Posts

በመላ ሃገሪቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዩን መረጠ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኡላማዎች የፈትዋና ዳዕዋ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ። በምርጫው በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ከማለዳ  ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የክልል ከተሞች በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት፥ ይወክለናል ያሉትን እጩ ሀይማኖታዊ ስነ ሰርአቱ በሚያዘው መሰረት ሲመርጡ አርፍደዋል። በየምርጫ ጣቢያው 25 እጩዎች የተጠቆሙ ሲሆን ፥ ከመካከላቸው አብላጫ ድጋፍ ያገኙ 20ዎቹ የምክር ቤት አባላት ሆነዋል። አብላጫውን ድጋፍ ያገኙትና በከፍተኛ ድምጽ የተመረጡት አምስቱ የምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ በመሆን፤ የስራ ድርሻቸውን እዚያው በህዝቡ መካከል የስራ ድልድል በማድረግ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የእምነቱ ተከታዮችም በምርጫው ንቁ ተሳታፊ በመሆን ፥ ዕምነቱ የሚፈቅደውንና የአመራር ስርዓቱን  አጠናክረው ያስቀጥላሉ የሚሏቸውን እጩዎች ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ በሆነ መልኩ መርጠዋል። በምርጫው ወቅት የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ መራጮች በመመዝገብ የመረጡ ሲሆን ፥ የመራጩ ቁጥርም ከተጠበቀው በላይ እንደነበር ነው የምርጫ አስፈጻሚዎቹ የጠቆሙት። በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞችና በጅማ፣ በሃረር፣ በደሴ፣ በሻሸመኔ፣ በጎንደር እና በመቀሌ ሪፖርተሮቻችን በተዘዋወሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ፥  ያነጋገሯቸው ድምጽ ሰጭዎች አፍራሽ ሃይሎች ያደርጉት የነበረው ቅስቀሳና በምርጫው ወቅት ያዩት ነገር የተለያየና ፍጹም ሰላማዊ እንደነበር ነው የገለጹት። ተመራጮቹ የእስልምና ምክር ቤቶች አባላት የመረጣቸውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መራጮቹ የጠየቁ ሲሆን ፥ ተመራጮቹም የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በአላህ

አንድነት ፓርቲ የፕሬስ አፈና እንዲቆም ጠየቀ

የፓርቲው ልሳን ጋዜጣ ወደ መጽሔት ሊቀየር ነው መንግስት በፕሬስ ላይ የሚያደርሰው አፈና እንዲቆም ያሳሰበው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ከህትመት የታገዱት የፓርቲው ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” እና “ፍትህ“ ጋዜጣ ለህትመት እንዲበቁ ጠየቀ፡፡ የፓርቲው አመራሮች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፤ “ፍኖተ ነፃነት” ወደ ህትመት እንድትመለስና የፕሬስ አፈናው እንዲቆም ለጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ለመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ለአቶ በረከት ስምኦን እንዲሁም ለብሮድካስት እና ለብርሃንና ሰላም ማኔጂንግ ቦርድ ደብዳቤ ቢጽፉም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ ልሳን ጋዜጣው ፓርቲው አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን የሚያነቃበትና ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት ድልድይ እንደሆነ ጠቁሞ፤ መንግስት ይሄን ድልድይ ነው የናደው ብሏል፡፡ መንግስት ጋዜጣውን የዘጋው ሆን ብሎ ፓርቲውን ለማፍረስና በመጪው የአዲስ አበባ ማሟያ ምርጫ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ነው ሲልም አክሏል፡፡ የጋዜጣውን መታገድና የፕሬስ አፈናን በመቃወም በቅርቡ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ የገለፁት የፓርቲው አመራሮች፤ ህጋዊ ሠውነት ስላለን የሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄያችን ተቀባይነት ያገኛል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ ፈቃዱን ካላገኘን ግን የራሳችንን የትግል መንገድ እንከተላለን ብለዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የታገደውን ጋዜጣ ለመተካት ሁለት አፋጣኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ መወሰኑን ገልፀው፤ አንዱ ጋዜጣዋን ወደ መጽሔት በመቀየርና ከግል ማተሚያ ቤቶች ጋር በመነጋገር በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ ማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው ፓርቲው የራሱን  የማተሚያ ማሽን በመግዛት ጋዜጦችን እራሱ ለማተም ውሳኔ ላይ መድረሱንም አመልክቷል፡፡ http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&

አውስትራሊያ ለኢትዮጵያ የትምህርት ድጋፍ ታደርጋለች፤ የሲዳማ ልጆች የእድሉ ተጠቃሚ ሁኑ

Image
አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለችውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ አውስትራሊያ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ሊዛ ፊሊፔቶ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ፈጣን ልማት ማስቀጠል የሚችል ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማሰልጠን በኩል አገራቸው ቁርጠኛ አቋም አላት፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ በአምስት ዓመቱ ሀገራዊ ዕቅዷ ከፍተኛ ትኩረት ከሰጠቻቸው መካከል ትምህርት፣ ግብርና እና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ አቅሟን ለመገንባት አውስትራሊያ ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሯ ገልጸዋል፡፡ አውስትራሊያ በማዕድንና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም በውሃና በንጽህና አጠባበቅ ያላትን ልምድና የቴክኖሎጂ አቅም ተጠቅማ በመስኩ የኢትዮጵያን የሰው ኃይል አቅም ለማሳደግ ትሰራለች ብለዋል፡፡ አውስትራሊያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ለአፍሪካ ሀገራት እንደ የማስትሬትና ዶክትሬት ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠት የሚያስችላትን የምዝገባ መርሐ ግብር ከመስከረም ወር ጀምሮ እስከ መጪው ታኅሣሥ ወር ድረስ ክፍት ማድረጓን አስታ ውቃለች፡፡ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ የልማት ትብብር ኮርፖሬሽን ኃላፊ ፒተር ደንካን ጆንስ በበኩላቸው እንዳሉት የትምህርት ዕድሉ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች አቅም ከማጎልበት ባሻገር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡፡ የአውስትራሊያ መንግሥት የሰጠው ይኸው የትምህርት ዕድል ኢትዮጵያ ቅድሚያ ትኩረት በሰጠቻቸው የልማት መስኮች እንዲሆኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ምክክር የተደረገበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የሥልጠናው ትኩረትም በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና የምግብ ዋስትና፣ ባቡርና ም

የእስልምና ምክር ቤት ምርጫ ዛሬ ይካሄዳል

Image
-    ሁለቱም ምክር ቤቶች ክስ ቀርቦባቸዋል በታምሩ ጽጌ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አገር አቀፍ ምርጫ ዛሬ ይካሄዳል፡፡ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሙስሊሙን የሚመሩ የሃይማኖት መሪዎች ለመምረጥ በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ምርጫው እንደሚደረግ የኡላማዎች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ የሃይማኖት መሪዎቹ የምርጫ ጊዜ ማለፉን በመጥቀስና ሕዝቡ ያልመረጣቸው መሪዎች ሊወክሏቸው እንደማይችሉ ሲገልጹ የነበሩ ከ50 በላይ ተጠርጣሪዎች በእስር ላይ ናቸው፡፡ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄና ፊርማ መቋቋሙን የገለጸ 17 አባላት ያሉት ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት እንዲበተኑና ለምክር ቤቱ የሚደረገው ምርጫ በገለልተኛ አካል እንዲደረግ፣ ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ አቅርቧዋል፡፡ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 408 መሠረት ምክር ቤቱ የራሱ የሆነ የመመሥረቻና የመተዳደሪያ ደንብ ያለው መሆኑንና ከተጣሉበት ኃላፊነቶች መካከልም፣ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከሌላ እምነት ተከታዮችና ከመንግሥት ጋር እምነታቸውን በተመለከቱ ጉዳዮች ግንኙነቶችን ማስተባበር መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሥራ አመራሮች የሚሾሙት በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት በግልጽ በየአሥር ዓመቱ በሚደረግ ሕዝባዊ ምርጫ መሆኑን የሚገልጸው ክሱ፣ ተመራጩም ያለምንም አድልኦ የመረጠውን የኅብረተሰብ ክፍል ለማገልገል ግዴታ መግባቱን ያብራራል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ የሚገኘው ምክር ቤት በምርጫ ያልተሾመ ከመሆኑም በላይ፣ ሕግና ደንቡን በመተላለፍ ላለፉት 13 ዓመታት ምንም ዓይነት ምርጫ አለማድረጉን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ እየፈጸማቸው የሚገኙት ተግባሮች

በትናንትናው እለት በኣለታ ወንዶ ስለተካሄደው የመምህራን ጉባኤ በተመለከተ ከማህበራዊ መረብ የተገኘ ኣጭር መልዕክት

 የሲዳሚኛ መልዕክቱ የቀረበው በ Hawassa Dumme  ነው Bero barra (25/01/2005 M.D) sidaamu zoone Alata wondi woradi rosiisano ganmba assineena roosiisaanonke naaxisiisano coye coydhe fultino.Gamba assitino Yadigete borojje irreesite fultino.Baalu sidaami xa'mo disidaamu xa'mooti yiino manchi(Shuguxe) wirro sidaamu xa'mo ikkase lallawa geeshsha mittu gambooshshino hasiisanokita reqecci assite kultinonsa.Leddeno sidaamu daga sharro agurtanohu Hige-mangisteteni uyinoonsa qoosso baala higuro calla ikkinota kadde wortino. Sidaamu mannira ille ikkitinooni rosiisanonke ki'neni naaxineemo. kuni albaanino rosaanona rosiisano gobbate lophphora,gashshootu taalonyira assitino sharro dhaggete giddo lowo bayco afidhino. kuni daafira sharro ki'nete,ninketena dawaro higa hooguro ga'a daggano illamatena yitinante gede sharronke noo garini heedholla. Dandaami'ne garrini wole sidaami giddo noo rosu mina giddo rosiisano rosiisanono mitto afoo ikkitano gede qumi assa hasiisano. MITTI