Posts

ባለፉት ሁለት ዓመታት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያስገኘ ነው-ሚኒስትር ደሴ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/ 2005 ባለፉት ሁለት ዓመታት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አስታወቁ። የቅጂ መብት ጥሰት መጠን ከ95 በመቶ ወደ 65 በመቶ መውረዱንም ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ዘላቂነት እንዲኖረው ጠንካራ አገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም የመገንባቱ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአገሪቱ የውጭ ቴክሎጂዎችን የመማር የማላመድና የመጠቀም አቅም አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ ባለፉት ሁለት አመታት ግን አመርቂ የሚባል መሻሻል ተመዝግቧል። ፈጣኑን የኢኮኖሚ እድገት በሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲታገዝ አገራዊ ጥረት እየተደረገ መሆኑንምተናግረዋል። የዩኒቨርሲዎችና የኢንዱስትሪዎች ትስስርን ከማጠናከር አኳያም የተሻለ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማፈላለግ የማስገባትና የመጠቀም አቅምን የሚያዳብሩ የአሰራር ሥርዓቶች በመዘርጋታቸው ቴክኖሎጂን በማዛመድና በመቅዳት ረገድ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ ስለመሆኑም አስረድተዋል። ቴክኖሎጂን አስመስሎ በመስራት ከውጭ የሚገቡትን በአገር ውስጥ በማስቀረት ረገድም ተስፋ የሚሰጥ ውጤት እየታዬ መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ኃይል ልማት ፍላጎት ጋር እንዲጣጣምና የተግባር ስልጠናውም ከማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የማስተሳሰሩ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ከሆነ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የቅጅ መብት ጥሰትን ለመቆጣጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄደው የጋራ ጥረት የሚያበረታታ ውጤት ተገኝቷል። 

መንግሥት ባከናወናቸው ተግባራት የዋጋ ግሽበቱ ወደ 19 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገለጹ

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 6/2005 መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ባከናወናቸው ተግባራት ባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ ከ40 በመቶ ወደ 19 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ መስከረም 28 ቀን 2005 የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት በቀረበው የማሻሻያ ሞሽን ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ እንደገለጹት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር መንግሥት በገበያ ውስጥ ያለውን የገንዘብ መጠን በመቆጣጠር፣ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግና የንግድ ሥርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የዋጋ ግሽበቱ ዝቅ ብሏል። መንግሥት የሚያጋጥመውን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን የብሔራዊ ባንክ ብድር ሳይወስድ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድን በመሸጥ የበጀት ጉድለቱ ከ1 ነጥብ 2 በመቶ እንዳያልፍ ማድረጉን አብራርተዋል። መንግሥት በጅምላ ንግድ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ለማስወገድ ያካሄደው ጥናት በማጠናቀቁ የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ጥናቱ በዚህ ዓመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የዋጋ ግሽበቱን በመቆጣጠር ረገድ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑን በመገንዘብ ባለፈው ዓመት ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ምርጥ ዘርፍ ለአርሶ አደሮች እንዲሰራጭ መደረጉን ተናግረዋል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በተያዘው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ኃይለማርያም አመልክተዋል። እንዲ

Colorado State University’s(CSU) delegates

Image
Colorado State University’s(CSU) delegates продвижение сайтов Category:  News Published on Friday, 05 October 2012 15:55 Hits: 216 A team of 7 delegates from Colorado State University’s(CSU)Agricultural  Science College have convened here at Hawassa University’s  (HwU) Agricultural College  on 01/10 /2012 .According to Dr.Yibra, DeanHwU’s College of Agriculture, his College has started collaboration with CSUon small projects and now the aim of the delegates visit is to scale up this collaboration.   He noted that the new collaboration framework mainly focuses on teaching learning, capacity building, agricultural extension and research.  He added,they will have five days stay in his College and in their stay,introduction between schools and departments of the two sister colleges will be held;strategies will be developed on how and which area to work together to contribute to the development of Ethiopia ,and finally action plan/roadmap  will be prepared. Then,in a

ሃዋሳ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት

Image
ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) እንደመነሻ “አዳራሽ ተቀምጣ ስታበላ ሥጋ ስታጠጣ ጠጅ  ስዕል ትመስላለች የምኒሊክ ልጅ”        እንዲህ ሆነ፡-  ዕለተ እሁድ መስከረም 27 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ድንገት ብድግ ብዬ ወደ ሃዋሳ መረሽኩ፡፡ የሁለት ቅን እና ትንታግ ወጣቶች (መስከረም እና ፍፁም) ደግነት ነው ወደ ሃዋሣ ያንደረደረኝ፡፡ የእንዳልክና የፀሃይም ደግነት የጉድ ነው፡፡ እነሆ ሃዋሳን ለሁለተኛ ጊዜ ረገጥኳት፡፡ ድንቅ ከተማ ናት፡፡ አውራጎዳናዎቿ የተወለወሉ ይመስላሉ፡፡ አንድ ወጥ የሆነ መልክና ፋት አላቸው፡፡ እንደእኔ ዓይነቱን አልፎሂያጅ መንገደኛ “ሊያምታቱ” ይችላሉ፡፡ አቀያየሳቸውም አነጣጠፋቸውም ፍፁም ተመሳሳይ ለሆነ ወደሌላ ቦታ መሄድ ያሰበ ሰው ተጉዞ ተጉዞ ራሱን እዚያው የተነሳበት ቦታ ሊያገኘው ይችላል፡፡ ስለዚህ ከከተማዋ አንድ ጥግ ወደሌላ ጥግ መሄድ የፈለገ ሰው፣ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ቆም ብሎ እንደአሸን እየፈሉ ካሉት ትልልቅ ሕንፃዎች መሃል አንዱን በምልክትነት ማስተዋል አለበት፡፡ የሃዋሣ መንገዶች ፍፁማዊ አንድወጥነት አስገርሞኝ ዋዘኛ ጥያቄ የሰነዘርኩለት ወዳጄ “ሃዋሣ አዙሪት ነገር አለባት የሚባለው ለዚህ ነው” የሚል ምላሽ ነበር የሰጠኝ፡፡ የሆኖ ሆኖ ሃዋሳ አ/አበባን የምትስንቅ ፅዱና ውብ ከተማ ናት፡፡ ሙሉ ጽሁፉን እዚህ ላይ ያንቡ

ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን ማበረታቻ ነገ ይቀበላሉ

Image
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 5 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ነገ በኤድናሞል ህንጻ በሚከናወን ስነ ስርአት ይቀበላሉ።  የኢትዮጽያ ብሄራዊ ቡድን ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ከሆነ የተለያዩ ድርጀቶችና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ከነዚህ መሀልም የኤድናሞል ባለቤት አቶ ተክለብርሀን አምባዬ ፥ የብሄራዊ ቡድኑ የልምምድ ሜዳ በመገኘት ለእያንዳንዱ ተጫዋች ለመስጠት ቃል የገቡትን ፥ የ25 ሺህ ብር ሽልማት ነገ ከ5 ሰአት ጀምሮ በኤድናሞል በሚከናወነው ስነ ስርአት ያበረክታሉ።  በነገው እለት በሚከናወነው በዚህ የማበረታቻ ፕሮግራም ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ፥ ለቡድኑ አባላት በሙሉ የምሳ ግብዣ እንደሚደረግላቸው ባልደረባቸን አራያት ራያ ዘግባለች።  ድሉን ተከትሎ የሚድሮክ ባለቤት ሼክ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ ለብሄራዊ ቡድኑ በአጠቃላይ የአምስት ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።