በሲዳማ ዞን የአማራጭ ኢነርጂ ልማት በመጠናከር ላይ ነው
ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በተካሄደው የደቡብ ክልል የውሃ ጉባኤ የቀረበው የ 2004 ኣ / ም የመምሪያው የስራ ኣፈጻጸም የተመለከተው ኣንድሪፖርት እንዳመለከተው በዞኑ ውስጥ በኣማራጭ ኢነርጂ ልማት ዘርፍ ኣበራታች ስራዎች ተከናውነዋል። መምሪያው በባጀት ኣመቱ ለማከናወን ካቀዳቸው 19 አዲስ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች ማህበራት እንዲቋቋሙ በማድረግ ለ 3- ማህበራት ፕሬስና ሞልድ ተገዝቶ ድጋፍ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ በ 19 ወረዳዎች በ 38 አማካይ ቦታዎች የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ላይ ለሕ ብረተ ሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ከእቅዱ በላይ በመስራት 4500 የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎ አንዲሰራጩ በማድረግ በርካታ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ኣድርጓል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ወረዳዎች 100 የሚሆኑ የቤተሰብ የሶላር ተጠቃሚ ማህበራት መደራጀታቸው ሲገለጽ፤ የኃይል አማራጭ ኢነርጂ አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። እንደሪፖርቱ ከሆነ የሶላር ኢነርጂ ተከላ እና የባዮ ጋዝ ግንባታ በተለያዩ ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን፤ ኣራት የአማራጭ ኢነርጂ ዳሰሳ ጥናት ም ተከናውነዋል።