ሀገሪቱን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ይመሯታል ተባለ
New ኢሳት ዜና:-በመስከረም ወር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በሚያካሂደው ምርጫ የሚመረጠው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ድርጅቱን ለስድስት ወራት ብቻ በጋራ እንደሚመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡ አቶ ሬድዋን ዛሬ ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ ቀጣዩ ጉባዔ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል በሚለው መሰረት ቀጣዩ ጉባዔ ከስድስት ወራት በኃላ እንደሚካሄድ ጠቁመው እስከዚያ ከአራቱም አባል ድርጅቶች 45 ሰዎች በድምሩ 180 አባላት የተወከሉበት የግንባሩ ም/ቤት በተጓደሉት አባላት ምትክ ግንባሩን “በጋራ የሚመሩ” ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ይመርጣል ብለዋል፡፡ “ከስድስት ወራት በኃላ የግንባሩ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀመንበሩና ምክትል ሊቀመንበሩ ብቻ ሳይሆን የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ሥልጣናቸውን ያስረክባሉ፡፡ከማንኛውም አባል ጋር ወርዶና የጉባዔው አባል ሆኖ ከተመረጠ ይመረጣል፡፡እስከዚያው ግን የሊቀመንበርነት ቦታ ተጓድሎአል፡፡ተጓደለውን ቦታ የሚመርጠው ጉባዔው ሳይሆን ምክርቤቱ በመሆኑ በዚሁ መሰረት በመስከረም ወር ይመርጣል፡፡ቀጣይ ስድስት ወር ሲሞላ አዲሱ ሊቀመንበር ሌላ የጉባዔ አባላት ይሆኑና እንደገና ምርጫ ተደርጎ የሚመረጡ ከሆነ ይመረጣሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የሰሞኑ ጉባዔ ስላሳለፈው ውሳኔ ተጠይቀው በሰጡት ምላሸ “…የሁልጊዜም የድርጅቱ መሰረታዊ እምነት ሕዝቡን ወደተሻለ ደረጃ በመውሰድ ላይ ያነጣጠረ ፣የህዝቡን ሕይወት በመቀየር ላይ ያነጣጠረ፣የሕዝቡን ሕይወት በመቀየር መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ በሃገሪቱ ለማምጣት መሰዋዕትነት መክፈል ላይ ያተኮረ ነው፡፡በመሆኑም