ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል::
ቀን፡-11/01/2005 ቁጥር፡-ድሩ ቄለ01/2005 ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፓብልክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አዲስ አበባ ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል:: ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ ፌ/ዴ/ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ የበላይ ህግ ያጎናፀፋቸው መብቶች በሰላማዊ አሰራር የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይደነግጋል፡፡ ይህ ህገ-መንግስት እንደገና በአንቀጽ 8 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡ ይሄ ሕገ-መንግሰት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን ፣ክራይ ሰብሳብነትንና ምግባረ-ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር ተያይዘው ሕዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝቡን ብሶት የሚቀሰቅሱ አጀንዳዎችን አንስተው በሕዝቡ መካከል በመዛት ያንኑ መልሰው ለመሸንገል በሚል አጀንዳ የመንግስትን ታአማንነት ለማግኘት ስሉ የመንግስትን ውስን ሀብት ለማባከን ላይ ታች ሲሉና የሥልጣን ዕድሜ ሲያራዝሙ ቆይተዋል፡፡ በዚህም መነሻ ህገ-መንግስቱ ለሲዳማ ህዝብ ካጎናፀፈለት መብቶች አንዱ የሆነውን ባህሉን ለማሳደግ የፍቼ-ጫምባላላ በዓል ስያከብር እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡በነቂስ የሚወጣው ህዝብም በዝህ በዓል እንደባህሉ የሚወደውን አወድሶ፣ያልተመቻቸውንና ህጋዊነቱን ያጎደለውን ነገር ወቅሶ በሰላም ወደቤቱ ይመለሳል፡፡በነሐሴ 8