የፖለቲካ ባህላችንን እንፈትሽ
በበላይ ዓለሙ ይህችን አጭር ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጳጉሜን 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ማታ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ የተላለፈው የአቶ ተስፋዬ ሐቢሶና የቅንጅት አባል የሆኑ ግለሰብ ውይይት ነው፡፡ ከጳጉሜን 3 ቀን በፊት ሁለት ግለሰቦች ያደረጉት ውይይት ካለ አልሰማሁምና አስተያየት መስጠት አልችልም፡፡ በዕለቱ በተደረገው ውይይት ሁለት ተፃራሪ ስሜቶች ናቸው የተሰሙኝ፡፡ አንደኛው መልካም ስሜት ሲሆን፣ ሌላኛው ግን ተቃዋሚዎቻችን እነዚህ ናቸው? እነዚህ ናቸው የአገራችን ተስፋዎች? የሚል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ነው፡፡ በእርግጥ የቅንጅቱ አባል የተናገሩት የግል አቋማቸውን ይሁን የድርጅታቸውን መለየት ቢያስቸግርም፣ የሳቸውን የሚመስል ተመሳሳይ አቋም ከሌሎችም አንቱ ከተሰኙ ተቃዋሚዎች የሰማሁ ስለሆነ፣ የድርጅቱ አቋም ሊሆን ይችላል የሚል ኃይለኛ ጥርጣሬ ጭሮብኛል፡፡ የምሽቱ ውይይት ያተኮረው በቅርቡ በሞት የተለዩንን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን አመራርን በተመለከተ ነበር፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ዜናዊን የሚያደንቋቸው ብዙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች እንዳሉ ሁሉ፣ በኃይለኛ የሚነቅፏቸውም በርካቶች ናቸው፡፡ በእነዚህ ሁለት ጽንፎች መሀል ያሉም አሉ፡፡ በምሽቱ በተደረገው ውይይት አቶ ተስፋዬ የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ ሳይሆኑ ስለ አቶ መለስ የሰጡት አስተያየት እጅግ አስደምሞኛል፡፡ በአንፃሩ የቅንጅት አባሉ የሰጡት አስተያየት እኚህ ሰው በእውነት የኢትዮጵያን ሁኔታ የተረዱ ሰው ናቸው ወይ? በእንደዚህ ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት ነው ወይ አገርን መምራትና ሕዝብን ማሰለፍ የሚቻለው? አስብሎኛል፡፡ የጠራ የፖለቲካ መስመር ተጨባጩን አገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን በትክክል ከመገንዘብ ስለሚመነጭ፣ ምን ዓይነት መስመር ይሆን እነዚህ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚቀ