ኢህአዴግ በአዲሱ ዓመት ያሞላቅቀን!
“የፓርቲዬ ባህል አይፈቅድልኝም” የሚል ሰበብ አንቀበልም! በሀዘን ክፉኛ የጨፈገገንን ደባሪ ዓመት ዛሬ እንሸኘዋለን - እንዲህ ያለ ዓመት ተመልሶ እንዳይመጣ እየተመኘን (ኧረ ፀሎትና ምህላም ያስፈልገዋል!) ግን በ2004 ምን መዓት ነው የወረደው? ብቻ በዚሁ በቃችሁ ይበለን! አሁን ወደ ዕለቱ ወጋችን ልመልሳችሁ፡፡በዛሬዋ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ሆኜ ምን እንዳማረኝ ታውቃላችሁ? በቃ … መሞላቀቅ፡፡ ግን ደግሞ በወላጅ ወይም በአያት አሊያም በፍቅረኛ አይደለም፡፡ እኔ መሞላቀቅ ያማረኝ በገዢው ፓርቲ ነው፡፡ (አሞላቆን ስለማያውቅ ይሆን?) በርግጥ ይሄ ጥያቄ የእኔ ብቻ አይደለም - የህዝብ ነው፡፡ ማስረጃ ካስፈለገም ፒቲሽን አሰባስቤአለሁ፡፡ እናም ኢህአዴግ እስኪበቃን ድረስ እንዲያሞላቅቀን እፈልጋለሁ፡፡ እየቀለድኩ እንዳይመስላችሁ… ከምሬ ነው፡፡ በቃ በአዲሱ ዓመት ሙልቅቅ ማለት አምሮኛል፡፡ እንደ ቦሌ ልጆች! እኔ የምለው… ኢህአዴግ እኛን ማሞላቀቅ ያቅተዋል እንዴ? ኧረ አያቅተውም፡፡ ዋናው ነገር የልብ መሻት ነው (When there is a will, there is a way እንዲል ፈረንጅ) መቼም አውራ ፓርቲያችን ሰበብ አያጣምና “የፓርቲያችን ባህል፤ ማሞላቀቅ አይፈቅድም” ሊለኝ ይችላል (አልሰማሁም እለዋለኋ!) እርግጥ በኢህአዴግ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መሞላቀቅ” የሚል ቃል ላይኖር ይችላል፡፡ ግን ደግሞ የህዝብ ጥያቄ ነው እያልኩት ነው (የህዝብ አጋር ነኝ ይል የለ!) ለህዝብ ጥቅም ሲል ይቸገራ! (ለህዝብ ጥቅም እያለ ስንት ነገር ያደርጋል እኮ) ደሞ እኮ 21 ዓመት ሙሉ ለገዛው ህዝብ ከዚህም በላይ ቢያደርግ አይቆጭም (ገና 30 እና 40 ዓመት ሊገዛን ያስብ የለ!) ስለዚህ ሰበብ መደርደሩን ትቶ ጭክን ብሎ ያሞላቀን - በአዲሱ ዓመት! እንዴት ነው የሚያሞላ