ኢህአዴግ “የፓርቲውን ሊ/መንበር በምስጢር መያዝ ባህሌ ነው!” እንዳይለን
“የስዊድን ጋዜጠኞችስ ተፈቱ! የእኛስ?” (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛ) “ጠ/ሚኒስትር ለመሾም ምህላ እንጂ ስብሰባ ምን ይሰራል?” (ሽማግሌ ጐረቤቴ) አዲስ ዓመት እንዴት ነበር? (ከዋጋ ንረቱ ውጭ ማለቴ ነው) እኔ የምለው … ለአውዳመቱ በግ ስንት እንደገባ ሰማችሁ አይደል? … በግ ነጋዴውን ጠጋ ብላችሁ ስትጠይቁት ምን ይላችኋል መሰላችሁ? “24 ውሰደው!” ግራ ይገባችሁና “ምንድነው የምትለው?” ስትሉት “ሰምተሃል!” ብሎ ሊያሾፍባችሁ ይሞክራል፡፡ (“ሼፉ” ፊልም ላይ እንዳለችው ገፀባህርይ) “አትሸጥም እንዴ?” ትሉታላችሁ ኮስተር ብላችሁ! “በቃ ከ23 ውሰደው!” ይላችኋል - ፍርጥም ብሎ፡፡ ምን ማለት መሰላችሁ? 2300 ብር ማለቱ ነው፡፡ ይታያችሁ … አንድ በግ በ2300 ብር! ለነገሩ በጉ እንኳን ሊቀር ይችላል፡፡ የማይቀረው ምን መሰላችሁ? የጤፉ ነገር ነው፡፡ ጤፉ ሊቀር ይችላል የሚባል አይደለም (አበሻ ምን ሊበላ?) በአሁኑ አካሄድ ግን ለእነ ጤፍ ምትክ ካልፈጠርንላቸው የምንከርም አልመሰለኝም! ከእነሩዝ ጋር ዝምድና ብንፈጥር ነው የሚሻለን፡፡ (የቻይና ደጀ-ጠኚ አደረግኸን ካላላችሁኝ በቀር) መቼም ጤፍ ተወደደ ብለን የረሃብ አድማ አናደርግም! ሳንነጋገር እየራበን? የምን አድማ! ይሄን ፅሁፍ እያጠናቀርኩኝ ሳለ በኢቴቪ “ሥነፆታ” በተባለ ፕሮግራም በዓሉን አስመልክቶ ተሞክሮአቸውን የሚያጋሩ ዘመናዊ ባልና ሚስት ቀርበው ነበር፡፡ ሚስት ሲናገሩ፤ ዳቦውንም ጠላውንም ራሳችን ካላዘጋጀነው ልንል አይገባንም፤ ሲሉ በሰጡት ምክራዊ አስተያየት “እኛ ለምሳሌ ዳቦ አንጋግርም… outsource ነው የምናደርገው… ለሌላው ሰው የሥራ እድል መፍጠር አለብን” ብለዋል፡፡ (ውጭ አስጋግረን ነው የምናመጣው ማለታቸው መሰለኝ) ያለው ማማሩ አሉ! ዕድሜ ለNGO! ያልፈጠረልን ቃል