Posts

በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ 283 የሚሆኑ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጅ ለእረፈት የመጡ ወጣቶች የጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ማሳተፋቸውን የወረዳው ወጣቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ::

በጽህፈት ቤቱ ወጣቶችን የማብቃት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መኮንን ዋይሶ እንደገለፁት ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰማሩት  ወጣቶች በችግኝ ተከላ ፣ በጤና፣ በከተማ ፅዳት ፣ በማጠናከሪያ ትምህትና በተለያዩ ዘርፎች  ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ የወጣቶችን አቅም ለማጎልበት ጽህፈት ቤቱ  የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ከሚገኙት መካከል ደምረው ደሹሬና ታመሩ ኤልያስ የእረፍት ጊዜያቸውን ሌሎችን በሚጠቅም ተግባር ላይ ማዋላቸው እንደሚያስደስታቸው ተናግረዋል፡፡ ትምህርቱን ከሚከታተሉት ተማሪዎች መካከል ያሬድ ገነሞ ከበጎ ፈቃደኞቹ እያገኘ ያለው ትምህርት ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ውጤታማ እንደሚያደርገው መናገሩን ቁምነገር ቦጋለ ዘግቧል፡፡

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተማርነውን ለህዝብና ለሀገር መስዋዕትነት የሚያስከፍለውን ጠንካራ የሥራ መንፈስ በመከተል ከሚጠበቅብን የሥራ ግዴታ በላይ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉ በሲዳማ ዞን ማልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ::

ነዋሪዎች እንዳሉት ድህነትን በልማት ለማሸነፍ የክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተሩን ራዕይ በልባችን ይዘን በአዲስ የሥራ ባህል መታነፅ ጀምረናል ብለዋል፡፡ አንዳንድ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስተሩ የነደፉትን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂን ተከትለው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የድካማቸው ውጤት ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ ሲታወሱ እንዲኖሩ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት አባቶችም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ምክንያት የደረሰብን ሀዘን የከፋ  ቢሆንም የተሰማን ቁጭት ዓላማቸውንና ራዕያቸውን ለማሳካት ብርታት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/29NehTextN204.html

የኢህአዴግ ምክር ቤት በመስከረም ወር ሊቀ መንበሩን ይመርጣል

Image
አዲስ አበባ ነሃሴ 30/2004 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትናንት ማምሻውን ተጠናቀቀ። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የህዝቡን መነሳሳትና ለፓርቲው የሰጠውን አደራ ገምግሞ በታላቁ መሪ በሳል አመራርና በኢህአዴግ የተነደፈውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በከፍተኛ ርብርብ ለማሳካት ውሳኔ አሳልፏል። የህዝቡን ተነሳሽነትም የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶችን በመደገፍ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየርና የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በበለጠ ግለት ለማስቀጠልም ወስኗል። በገጠር በተፋሰስ ልማት፣ በመስኖና በተለያዩ የውኃ አሰባሰብ ዘዴዎች እንዲሁም በዘመናዊ የግብዓት አቅርቦትና የሙሉ ፓኬጅ አጠቃቀም ዙሪያ አርሶ አደሩን በማሳተፍና በመደገፍ የገጠር ልማት ሥራዎችን፣ የአርሶ አደሩን ምርታማነትና ተጠቃሚነት በከፍተኛ ፍጥነት ለማስቀጠል አጽንኦት ሰጥቶም መክሯል። በከተሞች የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመረውን የጥቃቅንና አነስተኛ ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማስፋት በመረባረብ እንዲሁም በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸውን የባቡር፣ የኢንዱስትሪዎችና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጨምሮ ሌሎች የኃይል ማመንጫ ተቋማት ግንባታዎችን ለማስቀጠል ሰፊ ምክክር አድርጓል። በተለይ መልካም አስተዳደርን ለማሻሻልና በራሱ ተሳትፎ የህዝቡን አደራ በብቃት ለመወጣት በሚቻልባቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ አጽንኦት ሰጥቶ መክሯል። ኮሚቴው የመንግሥትን የገቢ አቅም የማጠናከር፣ ቁጠባና ኢንቨስትመንትን የማበረታታት፣ የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠር፣ የኤክስፖርት ገቢን የማሳደግ፣ ልማታዊ የግል ዘርፍን የማጎልበት ሥራዎችን አፈጻጸም በተመለከተ እስካሁን ያሉበትን ሁኔታዎች የቃኘ ሲሆን፣

ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ

የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚ ማክሰኞ፣ መሰከረም 4፣ 2012 ተሰብስቦ ውሎአል። ስብሰባውን ባለማጠናቀቁም ዛሬ መስከረም 5 ቀጥሎ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ። የስራአስፈፃሚው አባላት በጥቅሉ 36 ሲሆኑ፣ በመለስ መሞት ምክንያት ተሰብሳቢዎቹ 35 ናቸው።     ህወሃትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት 8 ሰዎች፣ ፀጋይ በርሄ፣ አባይ ወልዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ደብረፅዮን፣ በየነ እና አዜብ መስፍን ሲሆኑ፣ ነባሮቹ እና አንጋፋዎቹ የህወሃት  አመራር  አባላት ከስብሰባው ውጭ በመሆናቸው ኢህአዴግ በብአዴን እጅ ላይ መውደቁ ይነገራል። ከብአዴን በረከት ስምኦን እና አዲሱ ሲገኙ  ከኦሮሚያና ከደቡብ ግርማ ብሩ እና ሬድዋን ሁሴን  ተገኝተዋል።  8ቱ የህወሃት አባላት መለስን የሚተካ አንድ ሰው ወደ ስብሰባው ለመጨመር ጠይቀው  የአመራሩ አባላት አሰራሩን በመጥቀስ ሳይፈቅዱላቸው ቀርተዋል።  ትናንት በዋለው ስብሰባ ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ሊደርሱ ባለመቻላቸው፣ አጀንዳቸውን ለማሳደር ተገደዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የስራአስፈፃሚው ስብሰባ ላይ መሳተፍ ያልቻሉት አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ድርድር ጠይቀዋል። እነዚህም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ኡቅባይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ ስብሃት ነጋ እና ሳሞራ የኑስ ናቸው። አከራካሪው አጀንዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የምክትሉ ሹመት ጉዳይ ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታም እንዲሁ እያወዛገበ ይገኛል።  http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/09/blog-post_4779.html?spref=fb

የሲዳማ ቋንቋ ትምህርት ደረጃ ኣንድ

Image
Tutorial for Sidama language level one course. To fully benefit from this tutorial, you have to visit " Sidama Language Level One (WIKI page)