Posts

የቴዲ አፍሮ የሐዋሳ ኮንሰርት ለሳምንት ተላለፈ

Image
ስቴዲየሙ ለጨዋታ ተፈልጓል በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ኮንሰርት ስቴዲየሙ ለኳስ ጨዋታ በመፈለጉ ተሰርዞ ለሚቀጥለው ቅዳሜ ተላለፈ፡፡ የቤለማ ኢንተርቴይመንት የፕሮሞሽን እና ኢቬንት ሐላፊ አቶ ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ) ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ ቤለማ ኢንተርቴይመንት በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ አስቦ ዝግጅቱን ካጠናቀቀ በኋላ ኮንሰርቱ ሊደረግበት የታቀደው ስታዲየም ለኳስ ጨዋታ ይፈለጋል በመባሉ ዝግጅቱ ለጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ሊተላለፍ ችሏል፡፡ ዝግጅቱ በዕለቱ ሊደረግ ከታቀደ በኋላ ለፕሪሚየር ሊግ ዕጣ ሲወጣ የሐዋሳ ከነማ እና የመድሕን ጨዋታ ጥቅምት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በሐዋሳ ስታዲየም ስለወጣላቸው ኮንሰርቱ ሊተላለፍ እንደቻለ ታውቋል፡፡ የዝግጅቱ ቀን በመተላለፉ ለማስታወቂያ ከወጣው 42 ሺህ ብር ውጭ ምንም ዓይነት ኪሣራ አለመድረሱን የገለፀው ዲጄ ዊሽ፤ በቀኑ መተላለፍ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረው ትልቅ ስጋት የአርቲስት ቴዲ አፍሮን ፕሮግራም አለማወቃቸው መሆኑን ጠቁሞ፤ ሆኖም አርቲስቱ እና ዛየን ባንድ ትልቅ ትብብር እንዳደረጉላቸው ገልጿል፡፡

ተቃዋሚዎች የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት አሉ

በመጪው ሚያዚያ ወር በሚደረገው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ምርጫ ቦርድ ከ75 ፓርቲዎች ጋ ከትላንት በስቲያ የመከረ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከጊዜ ሰሌዳው በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገለፁ፡፡የምርጫ አጃቢና አሯሯጭ መሆን ስለማንፈልግ የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - ተቃዋሚ ፓርቲዎች፡፡ሃያ አንድ ነጥቦችን ባካተተው የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአንድነት ፓርቲ ሃላፊ አቶ አስራት ጣሴ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ በተጣበበበትና የፕሬስ ነፃነት በሌለበት ሁኔታ ነፃ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡ ወደ ጊዜ ሰሌዳ ውይይት ከመገባቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ ከህዳር 17 ጀምሮ የወረዳ የምርጫ ጽ/ቤቶች ተከፍተው ስራ እንደሚጀምሩና ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ምርጫው እንደሚደረግ የጠቀሱት አቶ አስራት፤ ከጊዜ ሰሌዳ በፊት መቅደም ያሉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፤ አጃቢ እና አሯሯጭ ሳይሆን ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ምርጫ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ ከሰፋና ሌሎች ችግሮች ከተፈቱ አንድነትና መድረክ በአካባቢ ምርጫ እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡ የኢዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ በበኩላቸው፤ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት የምርጫው ሜዳ መስተካከል አለበት ብለዋል - “የመራጮች ምዝገባ እና የፓርቲዎቹ የምርጫ ክርክር ጊዜ የተጣጣመ አይደለም” በማለት፡፡ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ያሉትን ችግሮች አጽድቶ የተመቻቸ የምርጫ ሜዳ እንዲፈጠር ጠይቀዋል - አቶ ወንድወሰን፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=3019:%E1%89%B0%E1%89%83%

ኢትዮጵያ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን የኤች.አይ.ቪ/ስርጭት ስርጭት ለመግታት ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 17/2005 ኢትዮጵያ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቫይረስ ስርጭት በመግታት ረገድ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡  ቢሮውና ኢንትራ ሄልዝ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከእናት ለእናት አመቻች ቡድን ጋር በመስራት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ /ጽንስ/ እንዳይተላለፍ በተሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የ200 ሕጻናት እናቶች ዛሬ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡  የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ፋንቱ ጸጋዬ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን በመከላከል ውጤታማ እየሆኑ ከመጡ ጥቂት አገሮች አንዷ ብትሆንም፤ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን ስርጭት ለመከላከል የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በመግታት ረገድ ያለውን ክፍተት ለመድፈን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕጻናት ላይ የሚኖረውን የቫይረሱን አዲስ ስርጭት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት የተያዘውን እቅድ በመቀበል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡  የእቅዱ መተግበሪያ ዋነኛው መንገድም እናቶች በእርግዝና ወቅት ምርመራ እንዲያደርጉና ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ከሆነም አስፈላጊውን ሕክምናና የምክር አገልግሎት አግኝተው መከላከያ በመውሰድ ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ሕጻን እንዲወልዱ ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ለዚህም የጤና ተቋማትን ማስፋፋትና በሁሉም ተቋማት አገልግሎቱ እንዲሰጥ ማድረግ ወሳኝነት እንዳለው ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከተማዋ የነበሯትን የጤና ጣቢያዎች ቁጥር በማሳደግና አገልግሎቱን በማጠናከር ሰፊ ሥራ መከናወኑንና በግል ጤና ተቋማት ጭምር አገልግሎቱ መስፋፋቱን አመልክተዋል፡፡ የጤና ተቋማቱን ቁጥር ወደ 11

ኢሕአዴግ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል ያስፈልገዋል

Image
ኢሕአዴግ በሕዝብ ተከብሮና ተደግፎ ጠንካራ መሠረት ይዞ ለመቀጠል ከፈለገ ይችላል፡፡ የሚችለው ግን ራሱን ሲያጠናክር ነው፡፡ ራሱን ማጠናከር የሚችለው ደግሞ ውስጡን ሲያፀዳ ነው፡፡ ውስጡን ማፅዳት የሚችለው ደግሞ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል ሲያካሂድ ነው፡፡ ደፋርና ቆራጥ የውስጥ ትግል ካካሄደ ፀድቶና ተጠናክሮ ይወጣል፣ ይቀጥላል፣ ይጓዛል፡፡ የለም አላደርግም፣ አልታገልም፣ አልቆርጥም፣ አልደፍርም ካለ ደግሞ ውስጥ ለውስጥ እየተሰነጣጠቀ፣ እየበሰበሰና እየተደረመሰ ይሄዳል፡፡ ይደክማል ከሕዝብ ይርቃል፡፡ የነበረው እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ኢሕአዴግ ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? 1.    ከላይ እስከታች በሙስና የተጨማለቁ በዝተዋል! አዎን ንፁኃን የሕዝብ አገልጋይ፣ ለልማትና ለለውጥ የቆሙና የሚታገሉ አባላትም አመራርም በኢሕአዴግ ውስጥ አሉ፡፡ በዚያው አንፃር ደግሞ ከሕዝባዊ መስመር እየራቁና እየሸሹ ለግል ገንዘብ፣ ንብረት፣ ክብርና ኔትዎርክ የሚሯሯጡ፣ በጉቦ የተጨማለቁና በሙስና የተነከሩ አሉ፡፡ እነዚህ በውስጥ ትግል፣ በደፋርና በቆራጥ ትግል ካልተገለሉና ድርጅቱ ካልፀዳ ድርጅቱን እያበሰበሱ የሚገድሉት ናቸው፡፡ 2.    አቅም አልባ… ምላስ  ብዙ በዙ! በብቃት መመደብ እየቀረ ደጋፊ እስከሆነ ችግር የለም እየተባለ የተሾመው ሁሉ የድርጅቱን ዓላማ ማራመድ አልቻለም፡፡ ሕዝቡንም ማገልገል አልቻለም፡፡ ባለአቅም እየጠፋ ባለምላስ በዛ፡፡ ተንዛዛ በጣም በዙ፡፡ ሕዝብ ይህንን እያየና እያስተዋለ ምንድን ነው ነገሩ? እያለ ነው፡፡ አይወስኑም፣ ቢሮ አይገቡም፣ አያሳምኑም፡፡ አንዳንዶቹም ይህን እያወቁ ሀቅን ከመጋፈጥ ይልቅ ሽሽትና ድብብቆሽ እየመረጡ ናቸው፡፡ ሕዝብ በድርጅቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ እያደረጉ ናቸው፡፡ 3.    ጠንካራ አን

Beyond the Politics: - A look at a Reality of Sidama Economy

Image
By Kinkino Kiya, October 25, 2012 According to the most recent World Bank’s report that analysis the World poverty index; Ethiopia by all measures remains one of the poorest countries of the world. The most critical challenge facing the Sidama authorities and the Ethiopian policy makers at large -today and for the years ahead is the urgent task of reducing absolute poverty from the Sidama region as well as for the federal authorities addressing the issues at a national level. The basic objective of economic resources management and the fundamental goal of government anywhere, at all times must be working towards improving the standard of living of their respective people’s over time in the given periods of time. [...] The numerous Ethiopians including the Sidama nation were so optimistic trusting that the current might declare war on the greatest enemy of our people, the abject poverty that has incarcerated the nation of the country with varying degrees. Regardless of the a