Posts

የዴሞክራሲ ስርዓትና መልካም አስተዳደር ለመገንባት የህግ የበላይነት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች በወንጀለ ቅጣት አወሳሰን በግሙሩክና በታክስ ጉዳዮች የእስራት ቅጣት ዙሪያ በቡታጅራ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡          የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አበራ እንደተናገሩት መልካም አስተዳደር ለመገንባትና ልማትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማስቀጠል በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ የፍትህ አሰጣጥ እንዲኖር የቅጣት አወሳሰን ወጥና ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡ በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውጤታማነትና ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ችግሮች ይታዩ እንደነበር የጠቆሙት ኘሬዝዳንቱ ችግሩን ለመቅረፍ በቅጣት አወሳሰን ላይ ተቀራራቢ የሆነ የቅጣት አወሳሰን እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ስልጠናው ሁሉም ዳኞች በተገቢው እውቀት ቅጣት አወሳሰድ ላይ ወጥ የሆነ ሥራ  እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስልጠናቸው ከክልሉ የተውጣጡ የዞኑ የወረዳ የፍርድ ቤት ኘሬዝዳንቶች እንዲሁም ዳኞች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/13TikTextN105.html

ከ2ዐዐ2 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ክልል ምክር ቤት አባልነት ሲያገለግሉ የቆዩት የተከበሩ አቶ ሀይሌ ባልቻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

ክቡር አቶ ኃይሌ ባልቻ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማዎች የተመራውን ፀረ ፊውዳላዊ ተቃውሞ በወቅቱ የነበሩ የይርጋዓለም ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም በትግል አጋርነት እንዲቀላቀሉ አስተባባሪ በመሆን መርተዋል፡፡ ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ በደርግ ዘመን በ1997 ዓ/ም በተካሄደው ብሔራዊ ሸንጎ ምርጫ በጎርቼ ምርጫ ክልል በእጩነት ቀርበው የደርግ ሥርዓት እስከ ተወገደበት እስከ 1983 ዓ/ም ድረስ የመርጣቸው ህዝብ መብት መከበር የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን የህይወት ታሪካቸው ይገልፃል፡፡ በማህበሪዊ ህይወታቸውም የስኳር በሽታ ህሙማን የሆኑና ከፍለው መታከም የማይችሉ የሀዋሣና የአካባቢው ታማሚዎችን በማስተባበር የስኳር ህሙማን ማህበር በማቋቋም የህክምና እርዳታና ስለ በሽታው ግንዛቤ እንዲያገኙ በጎ ተግባርን ፈፅመዋል፡፡ በቤተሰብ ህይወታቸውም ሴት ልጅን በማስተማር በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ እንደ መልካም አርአያ ይቆጠሩ አንደነበር የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥቅምት 12/2ዐዐ5  ሲፈፀም ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጨምሮ የከልል፣ የሲዳማ ዞንና የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡ ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ ባለትዳርና የ6 ወንድና የ4 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡

መምህራንን ለመመዘን ዝግጅቱ ተጠናቅቋል

Image
ሃዋሳ፡- የመምህራንን የሙያ ምዘና ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። የመጀመሪያው የመምህራን ምዘና በሕዳር 2005 መጨረሻ እንደሚካሄድ አስታወቀ። የደቡብ ክልል 18ኛ አጠቃላይ የትምህርት ጉባዔ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሠጣጥና እድሳት ዳይሬክተር አቶ ሳህሉ ባይሳ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የመምህራንን የሙያ ምዘና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ በመንግሥት በኩል ዋና ዋና ዝግጅቶች ተጠናቅ ቀዋል። ለምዘና ሥራው የሚረዱ ስታንዳርዶችን የማውጣትና እነዚህን ለማስፈፀም የሚረዱ መመሪያዎችን የማዘጋጀቱ ሥራ መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ሳህሉ፤ ለምዘና ሥራው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል። የፈተናው ዝግጅት ሥራም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተከናወነ መሆኑንና በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ተጨባጭ ተግባራት ለመጀመር መታቀዱን አብራርተዋል። በአገራችን የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥርዓት ሲጀመር ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆን አቶ ሳህሉ ገልጸው፤ የመምህራን ምዘና ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል። መምህራን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት ሙያቸውን እየፈፀሙ መሆኑን ለማወቅ እንደሚያስችልም ተናግረዋል። የምዘና ሥራው በዋናነት በክልሎች እንደሚመራ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ስታንዳርዶችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የምዘና ሥራውን በበላይነት የመቆጣጠር ሥራ እንደሚያከናውን አስረድተዋል። በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚዘጋጅና በቀጣይ ፈተናው በክልሎች የሚዘጋጅ መሆኑንም አስረድተዋል። ፈተናውን የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነትም የክልሎች እንደሚሆን አስታውቀዋል።

Judge Firehiwot Samuel's testimony on Prime Minister Hailemariam Desalegn

Image
Judge Firehiwot Samuel's testimony on Prime Minister Hailemariam Desalegn

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ዓለም አቀፍ የጉዲፈቻ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ

Image
ሃዋሳ፡- በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና አማራጭ የሌላቸውን ሕፃናት በሀገሮች መካከል በሚደረግ የጉዲፈቻ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር እየሠራ መሆኑን ገለጸ። በሀገሮች መካከል የሚደረገውን የጉዲፈቻ አገልግሎት ለማስፈፀም በወጣው የሄግ ስምምነት የአፈፃፀም ሂደት ላይ የባለድርሻ አካላትን አቅም ለማጎልበት በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ላይ የሚኒስቴሩ የሕፃናት መብትና ደህንነት የማስጠበቅ ዳይሬክተር ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁኔ እንደተናገሩት፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና አማራጭ የሌላቸው ሕፃናት በሀገሮች መካከል በሚደረግ የጉዲፈቻ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው። በሀገሮች መካከል የሚደረግን የጉዲፈቻ አገልግሎት ለማስፈፀም በወጣው የሄግ ስምምነት ሰነድ ላይ የተቀመጡ ሕጎችና አሠራሮችን እንዲሁም ኮንቬንሽኑን ለማስተግበር መዘጋጀቱን የገለጹት ዳይሬክተሯ፤ በማዕከላዊ ደረጃ በሚዋቀረው ተቋምና በአሠራሮቹ ዙሪያ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ለማስፋት መድረኩ ምቹ መሠረት እንደሚጥል ተናግረዋል። ኮንቬንሽኑን ተግባራዊ ለማድረግ የመንግሥት አካላት ከልማት አጋሮች ጋር በተቀናጀ በበቂ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል። ሕፃናት በሁሉም ረገድ የሚገጥማቸውን ችግሮች በተቀናጀ መልኩ ለመፍታትና ሁለንተናዊ መብታቸውንና ደህነነታቸውን በተጨባጭ ለማስከበር የሚደረገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገር አኳያ መድረኩ በተሻለ አቅም እንደሚሠራ ተናግረዋል። ውይይቱ በፌዴራልና በክልል የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሠራርን ከማጠናከር አኳያ ፋይዳው ጉልህና ውጤታማ እንደሆነም አብራርተዋል። በሕፃናት ሰብአዊ መብት መ