‹‹የዳኝነት ሥርዓቱ ራሱን ከመቆጠብ መውጣት ይኖርበታል››
አቶ ጌታሁን ካሣ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል መምህር አቶ ጌታሁን ካሣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል መምህር ናቸው፡፡ የትግራይ ብሔራዊ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አባል በመሆንም ለሁለት የሥራ ዘመኖች አገልግለዋል፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤትም በመምህርነት ሠርተዋል፡፡ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከእንግሊዝ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት ማዕከል በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የፒኤችዲ ምርምራቸውን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ሰለሞን ጎሹ በዳኝነት ነፃነትና በሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ላይ አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ የፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ዳኞች ምን ዓይነት ሚና ነው ያላቸው? አቶ ጌታሁን ፡- ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ሕገ መንግሥቶች ወይም ከዚያ በፊት የነበሩትን ሁኔታዎች ስንመለከት የዳኝነት ተቋማት ሥራ በዋነኛነት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የሁለት ወገኖችን ክርክርና ማስረጃ በመመልከትና በማገናዘብ ውሳኔ መስጠት ነው፡፡ የመንግሥት አደረጃጀትን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ በሥልጣን ክፍፍል መርህ ስናይ ግን በሦስት እንከፍላለን፡፡ ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈጻሚው ይኖራሉ፡፡ በአገራችንም እነዚህ የመንግሥት አካላት አሉን፡፡ አንዱ በአንድ ወቅት ከነበረው የሚለይበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ የተለያዩ ገጽታዎችም አሏቸው፡፡ ለምሳሌ የተጻፈ ሕገ መንግሥት ከኖረን ጊዜ ጀምሮ ያለውን ብንመለከት የዳኝነትና የሕግ አስፈጻሚነት ሥልጣን በአንድ አካባቢ ተደራርቦ የምናገኝበት ሁኔታ ነበር፡፡ አሁን ባለው