ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የግብርና ምርምር የጥራት ላቦራቶሪ ተከፈተ
አዲስ አበባ መስከረም 12/2005/ዋኢማ/ -የግብርና ምርምር የጥራት ላቦራቶሪ ኢትዮጵያ በግብርና ምርቷ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋት የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው አስታወቁ። � ሚኒስትሩ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤት ቅጽር ግቢ በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጀውን ላቦራቶሪ ትናንት መርቀው ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ላቦራቶሪው ግብርናውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያሸጋግርና የሀገራችንን ግብርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥራት መስፈርት እውቅና ለማግኘት የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው። ላቦራቶሪው አርሶ አደሩንም ሆነ አርብቶ አደሩን እንዲሁም መላ ሀገሪቱን ተጠቃሚ ያደርጋል። ይህም የግብርና ዕድገት ያፋጥናል። � እንደ አቶ ተፈራ ገለጻ፤ ኢንስቲትዩቱ የሀገሪቱ የግብርና ምርት እንዲያደግ አዳዲስ ዝርያዎችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ላቦራቶሪውም ለቀጣይ እድገቱ አስተዋጽኦ በእጅጉ የጐላ ነው። ለግብርናው ዘርፍ እድገት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በዘርፉ የተቀመጠው ግብ ስኬታማ ይሆን ዘንድ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ጀኔራል ዶክተር ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ላቦራቶሪው በግብርናው ዘርፍ ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። የሀገሪቱንም እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የምርቶችን የጥራት መስፈርት ማሟላት አጠያያቂ አይደለም። ለምርት ጥራት መረጋገጥ ደግሞ ላቦራቶሪው ዓይነተኛ ሚና አለው። ላቦራቶሪው በስድስት ወራት ውስጥም ዓለም አቀፍ እውቅና እንደሚያገኝ ጠቁመው፤ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚያገኛው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትም ጭምር መሆኑን አስረድተዋል። � እንደዶክተር ሰለሞን ገለፃ፤ የአርሶ አደሩን የተመራማሪዎችን ብሎ