Posts

በሲዳማ ዞን የአሮሬሳ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ለህዳሴው ግድብ ለ2ኛ ጊዜ በ1 ወር ደመወዛቸው ቦንድ ለመግዛት መስማማታቸውን ገለጹ፡

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ማሞ እንዳሉት ሠራተኞቹ ለቦንድ ግዥው ደመወዛቸውን የሚቆርጡት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ነው፡፡ የወረዳው ደኢህዴን ን/ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋቢሶ ጋቢባ በበኩላቸው በትምህርት ጥራት ላይ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ህዝቡ፣ መንግሥትና ድርጅት የአንድ ዓላማ የልማት ሠራዊት ሆነው መሥራት አንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ዎራና ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 53 በማድረስ በትምህርት ተደራሽነት ላይ የተገኘውን ስኬት በትምህርት ጥራትም ላይ መድገም አለብን ብለዋል፡፡ ዘገባው የሲዳማ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን  መምሪያ ነው፡፡

በተያዘው የበጀት አመት በሽታን በመከላከልና ጤናን በማጎልበት የህክምና አገልግሎቶችን በጥራትና በፍትሀዊነት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ አቅዶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የጎርቼ ወረዳ ጤና አጠባበቅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ጤና አጠባበቅ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተረፈ ያዕቆብ እንደገለፁት በወረዳው በጤናው ዘርፍ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ተደራሽነት ለማረጋገጥ የጤና አገልግሎት ተቋማትን በየቀበሌው በማስፋፋትና የጤና ልማት ሠራዊትን በመገንባት በተያዘው የበጀት ዓመት በዘርፉ ሰፊ ስራ ለመስራት ታቅዷል፡፡ በወረዳው ባለፈው የበጀት ዓመት የእናቶችንና የህፃናትን ጤና በመንከባከብ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር እንዲያስችል የፀረ ዘጠኝና የፖሊዬ ክትባቶች ተደራሽነት በበቂ ሁኔታ መከናወኑን ኃላፊው ገልፀው ከዚህም የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር በዘንድሮው ዓመትም የተሻለ አፈፃፀም ይመዘገባል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ አደረጃጀቶችንና ከ5መቶ 30 በላይ ቁርኝቶችን በመጠቀም አስራ ስድስቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆችን ለመተግበር በ6 የጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችና በ21 ጤና ኬላዎች ህብረተሰብ አቀፍ የጤና ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡ አምባዬ አዳነ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/6TikTextN305.html

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለምርጫ ሥነ ምግባር አዋጁና ድርድር ምን ይላሉ?

‹‹የሥነ ምግባር አዋጁን ፈርመን ብንደራደር በግሌ ችግር የለብኝም›› አቶ ግርማ ሰይፉ (መድረክ) ‹‹እንደ ዜጋ አዋጁን አከብራለሁ አስገድደው ሊያስፈርሙን ግን አይችሉም›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (መድረክ) ‹‹አጠቃላይ መፍትሔ አምጪ ባይሆንም አንድ ዕርምጃ ነው›› አቶ ሙሼ ሰሙ (ኢዴፓ) ‹‹አዋጁን ፈርመን ብንቀበልም ያስከበረልን ነገር ስለሌለ ከጋራ መድረክ ወጥተናል›› አቶ ወንድማገኝ ደነቀ (መኢአድ) በዮሐንስ አንበርብር የፓርቲዎች የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ የበርካታ ፓርቲዎች ይሁንታን አግኝቶ ከፀደቀ ሦስት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም፣ ይህ የሥነ ምግባር አዋጅ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሒደት ውስጥ ካበረከተው አስተዋጽኦ ይልቅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ፈተና የሆነ ይመስላል፡፡ አንዳንዶቹ በአዋጁ ዙሪያ እርስ በእርስ አይግባቡም፤ ሌሎች ደግሞ አዋጁን ፈርመን የገባንበት የድርድር መድረክ ያመጣልን ነገር የለም ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በተቋቋመው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተሳታፊ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥታቸውን አቋም ባለፈው ማክሰኞ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ከመድረክ ፓርቲ ለቀረበላቸው የድርድር ጥያቄ የኢሕአዴግንና የሚመሩትን መንግሥት አቋም አሳውቀዋል፡፡ መድረክ ከኢሕአዴግ ጋር ለመወያየት በመጀመሪያ የሥነ ምግባር አዋጁን መፈረም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የውይይት መድረኩ የተዘጋ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን አስመልክቶ የመድረክ አመራሮችን ያነጋገርን ሲሆን፣ መድረክ በተሰጠው ምላሽ ላይ ተነጋግሮ አቋም ያለመያዙን ለመረዳት ተችሏል፤ አመራሮቹ ግን እርስ በርሳቸው በጉዳዩ ላይ ያላቸው አቋም የተለያየ ነው፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመድረክ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ድርድር ለመጀመር የቀረበው
Image
Such negative connotations can be sensed in segments of the southern ethnic groups, among which the  Sidama  are a major group. Kellas (1991) says that " favorable attitudes are held about the in-group and unfavorable ones about the out- ... http://books.google.com.gt/books?id=fYiPXWEg6PgC&pg=PA32&lpg=PA32&dq=sidama&source=bl&ots=oBmPlGqzna&sig=rruH5TRmPIevWnozMI5Ni1u9yns&hl=en&sa=X&ei=h6WFUMDRGYm08ATM94HwDA&ved=0CFkQ6AEwCQ

Sidama and Ethiopian: the emergence of the Mekane Yesus Church in Sidama

Image
Sidama and Ethiopian: the emergence of the Mekane Yesus Church in Sidama