Posts

ዕውቀት እንረዳለን

Image
አራተኛ   ክፍል   እያለሁ   የሂሳብ   መጽሐፍ   ለአራት   ነበር   የሚታደለን፡፡   ታድያ   የቤት   ሥራ   የተሰጠ   ቀን መጽሐፉን   ለመውሰድ   ተረኞች   ያልነበርነው   ሦስታችን   የቤት   ሥራውን   ስንገለብጥ   ከተማሪው   ሁሉ ወደ   ኋላ   እንቀር   ነበር፡፡   ሕፃናት   ስለ   ነበርን፣   ከዚያም   የተሻለ   ስላላየን   መጽሐፍን   ለአራት   ለአምስት መውሰድ   የዓለም   ሥርዓት   መስሎን   ነበር   ያደግነው፡፡   የመጽሐፍ   ኮንደሚኒየም   አትሉም፡፡ የሚገርመው   ነገር   ይህ   አሠራር   በሁለተኛ   ደረጃም   ሆነ   በኮሌጅ   ደረጃ   ሳይሻሻል   ነው   እኛ   ትምህርት « ጨርሰን »   የወጣነው፡፡   በተለይ   አዲስ   አበባ   ዩኒቨርሲቲ   ስድስት   ኪሎ   እያለሁ   እንድናነብ የሚሰጠንን   መጽሐፍ   ቤተ   መጻሕፍት   ሄዶ   ማግኘት   አስቸጋሪ   ነበር፡፡   አንዳንድ   ጊዜ   ሌላ   ሰው   ቀድሞ ያወጣውና   ወረፋ   ያዙ   እንባላለን፡፡   ወረፋው   ሳይደርሰን   ፈተናው   ቀድሞ   ይደርሳል፡፡   አንዳንድ   ጊዜ ደግሞ   ከነ   አካቴው   መጽሐፉ   አይኖርም፡፡   ምነው ?   ስንል  « መምህሩ   አውጥቶታል »   እንባላለን፡፡   ሌላ ጊዜ   ደግሞ   « በኮርስ   አውት   ላይኑ »   ላይ   ያለው   የመረጃ   መጻሕፍት   ዝርዝር   ከሌላ   የተገለበጠ   ይሆንና ቤተ   መጻሕፍቱ   እንኳን   ሊኖረው   ሰምቷቸውም   አያውቅ፡፡   እንዲህ   እኛ   መጽሐፍ   ብርቅ   ሆኖብን   አድገን   በኋላ   ገዝታችሁ   አንብቡ   ስንባል   ውቃቤ   ሊቀርበን አልቻለም፡፡   እኛ   በመጽሐፍ   መከራ   እንጂ   መች   ደስታ   አይተን