Posts

ዘንድሮ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ዝግጅት እየተደረገ ነው

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 9/2005 (ዋኢማ)  - ዘንድሮ የሚካሄደውን የአካባቢ ምርጫ ግልጽ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለጹት ምርጫውን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ  ለማድረግ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ከወዲሁ እየተከናወኑ ነው። በተለያየ ደረጃ የነበሩ የምርጫ ጣቢያዎችን በአዲስ መልክ በማደራጀት በኦሮሚያ፤ በትግራይ፤ በአማራና በደቡብ ክልሎች ለሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚ አባላት  የአቅም ግንባታ ስልጠናመሰጠቱን  የገለጹት አቶ  ይስማ ለፖለቲካ ፓርቲዎችም በእጩዎች አቀራረብ ዙሪያ  ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል። የእጩ ተመራጮችና የመራጮች  ምዝገባ እንደዚሁም  ምርጫው የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር በመወያየት  ወደፊት እንደሚወሰን አቶ ይሰማ ገልጸዋል። በአካባቢ ምርጫው የወረዳ፤ የቀበሌ ፤የማዘጋጃ ቤት፤ የከተማ አስተዳደርና የዞን ምክር ቤቶች አባላት እንደሚመረጡ የገለጹት አቶ ይስማ  ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ መላው ህብረተሰብ  የበኩሉን ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በማዕድን ፍለጋና ልማት ላይ ተሰማርተዋል

Image
ሃዋሳ ጥቅምት 09/2005 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በማዕድን ፍለጋና ልማት ላይ መሰማራታቸውን የማዕድን ሚኒስትሯ ገለጹ፡፡ ስለማዕድን ኢንዱስትሪ ግልጽነት ኢኒሼቲቭ አሰራር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ግንዛቤ ለማስጨበጥ በሀዋሳ ከተማ ትናንት በተዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ እንደገለጹት ባለሀብቶቹ በዑጋዴን፣ በመቀሌ፣ በአባይ፣ በኦሞና በጋምቤላ በርካታ ኩባንያዎች በማዕድን ቆፋሮ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ማዳበሪያ፣ መስተዋት፣ ሳሙናና ሌሎችን ለማምረት በግብዓትነት የሚጠቅሙ በርካታ የማዕድን ሃብቶች እንዳሉ ያስረዱት ሚኒስትሯ በነዳጅ ዘርፍም በተለያዩ ሥፍራዎች ፍለጋው መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡  ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የምርት ዓይነቶች የማዕድን ሃብት 20 በመቶውን እንደሚይዝና ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ የወርቅ ፣ የታንተለም፣ የጌጣጌጥና የመሳሰሉት የማዕድን ጥሬ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከ460 ሚልዮን በላይ ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱንና በዚሀ ዓመትም ይህንን በእጥፍ ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በማዕድን ፍለጋና ምርመራ ስራ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሯ የማዕድን ሃብት አለኝታ ጥናት በተለያዩ ወቅቶች በውጭና በሀገር ውስጥ የስነ ምድር ባለሙያዎች ሲከናወን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ እስከአሁን በተደረጉ ጥናቶች የኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን፣ የጌጣ ጌጥ ፣ የወርቅ፣ የብረታ ብረት፣ የሃይድሮ ካርቦን ክምችትና የጂኦተርማል ማዕድናት መኖራቸው መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡  የማዕድን ኢንዱስትሪ

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል

ሃዋሳ ጥቅምት 09/2005 የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡ በሀዋሳ ሲካሄድ የቆየው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2004 አጠቃላይ የትምህርት ጉባዔ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የትምህርት አመራሮች ማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ መሃመድ አህመዲን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ሁሉም የህብረተሰብ ከፍልና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል፡፡ ክልሉ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሳይንስ ዘርፍ ትምህርትን ለማጠናከር ኮምፒዩተሮች እንደሟሉና የቤተ ሙከራ ግብአቶችን በማቅረብ አበረታች ስራ እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ለትምህርቱ ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠትና በአግባቡ እንዲመራ በማድረግ በኩል ለሌሎች አርአያ እንዲሆን የሚያስችል ስራ ማከናወኑን አመልከተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ30 ሺህ በላይ የወላጅና የመምህራን ህብረት አመራሮች በትምህርት ቤቶች በመደራጀት በየጊዜው የተለያየ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ለትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል በማድረግ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ በማድረግ በኩል አበረታች ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ካመጡት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቤተልሄም ታሪኩ፣ ገዛህኝ አበራ፣ ኢዩኤል ተከተልና ተማሪ ዲቦራ አበራ በሰጡት አስተያየት በትምህርት ቤቶች የተፈጠሩ አደረጃጀቶች፣ የመምህራን የዕለት ተዕለት ክትትልና አስፈላጊ የትምህርት ግ

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል በተያዘው ዓመት ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና ይለማል

Image
አዋሳ ጥቅምት 08/2005 በደብብ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ለተከላው ከ320 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ይዘጋጃል።  በክልሉ ግብርና ቢሮ የመንግስት ኮሚኒኬሽን የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አያሌው ዘነበ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ ቡና አብቃይ በሆኑ ወራዳዎች 116 ሺህ 648 ሄክታር መሬት በስግሰጋና በአዲስ በቡና ይለማል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በክልሉ ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ መጠን ለማሳደግ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።  በምርት ዘመኑ በክልሉ በቡና የተሸፈነውን መሬት መጠን 22 በመቶ ለማሳደግ በተያዘው ግብ መሰረት ምርጥ የቡና ዘር በማሰባሰብ በግብርና ምርምር ማዕከላት፣ በመንግስት፣ በባለሀብትና በአርሶ አደሩ የችግኝ ጣቢያ ከ122 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ምርጥ የቡና ዘር በማፍሰስ የችግኝ ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።  በቡና ተከላ ስራ ለሚሰማሩ ከ438 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች በቡና ማሳ ዝግጅት ተከላ እንክብካቤ አሰባሰብና አከመቻቸት ዙሪያ በተግባር የታገዘ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አቶ አያሌው ገልጸዋል።  በክልሉ በቡና ከለማውና ለምርት ከደረሰው 349 ሺህ948 ሄክታር ማሳ ከ3 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱንና የቡና ምርታማነትን በሄክታር 10 ነጥብ 5 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።  ዘንድሮ በቡና ለሚሸፈነው ከ116 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት 320 ሚሊዮን 895 ሺህ 915 የቡና ችግኝ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አቶ አያሌው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

ልዩነት ለዘለዓለም ይኑር!

ሰላም! ሰላም! እንዴት ናችሁልኝ? ‹‹እንደርሳለን ብለን ከመሸ ተነስተን፣ ስንገሰግስ ነጋ ምንድን ነው የሚሻለን?›› አለችላችሁ አንዷ አዝማሪ። እውነቷን ነው እኮ! ‹‹በዚህ አካሄዳችን እንኳን ልንደርስ የት እንደምንሄድም የምናውቅ አንመስልም፤›› ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ማንጠግቦሽን እንዲህ ብላት፣ ‹‹ኧረ ተረጋጋ። እንዴ ቅዠትና እውነትን ለይ እንጂ፤›› አለችኝ። ስንት መልካም ጅማሮዎች ባሉት በዚህ ጊዜ የእኔስ እንዲህ ማለት አይገርማችሁም? ‹‹የእኔ ባትሆኝ ይቆጨኝ ነበር፤›› አልኩ። የእውነት የእኛ አልሆን እያለን የሚያስቆጨን በዝቷል። ሌላ ምንም ሳይሆን የገዛ ኑሯችንን መውሰድ ትችላላችሁ። እኛ እየኖርነው የእኛ ይመስላል? እሱ በፈለገው እንጂ እኛ በፈቀድነው እንመራዋለን? ኧረ ጣጣ ነው ዘንድሮ ወገኖቼ! እውነቴን ነው የምላችሁ ልቤ ክፉኛ የሚዝለው እንዲህ እንዲህ ሳስብ ነው። የደላላ ልብ ጥቁር ድንጋይ ነው ያለው ማን ነው? ‹‹እኛም እኮ አንዳንዴ ሰው ነን፤›› አለች አሉ ጦጣ። ‘እኛም በቤታችን እህህ አለብን’ ሲባል ባትሰሙ ነው? ይህችን እንኳን የእኛ ሠፈር አባባል ስለሆነች ላትሰሙዋት ትችላላችሁ። አንድ ደፋር ነው አሉ፣ ‹‹ማንም ያለሙያውና ዕውቀቱ ስንት ቦታ እየገባ ነገር ሲያበላሽ እየታለፈ የእኛ ሠፈር በዚህ አባባል አትጠቆርም፤›› ብሎ የለፈፈው። ወይ የዘመኑ ፈጠራ! ሁሉንም ነገር ካዛመድነው እዚህ አገር ስለሙያና ባለሙያው ብዙ ይወራል። በየዘርፉ ለሥራቸው ባላቸው ትጋት ምሥጋና የምንቸራቸው ሰዎች ጥቂት አይደሉም እኮ። ባናስተውለው ነው እንጂ! ታዲያ በዚያው ልክ ያለ ቦታው ገብቶ የሚያደናቁረውን ስታዩ የማማረሪያ ቃላት አይበቋችሁም። በነገራችን ላይ የዘንድሮ ቃሪያ አንሰፍስፎ አላቃጥል ያለን ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ያለቦታቸው የገቡ የሰው ቃሪያዎች በ