የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳን በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ (ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ)
የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳ በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሕገ-መንግስቱ በአንቀጸ 39 ላይ የተደነገገውን መብት እስክንጎናጸፍ ድረስ የማንነት ጥያቄአችን ከምንም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ በምንም ዓይነት ሁኔታ አይቆምም!!! ውድ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ በሙሉ እንኳን በዓይነቱ ልዩ ለሆነውና በሲዳማ ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል ለሚገባው ለ2005 ዓ.ም ሲዳማ የዘመን መለወጫ fichee cambalaalla በዓል ለማየት፣ለመስማት አበቃችሁ/ በሰላም አደረሳችሁ/ን/!! የሲዳማ ዘመን መለወጫ የfichee cambalaalla በዓል ነሐሴ 9/2004/ በሲዳማ ቀን አቆጣጠር መስከረም 1/ 2005 ዓ.ም በአስገራሚ ሁኔታ ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫዉ ወደ ሀዋሳ የመጡት የብሔሩ ተወላጆች ብቻ ሌሎች ታዳሚዎችን ሳይጨምር በጥቂቱ ቁጥራቸው ወደ 2.5ሚሊየን የሚጠጉ በባህላዊ አጋጌጥ ተውበው ጦርና ጋሻቸውን አንግበው በዋና ከተማቸው በድምቀት ለማክበር በቄጣላ በመግባታቸው የከተማውን ሕዝብ ጉድ ያስባለና ያስደነቀ ታሪካዊ በዓል መሆኑ ይታወሳል፡፡ በዕለቱም ሰፊው የሲዳማ ሕዝብና የበዓሉ ታዳሚዎች/ተጋባዥ እንግዶች በዓሉን እንደጓጉለት ለማክበር አልታደሉም፡፡ በዓሉን ለማክበር የወጣውን የሕዝብ ብዛት ከሩቁ የተመለከቱና ከየአቅጣጫው በቄጣላ የዘመኑ የሙዚቃ ቅንብር በማይተካ መ