Posts

የእጭዎችና የመራጮች ምዝገባ ከታህሳስ 22/2005 ጀምሮ ይካሄዳል

Image
አዲስ አበባ፤   ጥቅምት 28/ 2005 (ዋኢማ)  - ለአራተኛውን  የአካባቢና የአዲስ አበባ   ምርጫ የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ  ከታህሳስ   22 እስከ ጥር 21/2005 ዓ/ም እንደሚካሄድ   ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ  ምርጫ ቦርድ   የህዝብ  ግንኙነት   ማስተባበሪያ   ኋላፊ   ወይዘሮ   የሺ ፈቃድ   ለዋልታ   እንደገለጹት በ2005 ለሚካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ  የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ  በወጣው የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን ከወዲሁ አንዳንድ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። እንደ ሃላፊዋ ገለጻ ከዚህ   በፊት  የተደረጉትን   የአካባቢ   ምርጫዎችን     በመገምገም የነበሩባቸውን ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በመለየት  የዘንድሮውን ምርጫ  በተሻለ   መልክ ለማጠናቀቅ  ቦርዱ  ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው።፡ ቀደም ሲል የመራጮች   የስነ  ዜጋ   ትምህርት  መሥጫ  መመሪያ አለመኖሩን  ያስታወሱት ወይዘሮ  የሺ  ለ2005 ዓ/ም  የአካባቢ   ምርጫ   የዜጎች  የስነ    ዜጋ  መመሪያ   በ13  የተለያዩ  ቋንቋዎች ተቀርጾ  ሥልጠና  እየተሰጠ   ይገኛል  ብለዋል፡፡ �  የባለድርሻ   አካላት አቅም   አለመገንባት አንዱ ችግር እንደሆነ  የጠቆሙት ወ/ሮ  የሺ    ችግሩን   ለመቅረፍም  ቦርዱ  ለፖለቲካ   ፓርቲዎች   የምክክር   መድረክ   በማዘጋጀትና የተለያዩ  ሥልጠናዎችን በመሥጠት   ላይ   እንደሚገኙ    ገልጸዋል ፡፡  እንደ ሃላፊዋ ገለጻ      በ2005ቱ   የአካባቢ   ምርጫ የሴቶችን   ተሳትፎ    ለማሳደግ   የሚያስችሉ   ሥልጠናዎች   ከተለያዩ   የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር  በመተባበር  ስልጠና  እየተሰጠ  መሆኑን   ገልጸዋል ፡፡ http://www.waltainfo.com/index.php?o

መንግሥትና ኢሕአዴግ ለአንደኛ ሴሚስተር ፈተና ይዘጋጁ

ከሐዘን በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሾም ጉዞው ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የታቀደው በሙሉ ተፈጸመ ወይ ብለን አንገመግምም፡፡ ገና ጅምር ላይ ነንና፡፡ ይህ ጥያቄ የሚነሳው በአጠቃላዩ የመልቀቂያ ፈተና ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ እየተደረገ ያለው ጉዞ ግን የመጀመሪያ ሴሚስተር በመሆኑ፣ ኢሕአዴግም እንደ ድርጅት መንግሥትም እንደ መንግሥት ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ ከተዘጋጁበት ፈተናው በጣም ቀላል ነው፡፡ ካልተዘጋጁበት ደግሞ ፈተናው ቀላል ቢመስልም፣ መልስ ለመስጠት ግን አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ የአሁኑ የመጀመሪያው ሴሚስተር ፈተና ዋነኛው ጥያቄ ኢሕአዴግም መንግሥትም በውስጣቸው አንድ ሆነው፣ በአንድ ልብ እየተወያዩ፣ እየተመካከሩና እየተናበቡ እየተንቀሳቀሱ ናቸው ወይ የሚል ነው፡፡ ሕዝብ እንደ ፈታኝ ይህንን ጥያቄ ያቀርባል እንጂ መልሱን እንደ ፈተና ኢሕአዴግና መንግሥት የሚመልሱት ነው፡፡ ኢሕአዴግ ስንልም ሁለት ገጽታ አለው፡፡ አንደኛው ኢሕአዴግ እንደ ኢሕአዴግ በአጠቃላይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አራቱ አባል ድርጅቶች በተናጠል ናቸው፡፡ አራቱም ድርጅቶች በየግላቸው በውስጣቸው አንድ ሆነው እየተጓዙ ናቸውን? ልዩነት የሚባል ነገር አይኖርም እያልን አይደለም፡፡ ልዩነት ኖረም አልኖረም በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ ብልጫ እየወሰኑና እያፀደቁ እየተጓዙ ነው ያሉት? ወይስ የግልና የቡድን ስሜትና ዕምነት ይዘው ሳይቀናጁ እየተንገዳገዱ ናቸው? የየግላቸውን ሁኔታ አይተውና መርምረው አንድ በመሆን ጠንካራ አንድነት ያለውን የጋራ ድርጅት ኢሕአዴግን እያንቀሳቀሱ ናቸው ወይ? መልሱን ለራሱ ለኢሕአዴግና ለመንግሥት እንተወዋለን፡፡ በመልሱ ዙሪያ ግን አጽንኦት ሰጥተን የምንለው ነገር አለ፡፡ አንደኛ ‹‹ለተማሪ ዜሮ አይሰጥም›› የሚባለው ነገር በዚህ ፈተና አይኖርም፡

Who has the mandate in Ethiopia?

Image
Posted by  admin  on November 8, 2012 0 Comment By Mekonnen H. Birru (PhD) Yesterday, over 90 million Americans voted and in Texas time exactly 11:12 PM, the former one term U.S senator from the state of Illinois won his second and last term of the U.S. presidency with 303 electoral votes. Florida’s result still not in but doesn’t matter anymore because the young African American incumbent won six of the seven battle ground states such as Iowa, Colorado, Nevada, and Ohio. Bereket Simon and Hailemariam Desalegn “We will pray for him,” said Mr. Romney in his concession speech right before Obama’s hopeful speech. To the rest of us who had been anxiously waiting to see the election result, now the snow is melted, the spring is in, the sun is rising again. Now, we all clearly know who has the mandate to lead this great nation; yes, we have a new democratically elected president. Not just democrats or the 50% who voted for Obama but the entire nation accepts the re-elected Com

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የአለታ ጩኮ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉደዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በወረዳው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ 1ዐዐ በላይ ሰዎች እንዲሁም ከሀይማኖት መሪዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ዙሪያ ሰሞኑን ውይይት ተካሂዷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ሮማን ማሞ እንደገለፁት መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋና አሰገድዶ የመድፈር ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚሁ በተያያዘም የቤተሰብ ምጣኔ፣ በሴት ልጅ ግርዛትና በተዛማጅ ችግሮች ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ በአለታ ጩኮ ወረዳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኡየሱስ የምግብ ዋስትናና ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ቲራሞ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመከላከል ጎን ለጎን የጤና ለማት ሠራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች እንደምትገኝ መግለፃቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በተያዘው የበጀት ዓመት የጤና ልማት ሠራዊት አቅምን በማጎልበት ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታደሰ አንዳስታወቁት በወረዳው የሰለጠኑ ሞዴል ቤተሰቦችን በ1 ለ5 ቁርኝት በማደራጀትና የየግላቸውን እቅድ እንዲያዘጋጁ በማድረግ ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢ ንፅህናን እንዲጠበቅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመትም ጽህፈት ቤቱ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተጠናከረ የማህበረተሰብ ውይይቶች በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊው በተለይም ከወረዳው ወባማ በሆነ 6 ቀበሌያት ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እስከ 5 አጎበር ከመከፋፈሉ በተጨማሪ የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ የጤና ተቋማት ተደራሽነት ለማስፋፋት በወረዳው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ 5 ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ በመንግስት በጀት በ2ዐዐ4 ግንባታቸው እየተገነቡ ካሉ ሁለት አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች የአንደኛው ግንባታ ተጠናቆ ርብርብ መደረጉንና በወረዳው ዋና ከተማ በቀባዶ አንድ ሆስፒታል በመገንባት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡