የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤት ትኩረት እንዲሰጡ ይደረጋል
ሀ ዋሳ፦ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤትና ሥነ ምግባር መሻሻል ትኩረት እንዲሠጡ ማድረግ የዘንድሮ የትምህርት ዘመን ቁልፍ ተግባሩ መሆኑን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ። በክልሉ በ2004 ዓ.ም በትምህርት ሥራ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሱፐርቫይዘሮች ተሸለሙ። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት 18ኛ አጠቃላይ የትምህርት ጉባኤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በተካሄደበት ወቅቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመዲን እንደገለጹት፤ የተጀመረውን የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ ሥራ በማጠናከር ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤትና ሥነምግባር መሻሻል ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ማድረግ የበጀት ዓመቱ ቁልፍ ተግባር ነው። ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በክልሉ በትምህርት ሠራዊት ግንባታ ሥራ መሠረት መጣሉን አስታውሰው፣ በ2005 ዓ.ም ሠራዊቱ ትክክለኛ ቁመና ተላብሶና የተቆጠረ ተግባር ወስዶ በተማሪዎች ውጤት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ዘንድሮ በትምህርት ልማት ሠራዊት ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላትን ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ ለማንቀሳቀስ መታሰቡን ያመለከቱት አቶ አህመድ፤ በሚሌኒየሙና በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተቀመጡትን ግቦች ከማሳካት አኳያ በተያዘው ዓመት ለትምህርት ተደራሽነት ሥራም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አመልክተዋል። በጎልማሶች ትምህርት ላይም የተሻለ ሥራ ለመሥራት መታቀዱን አብራርተዋል። የትምህርትን ጥራት የሚያረጋግጥ ሥራ በዋናነት የሚመራው በመምህሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ ክልሉ የመምህራንን አቅም ለማጎልበት የቅድመ ሥራ ላይ ሥልጠና፣ የሥራ ላይ ሥልጠናና አጫጭር ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል በቅርቡ ከ35ሺ