጓደኞቹ ጋር በተለያዩ ሬስቶራንቶችና ሆቴሎች ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ጓደኞቹ አስቀድመው በነበራቸው የመግደል ሐሳብ፣ ወጣቱን በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በማዞርና በማጠጣት በስካር ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ፣ ወደ ሰዋራ ሥፍራ በመውሰድ ውብሸት የተባለው ጓደኛው ሲይዘው፣ ጌታሁን የተባለው ሌላኛው ጓደኛው በስለት የግራ ደረቱን እንደወጋው ክሱ ያብራራል፡፡ ጓደኞቹ ድርጊቱን ሌላ ሰው የፈጸመው ለማስመሰል ለመሞት በማጣጣር ላይ የነበረውን አማረ ሙሉጌታን በመሸከም አሴር ወደሚባል ሆስፒታል ቢወስዱትም፣ ሕክምና ሳይደረግለት ሕይወቱ ማለፉን የቅጣት ውሳኔው ሰነድ ያስረዳል፡፡ ጓደኞቹ በጥርጣሬ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃል፣ ጓደኛቸው መሆኑንና ለሦስት ዓመታት

Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem.

Image
Addis Ababa, Ethiopia – Week 4 of the Ethiopia Premier League will continue here with current leaders Dedebit FC taking on Ethiopian Insurance; EEPCO hosting Adama and defending champions St. George entertaining newly promoted side, Ethiopian Water Works FC. Mugher Cement will face Harar Beer at home and Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem. The league will continue on Monday with two matches featuring Ethiopian Coffee vs Hawassa and CBE vs Defence Force. After 3 matches, Dedebit and Harar Beer seat on top of the league with 7 points each, followed by EEPCO, Ethiopian Coffee and St. George FC. Week 4 Sunday, November 11 Dedebit v Insurance EEPCO v Adama Mugher v Harar Brewery Sidama Coffee v Arba Minch Water Works Sport v St George Monday, November 12: CBE v Defence Force Ethiopian Coffee v Awassa