Posts

አምባሳደር ብርሃነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ሞት ተከትሎ በተጠራው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ምክትላቸው የነበሩትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ወዲህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ክፍት ሆኖ የቆየ ሲሆን ለዚህም ሚኒስቴሩን ላለፉት ሁለት አመታት በሚኒስትር ደኤታነት ያገለገሉት አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደታጩ መመደባቸውን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ ሀገሪቱ የምትመራበትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በማርቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አምባሳደር ብርሃነ፤ ከሚኒስትር ደኤታነታቸው በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የተጓተቱ እቅዶችን ጨምሮ በተያዘለት ጊዜ ለማስፈፀም እንዲቻል በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራና ባለ ድርሻ ባለሙያዎች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቋመ፡፡ በተያያዘም አቶ ኃይለማርያም በቦርድ ሰብሳቢነት ይመሩት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ መሠጠቱንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በቅርቡ እንደሚቋቋም ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡  http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=2944:%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%88%B3%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%90-%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%88%8A%E1%88%86%E1%8A%9

በቅርብ ቀን ሲዳማ ውስጥ መከሰቱ ኣይቀርም

Image
የሲዳማ ህዝብ ለኣምባገነኖች ኣይምበረከክም!

The Sidama has no grievance with sisterly oppressed Nation(s)

Image
The Sidama has no grievance with sisterly oppressed Nation(s) Mulugeta B. Daye . Frustrated SPDM on Sidamas’ commitment to abide law of the land and keeping on the demand for regional autonomy in civilised manner, opted to pervert the course of justice.    The President of SNNPRS   forced   820 cadres to declare nine points, against the will and wish of the Sidama.  This distortion was transmitted on Ethiopian Television on 2, October 2012. Nine points can be analysed into three main categories. 1)        public confession for part of the 820 Sidamas, those who are  integrated to SPDM political system that marginalised 3.4 million Sidamas for either they  are  suspected ofsupporting , sympathising and joining the struggle for S idama’s quest for regional autonomy, that worried the president of SNNPRS who f elt left alone.   2) Reducing the demand of 3.4 million Sidamas’ for regional self-administration as the demand of internally:- parasites and rent see

የሲዳማ ክልል እውን ትሆናለች

ናት ሐመሶ በሲዳማ ህዝብ ላይ ሲዶልቱ፣ ሲያሴሩ፣ ሲሰልሉና በህዝባችን ላይ በደል ሲፈጽሙ የነበሩ ትላንትና በሂስ ግለሂስ ወቅት ተጋለጡ በሲዳማ ምክክር ፎረም (sidama dialogue forum) – ከዚህ ቀደም “የሲዳማ ታጋዮች ፎረም” ይባል የነበረው ነው፡፡ ሰሞኑን የደኢህዴን/ኢህአዴግ አመራሮችና ካድሬዎች (የሲዳማ ዘርፍ) ከያሉበት ተሰባስበው በሲዳማ ባህል አደራሽ ከተው ሲመክሩና ህዝባችንን ሲክዱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ስብሰባው የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት ሰኞ መስከረም 13/2005 ዓ/ም ሲሆን እስከ ትላንትናው ቀን ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ዘልቋል፡፡ ሽፈራውም በመኖሪያ ቤቱ በርካታ መንፈሳዊ አገልጋዮችንና መንፈሳዊ ሰዎችን ጠርቶና አስጠርቶ የምስጋና ጊዜ አዘጋጅቶ ቀኑን ሲያስብ የዋለው ቅዳሜ ቀን መስከረም 18/2005 ዓ/ም ነው፡፡ ይህ ቀን የተመረጠበት ምክንያት ግልጽ ነው - ከያሉበት አከባቢ ሁሉ የተሰባሰቡ ካድሬዎችን (እጅ ብቻ የሚያነሱ የማይናገሩና የራሳቸው የሆነ አቋምና ዓላማ የሌላቸው ሰው መሰል ፓርላማ ተብየ ፍጡራንን ጨምሮ) “ለሲዳማ ክልል አያስፈልገውም” በሚል ሀሳብ ዙሪያ እጅ አስነስቶ አስወስኖ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ይህ የክህደት ውሳኔ የተላለፈው “ከምስጋና ቀን” አንድ ቀን አስቀድሞ አርብ ለት  በ17/01/2005 ሲሆን ለምስጋና ፕሮግራም ቅዳሜ የተመረጠውም ለዚህ ነው፡፡ በርግጥ ይገባዋል፤ የሲዳማ ህዝብ ሁሉ “ደኢህዴንም ሆነ አንተ አትወክለንም፤ አንተ ከስልጣን ውረድ…” ብሎ በአንድ ሀሳብ ካወገዘውና የጫምባላላ ታዳሚ ሁሉ በረገመውና በሰደበው ማግስት ካድሬውን መልሶ ማሳመን ከቻለ ለርሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በርግጥ ስብዕና ቢኖረው ኖሮ ከዛ ሁሉ ውርደት በኋላ ሀገር ጥሎ በጠፋ ነበር፡፡ ቢሰደብ የሚዋረድ ስብዕና ስለለሌው ግን እንኳ

የሞዴል ትምህርት ቤቶችን ቁጥር በማበራከት በትምህርት ተደራሽነት ላይ የተገኘውን ውጤት በትምህርት ጥራትም ላይ ለመድገም እየሠራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የማልጋ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በወረዳው 6ቱንም የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችንና ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን በአግባቡ በማከናወን የሞዴልነት ማዕከል የሆነው የማልጋ የመጀመሪያ ሳይክል 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተሞክሮን ሌሎችም እንዲቀስሙ የልምድ ልውውጥ ኘሮግራም አካሂዷል፡፡ በዚህም ወቅት የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ሻላሞ እንዳሉት ጥራቱ በተጠበቀ ትምህርት የተቀረፀ ዜጋና የልማት ሠራዊት ለማፍራት በወረዳው የተጠናከረ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በ2ዐዐ4 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ከ86ዐ በላይ ተማዎች 9ዐ በመቶ በላይ የሚሆኑ ፈተናውን ማለፋቸውንና ይህም ከቀደሙት ዓመታት 49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ አላካ በበኩላቸው በተገኘውን ውጤት አጠናክረን ካስቀጠልን በታላቁና በባለራዕዩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተነደፈውን የትምህርት ፖሊሲ አጭር መንገድ ተጉዘን እናሳካለን ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋሁን በየነ 2ዐ የ1 ለ5 አደረጃጀቶችን በመጠቀም ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ገልፀው ተማሪዎችም ኩረጃን ሙሉ በሙሉ እንዲፀየፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ ላስመዘገበው ውጤት የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት መስጠቱንና የትምህርት ቤቱ እሴቱ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎች በታዳሚዎች መጎብኘቱን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/16MesTextN405.html