ደኢህዴን የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላስጠበቀ ለሲዳማ ህዝብ ምኑ ነው?
( የሲዳማ ተወካዮች እነማናቸው ?) ካለፈው የቀጠለ ለመሆኑ በተለይ በዚህ ሳምንት ያወጡት የኣቋም መግለጫም ሆነ ወሳኔዎቹ በርግጥ የሲዳማን ህዝብ ይጠቅማሉ ? ወይስ የሲዳማን ህዝብ ጥቅም ባያስጠብቁም የደኢህዴን ፖሊስ ለማስፈጸም ያህል የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው ? ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት። ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ደኢህዴን የዛሬ ሶስት ወራት በፊት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ለማስተዳደር በምል ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ ከሰፊው የሲዳማ ህዝብ እጅ ቀድሞ ገብቶ ለእቅዳቸው ኣለመሳካት ለጊዜውም ብሆን ሳንካ ሆኗል። በጊዜው የክልል ባለስልጣናት ስለ የውይይት ጽሁፉ የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸው የምታወቅ ሲሆን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ቀርበው የበሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ህዝብ ለመዋሸት መሞከራቸው እንዲሁ የምታወስ ነው። በወቅቱም ብሆን ኣንዳንድ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮ እንዳሉት የክልሉ ባለስልጣናት በሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ያስወሩት የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር የመበረዝ ኣካሄድ ድርጅቱ ጊዜ ወስዶ ተዘጋጅቶበት መክሮ እና ዘክሮ ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ መሆኑን ነበር። ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት። ታዲያ ያን ጊዜ የሲዳማ ህዝብ ባሳየው ህዝባዊ ንቅናቄ ተደናግጠው ሀሳቡን ለማድበስበስ ጥረት ኣድርገው ህዝቡን በማረጋጋቱ ረገድ ተሳክቶላቸው ማለት ይቻላል። ነገር ግን የወቅቱ የሲዳማ ህዝብ