Posts

መረጃ:- የግልጽነትና የተጠያቂነት ቁልፍ መሳሪያ

ከኢፌዲሪ ህገ- መንግስት አምስት መሰረታዊ መርሆዎች ውስጥ የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት አንዱ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ በመንግስት ሀላፊዎች የሚወሰዱ ውሳኔዎችና የስራ እቅስቃሴዎች ለህዝቡ ግልጽ መሆናቸውንና ህዝቡም ይህንን በተመለከተ ያሉትን መረጃዎች ለማግኘት ያለውን መብት የሚያረጋግጥ መርህ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የዲሞክራሲ ዋልታ በመሆኑም ከመርሁ ተግባራዊነት ውጪ ዲሞክራሲን ማስፈን የማይታሰብ ነው፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት ትልቁን ድርሻ የሚይዘውን የህዝቦች ተሳትፎና የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥም ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግስት አሰራርን እውን ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ዜጎች በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና የመንግስት ሀላፊዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ለመመርመር ተገቢውን መረጃ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ግልጽነትም ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ለተጠያቂነትም እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጣል፡፡ በመሆኑም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የህዝቦችን ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ዜጎች መረጃ የመጠየቅ፣ የማግኘትና የማስተላለፍ መብታቸው መከበሩ አንድም ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ ሌላም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን በመተግበር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው፡፡፡ ዜጎች መረጃ ለማግኘት በራሳቸው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በመፈለግና ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግም የመገናኛ ብዙሀን ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 የመደንገጉ ምክንያትም የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብትንና የመገ

በቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2005  (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀድሞውን የሀዋሳ ከንቲባ ጨምሮ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ በነበሩ የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች በተከሰሱበት በእነ አቶ እንድርያስ ኦሌሳ መዝገብ የተለያዩ ትአዛዞችን አስተላለፈ፡፡  ከመሬት ጋር በተያያዘ ያልተገባ ጥቅም ለራሳቸውና ለቤተሰቦቿቸው ለማስገኘት በማሰብ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የተከሰሱት እነዚሁ የከተማዋ አስተዳደር የተለያዩ ሃላፊዎች የፍርድ ሂደት የሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲመለከተው ቢቆይም በነጻ አሰናብቷቸው ነበር፡፡ የከልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ማየት ከጀመረ በኋላ ግን ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ያልቻሉትን 1ኛ ተከሳሽ እንድሪስ አሎሳና 2ኛ ተከሳሽ ጉደታ ጎምቢ በፖሊስ ተፈልገው ሊገኙ ስላልቻሉ ስማቸውና ምስላቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ እንዲፈለጉ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዚሁ መዝገብ የተከሰሱ የሌሎች 4 ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነብዩ ይርጋአለም ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26121&K=

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ579 ሚልዮን ብር ግንባታ አጠናቀቀ

Image
አዋሳ መስከረም 18/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በ579 ሚልዮን ብር የጀመረው የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በ2 ቢልዮን 460 ሚልዮን ብር ወጪ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡፡ የዩኒቨርስቲው የቢዝነስና ዲቨሎፕመንት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጋቱ ረጋሳ ከትናንት በስቲያ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በዩነቨርስቲው ሜዲካልና ይርጋዓለም ካምፓሶች እንዲሁም በዋናው ግቢና ግብርናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች ከአንድ አመት በፊት የተጀመሩት አዳዲስ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀዋል፡፡ ከተጠናቀቀው ፕሮጀክቶች መካከል በተለምዶ ኋይት ሀውስ የሚባለው የተማሪዎች ማደሪያ ፣ የመማሪያ ክፍሎች ቤተ መፃህፍት፣የአስተዳደርና የመምህራን ቢሮዎች ጨምሮ ሌሎችም ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ መገልጋያዎች እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡ በሜዲካልና በይርጋለም ካምፓስ ብቻ በእያንዳንዳቸው 780 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስማር የሚያስችሉ መሆናቸውን አመልከተው የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ እየተዘጋጁ ናቸው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሰቲው በ460 ሚልዮን ብር ወጪ ባለፈው ዓመት ግንባታው ያስጀመረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አምስት ትላልቅ ዶርሚቴሪዎች በመያዝ እያንዳንዱ ዶርሚተሪ 780 ተማሪዎች ለማስተናገድ የሚያስችሉ ህንፃዎች ማካተቱን ተናግረዋል፡፡ በሁለት ሀገር በቀል ተቋራጮች የሚካሄደው የቴክኖሎጂ እንስቲትዩት 145 የመማሪያ ክፍሎች በተጨማሪ የአስተዳደር ቢሮዎች እና ሌሎችም ዲፓርትመንቶች ያካተተ ግዙፍ ህንፃ መሆኑን ከሁለት ዓመት በኋላ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ አስታውቀዋል፡፡ የቴክኖሎጂ እንስቲትዩቱ የሚ

ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕጎችን በሦስት ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተመውን ሰነድ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረከበ፤ በሲዳማ ኣፎ መቼ ነው መሰል ሰነዶች መቶርጎም የምጀምሩት?

Image
አዲስ አበባ መስከረም 15/2005 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች፣ ስምምነቶችና መርሆዎችን በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተመውን ሰነድ ዛሬ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረከበ። ኮሚሽኑ በሁለት ሚሊዮን ብር ወጪ ያሳተማቸውን 35 ሺህ "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች አስረክበዋል። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዳራሽ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አምባሳደር ጥሩነህ ዜና እንደገለጹት አገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች፣ ስምምነቶችና መርሆዎች በሰብአዊ መብት ማስከበር ተግባር ላይ ሳይውሉ ቆይተዋል። እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜያት ሳይተረጎሙ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል። ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህጎቹን ወደተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ዳኞች እና ዐቃቤ ሕጎች ከአገሪቱ ሕጎች ጋር አቀናጅተው እንዲጠቀሙባቸው ማሳተሙን አስረድተዋል። በአገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ዳኞች እና ዐቃቤ ሕጎች "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነድ በሥራ ላይ በማዋል ሊጠቀሙበት እንደሚገባም ገልጸዋል። እንዲሁም ለፌዴራልና ለክልል ሕግ አውጪ አካላት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ለሚሰሩ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች "የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች" ሰነዱን ለማሰራጨት የሚያስችል ስትራቴጂ የተነደፈ መሆኑን

ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት በብቃት ማነስ ተገምግመው ኣይደለም፤ ኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ

Image
የኢትዮጵያ ኣምባሳደር በጃፓን፤ ኣውስትራልያ፤ በኒውዝይላንድ እና በፓፓ ኔው ጊኒያ ኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ሪቄ Markos Tekle Rike, Ethiopian Ambassador responsible for Japan, Australia, New Zealand and Papua New Guinea, talks about the leadership ability of newly elected PM Haile Mariam Desalegn and Ethiopia's future direction. The ruling party council of the Ethiopian Peoples' Revolutionary Front (EPRDF) elected last weekend the former Deputy Prime Minister and Foreign Minster Haile Mariam Desalegn as Chairman of the Front. Desalegn who assumed the position of Prime Minster of Ethiopia is to be endorsed by the parliament in the coming weeks.