የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች መንግስት በዞኑ የምፈጸመውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ፡ እስር እና እንግልት እንዲያቆም ጠየቁ፤ በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት በምል የታሰሩ ግለሰቦች ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ እንዲፈቱ ኣሳሰቡ።
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው ያኗገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ መንግስት በሰበብ ኣስባቡ የተለየ ኣመለካከት እና ኣስተሳሰብ የምያራምድ ግለሰቦችን በኣስፈለገው ጊዜ እና ወቅት የተለያዩ ስሞችን በመስጠት በማስር ላይ ነው። በሃዋሳ ከተማ ሌዊ ሆቴል ሲዝናኑ ያገኘናቸው ካላ ጌታሁን ሳርምሶ የተባሉ በከተማዋ የኣዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪ እንደተናገሩት፤ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት በተለይ ከክልሉ ባለስልጣናት ፖለቲካዊ ኣመለካት የተለየ ያለ ኣመለካከት ያላቸውን ግለሰቦች ማሰሩ የተለመደ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በኣሁኑ ጊዜ በተለይ ከሲዳማ የፊቼ በዓል ማግስት ጀምሮ በርካታ ሰዎች ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት ተከሰው ታስረዋል። ግለሰቦች የመሰላቸውን ፖለቲካዊ ሆነ ማህባራዊ ኣመለካከትን ያለ ምንም ገደብ እንዲያራምዱ በምፈቅድ ህገ መንግስት ባለባት ኣገር ግለሰቦች የተለየ ኣመለካከት ስላላቸው ብቻ ስብኣዊ መብታቸው መጣሱ ኣግባብነት የለውም ብለዋል። ወጣት ንቆዲሞስ ኣየለ የተባለ በሃዋሳ ከተማ የባጃጂ ታክሲ ሽፌር በበኩሉ፤ የሲዳማ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በተመለከተ ህዝባዊ ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በተለይ ወጣቶች በመንግስት የጸጥታ ሰዎች ማስፈራሪያ እንደምደርሳቸው ገልጿ፤ ለህዝቡ ጥያቄ ኣግባብነት ያለውን ምላሽ መስጠት እንጂ ሰዎችን ማስር እና ማንገላት መፍትሄ ኣይደለም ብለዋል። ካላ ዘርሁን ናራሞ የተባሉ በተለምዶ ስሙ ሊዝ ሰፈር በምባለው ኣከባቢ መንገድ ላይ ሲጓዙ ያገኘናቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ፤ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃዋሳ ከተማ ብሎም በሲዳማ ዞን ወረዳዎች ውስጥ ግለሰቦች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቦታቸው እና ከስራ ገበታቸው እየተያዙ እንደምታሰሩ ጠቅሰው፤ ግለሰቦች በተጠረጠሩት ጉዳይ ላይ