በቅርቡ ከእስር ቤት ወደ ሆስፒታል ስወሰዱ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የመኪና ግጭት ኣደጋ ደርሶባቸው የነበሩት ካላ ዱካሌ ላሚሶ
በኣደጋ ምክንያት በግንባራቸው ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ፎቶውን ኣጉልተው ይመልከቱ የ 55 ዓመት እድሜ ባለበት የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት በማረሚያ ቤት ሆነው በስኳርና የደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት ካላ ዱካሌ ላሚሶ ፣ በነሐሴ 10/2004 ዓ . ም ከስራ ቦታቸው ታፍነው እስር ቤት የተወረወሩት፣ እስከዛሬ መስከረም 15/2005 ዓ . ም ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት እና ለሲዳማ ሕዝብ መብት ሕይወታቸውን ሙሉ ሲታገሉ የኖሩ፣በግብርና ዘርፍ ማስተርሳቸውን በእንግሊዝ ሀገር በ 1980 ዎቹ ያገኙት አቶ ዱካሌ ላሚሶ መስከረም 14/2005 ዓ . ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በቴክኒክና ሞያ ት / ቤት አካባቢ ከወህኒ ቤት በፖሊስ ታጅበው ለደም ግፊት ህክምና ወደ ሃዋሳ ሬፈራል ሆስፒታል ሄደው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተጫኑበት ባጃጅ ጭምር ታርጋ በሌለው መኪና ተገጭተው 4 ሜትር በሚረዝመው የአስፋልት ጠርዝ ገደል ውስጥ ጥለዋቸው ለጊዜው ተሰውረዋል፡፡በዚህም አደጋው በደረሰበት አካባቢ ህብረተሰብ ርብርብ ሕይወታቸው የተረፈ ሲሆን ታርጋ የሌለው ተሸከርካሪም ለጊዜው ተሰውሯል፡፡