ቀይ መብራት --የሃይለማርያም ደሳለኝን እና የደመቀ መኮንን የተደበቀ ታሪክ
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ክልል በነበሩበት ጊዜ የራሳቸውን የብሔረሰብ አካላት ወደ ስልጣን የመሰብሰብ ስራ ሲሰሩ ከሲዳማ ማህበረሰብ በኩል ለምን እኛስ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም ለዚሀ የሰጡት መልስ “ከእናንተ የተማረ ማህበረሰብ ስለሌለ ነው ካቢኔውን በተማረ ማህበረሰብ ያዋቀርኩት” የሚል መልስ ነበር (አንድ አድርገን መስከረም 10 2005 ዓ/ም)፡- አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ እና የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አቶ ደመቀ መኮንን የትምህርት ሚኒስትር ፤ አቶ ሶፊያን አህመድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ፤ እነዚህ በስም የተዘረዘሩት ሶስት ከፍተኛ የሀገሪቱ ቱባ ባለስልጣናት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በህይወት በተለዩበት ወቅት የኢህአዴግ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለውድድር ያቀረባቸው ሰዎች ናቸው ፡፡ ፓርቲው ባደረገው ምርጫ መሰረት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር ፤አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መሾሙ የሚታወቅ ነው ፤ በቂ ድምጽ ያላገኙት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የተጠቆሙት አቶ ሶፍያን አህመድ በሶስተኝነት ወደ ኃላ ቀርተዋል ፤ ነገ 11/01/2005 ዓ.ም ፓርላማው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ድምጽ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል ፤ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ሶፍያ አህመድ ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ናቸው ፤ በመሰረቱ ደመቀ መኮንን ብሎ የእስልምና እምነት ተከታይ ይኖራል ብለው ሰዎች ላያስቡ ይችላሉ ፤ አቶ ደመቀም ከወደ ወሎ መሆናቸው ሰዎች ይናገራሉ ፤ አሁን እኛን ያሳሰበን ነገር የኢህአዴግ የፓርቲ ምርጫ አይደለም ፤ የነዚህ ሰዎ