Posts

በሲዳማ ዞን ባፈው የክረምት ወራት ከ111 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት...፡

በሲዳማ ዞን ባፈው የክረምት ወራት ከ111 ሺህ  በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ የመንግስት በጀት ከወጪ ማዳናቸውን የዞኑ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የወጣቶች ዘርፍ በ2ዐዐ4 እቅድ አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 እቅድ ትግበራ ዙሪያ ሰሞኑን ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዚህን ወቅት የመምሪያው ምክትልና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ሳሙኤል እንዳሉት ወጣቶቹ በተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ሥራዎች በመሳተፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡ በአካባቢ ልማትና በአፈር ጥበቃ ብቻ ከ5 ሺህ 5ዐዐ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል በፓኬጅ ለተደራጁ ወጣቶች ከተሰራጨው ከ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የብድር ገንዘብ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንዲመለስ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና አፈፃፀሙ ከግማሽ በታች ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው ለዚህም በምክንያነት የሚጠቀሱት የተሰጠው ብድር ሳይመለስ በወቅቱ የነበሩ ኃላፊዎች መቀያየር እንዲሁም አንዳንድ ወጣቶች ገንዘቡ የማይመለስ አድርገው መመልከትና ጉዳዮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ ያለመሥራት ናቸው ብለዋል፡፡ ዘገባው የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/9TikTextN405.html

በደቡብ ክልል ከተገነቡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ጀመሩ

አዋሳ ጥቅምት 14/2005 በደቡብ ክልል በ240 ሚልዮን ብር እየተገነቡ ካሉ 50 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 46ቱ ተጠናቀው አገልግሎት መጀመራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አዳነ ንጉሴ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ የምዕተ ዓመቱን የትምህርት ልማት ግቦች ለማሳካት ለተገነቡት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የውስጥ ድርጅት በማሟላት አገልገሎት ጀምረዋል፡፡ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልገሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች መካከል 32ቱ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ቀሪዎቹ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ግንባታው የአስተዳደር ቢሮ፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መፃህፍትና የመፀዳጃ ቤቶችን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በአብዛኛው የተከናወነው ቀደም ሲል 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ባልተዳረሰባቸው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መሆኑን የገለጹት አቶ አደነ በዚህ አካባቢ የሚታየውን የተሳትፎ ልዩነት ለማሻሻል እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ ለአገልገሎት መብቃታቸው በክልሉ 287 የነበረውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ 333 በማሳደግ ከ22ሺህ ለሚበልጡ ተጨማሪ ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ከመረዳቱም ባሻገር በትምህርት ቤትና በመኖሪያ አካባቢ መካከል ባለው ርቀት ምክንያት የሚደረሰውን ችግር የሚያስቀርና አቅም የሌላቸው ወላጆችን ችግር በእጅጉ እንደኒፈታ ገልጸዋል፡፡ በ2004 የትምህርት ዘመን አንድ ለ 66 የነበረውን የተማሪ ክፈል ጥምርታን ወደ አንድ ለ 60 ለማድረስ በመቻሉ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ አዲስ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ትምህር

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርና ሁለት የዞን ፖሊስ አዛዦች ታስረው እንዲቀርቡ ታዘዘ የሲዳማ ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥም ይገኝበታል

በታምሩ ጽጌ የፌዴራል ፍርድ ቤት ትዕዛዝን አላከበሩም በሚል የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ወይም ምክትል ኮሚሽነር፣ የጌዲኦ ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥንና የሲዳማ ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥን የፌዴራል ፖሊስ አስሮ የፊታችን ዓርብ እንዲያቀርባቸው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዘዘ፡፡ ፍርድ ቤቱ ኃላፊዎቹ ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ያስተላለፈው ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነና ባልታወቀ መንገድ ሥራውን እንዲያቆም የተደረገው፣ በጌዴኦ ዞን ይሠራ የነበረው የሳማሪታንስ ፐርስ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ሠራተኞች ባነሱት የመብት ጥያቄ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል፡፡ በድርጅቱ ላይ ክስ መሥርተው ለነበሩት አቶ ደረጀ ገብረ ማርያም፣ ወ/ሮ አቢጊያ ለገሰ፣ አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ፣ ወ/ሮ ምህረት አበራ፣ አቶ ዮሐንስ አዳሙ፣ ወ/ሮ እመቤት ዓለሙ፣ አቶ አዲስ አበባና አቶ መስፍን ግዛው፣ የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደየአገልግሎታቸው እንዲከፈላቸው ያስተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም፣ በድርጅቱ አካውንት ውስጥ ምንም ዓይነት ገንዘብ ባለመኖሩ፣ የድርጅቱ ንብረት መሆናቸው የተረጋገጡ ተሽከርካሪዎችን በመያዝና በሐራጅ ተሸጠው እንዲከፈላቸው ታህሳስ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ውሳኔ ማስተላለፉን የውሳኔው ግልባጭ ያስረዳል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ቆመው በተገኙበት የዞኑ ፖሊስ አዛዦች ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም መምርያ እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ትብብራቸውን ቢጠየቁም ሊያቀርቡ ባለመቻላቸውና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲያስፈጽም ቢታዘዝም ተፈጻሚ ሊያደርግ ባለመቻሉ፣ ሦስቱም በፌዴራል ፖሊስ ታስረው ጥቅምት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ የፍርድ ባለመብቶቹ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሕግ በወሰነላቸው መብት ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና በመጉላላት ላይ እንደሆኑም ፍርድ ቤ

በሲዳማ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የሬዲዮ ፕሮግራም በቅርቡ ይጀምራል

በሲዳማ ወቅታዊ ጉዳዮ ላይ በተለይ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የምያደርገው ''ሲዳማ በዚህ ሳምንት'' የተባለው የኢንተርኔት ላይ ሬዲዮ ፕሮግራም በወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ኣማካይነት በኣለም ላይ ለምገኙ የሲዳማ ተወላጆች እና ሲዳሚኛ ኣድማጮቹ ይስራጫል። የሙከራ ፕሮግራሙን ከታች ይከታተሉ:፡  Click Here የሙከራ ፕሮግራም

2012/13 Premier league “Meles Cup” season kicks-off Saturday

The 2012/13 Ethiopian premier league “Meles Cup” championship brings city rivals Saint George and Ethiopian Coffee in a head-on clash  for the  season’s opening weekend showdown. Runner-up Dedebit FC travels to  Yirgalem to face Sidama Coffeewhile newcomers Water Sport,  in their first-ever premier league match, is set to play against third place Electric FC.   The new season,  dedicated to the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, brings together 14 teams, including newcomers Insurance and Water Sport, for  fixtures to be conducted in two rounds. With eight teams from Addia Ababa, three from SNNPR, two from Oromia and one from Harar in contention, the new season is expected to bring the best out the players and fans,  following the superb triumph that the Ethiopian national team had against its neighbour, Sudan. The discipline and support of the great fans coupled with the determination of our players is something that will not be forgotten in a long time.  Of the fourteen,